Get Mystery Box with random crypto!

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ሀገር አቀፍ የአምሳለ ችሎት ውድድር በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ | Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ሀገር አቀፍ የአምሳለ ችሎት ውድድር በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ

=============

ደብረ ማርቆስ ዩንቨርሲቲ | ሚያዚያ 21 /2015 ዓ.ም | ህዝብ ግንኙነትና ኮምኒኬሽን ዳይሬክቶሬት|
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በ2015 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የምስለ ችሎት ውድድር እንዲያካሂድ በመመረጡ በሀገሪቱ ካሉ 12 ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ተወዳዳሪ ተማሪዎች ከሚያዝያ 20 ጀምሮ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ በወድድሩ እተሳተፉ ይገኛሉ ፡፡


በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ህግ ትቤት ዲን አቶ አማረ ስጦታው ለተወዳዳሪዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ካቀረቡ በኋላ የምስለ ፍ/ቤት ውድድር መካሄድ የተጀመረው በ2008 ዓ.ም ሲሆን በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ሲካሄድ ቆይቶ በ2015 ዓ.ም 7ኛው ዙር በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

ይህንን ዓይነት ውድድር ማካሄድ የትምህርት ጥራትን ማስጠበቂያ አንደኛው መንገድ ቢሆንም ከዚህ በተጨማሪ በሀገራችን ያሉ የተለያዩ ባህሎች ፣ አካባቢዎች፣ታሪካዊ ቦታዎችን እንድናውቅና እርስ በርስ እንድንተዋወቅ ሰፊ ዕድል እንደሚፈጥር የጠቆሙት አቶ አማረ ውድድሩ መሸናነፍን መሰረት ያደረገ ሳይሆን ወንድማማችነትንና አንዳችን ከአንዳችን የምንማማርበት እንደሚሆን ምኞታቸው መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል፡፡

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶ.ር በለጠ ያዕቆብ እውነተኛ ፍትህን ለማስፈን በሙያው የተካኑ ፣ ቁርጠኛ ፣ሚዛናዊ ለእውነት ያደሩ ፣ ህሌናቸውን ዳኛ ያደረጉ ወጣቶች እንደሚያስፈልጉ ጠቅሰው እንደዚህ ዓይነት ዳኞችን ፣ ዐቃቢ ህጎችን፣ የፍትህ ሰዎችን ለማግኘት ደግሞ ይህን መሰል ሀገራዊ የውድድር መድረኮች እንደሚያስፈልጉ እና ይህን አጠናክሮ መቀጠል ተገቢ ነው ሱሉም አክለዋል፡፡

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የዕውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ!

===========

ለተጨማሪ እና አዳዲስ መረጃዎች


#ቴሌግራም፡ https://bit.ly/3HbDPCB

#ፌስቡክ፡ https://bit.ly/3mYfnNW

#ዩቱዩብ፡ https://bit.ly/3L73hu3

#ዌብሳይት www.dmu.edu.et