Get Mystery Box with random crypto!

ለደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ እና አካባቢው ማህበረሰብ 97.7 ሬዲዮ ጣቢያ ጋዜጠኞች ስልጠና ተሰጠ | Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

ለደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ እና አካባቢው ማህበረሰብ 97.7 ሬዲዮ ጣቢያ ጋዜጠኞች ስልጠና ተሰጠ

================
ደብረ ማርቆስ ዩንቨርሲቲ | መጋቢት 13/2015 ዓ.ም | ህዝብ ግንኙነትና ኮምኒኬሽን ዳይሬክቶሬት |
በስልጠናው የዩኒቨርሲቲያችን የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚደንት ይኸይስ አረጉ ዶ/ር የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲና አካባቢው ማህበረሰብ ኤፍ ኤም 97.7 ሬድዮ ጣቢያ የቦርድ አባላት በተገኙበት "FOJO" በተባለ የሚዲያ ተቋም ከመጋቢት 12 እና 13/2015 ዓ.ም ለሁለት ቀናት ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።

ስልጠናው ትኩረት ያደረገባቸው ርዕሰ ጎዳዮች *የማህበረሰብ ሬዲዮ እና ዘለቄታዊነት ፤
*የምርምራ ጋዜጠኝነት ምንነትና አተገባበር እና
የመጽሔት ፕሮግራም ቅጽ አዘገጃጀት የሚሉ ሲሆኑ
ስልጠናውን የሚሰጡትም W. Jacob Ntshangase, "Head Wits Radio Academy Wits center for Journalism እና ረዳት ፕሮፌሰር ዘላለም ተስፋዬ በባህርዳር ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነት እና ተግባቦት ትምህርት ክፍል መምህር ናቸው።

የማህበረሰብ ሬድዮን ዘላቂ ለማድረግ የተነሱ ነጥቦች
*ጠንካራ አቅም ያለው አስተዳደር ማዋቀር፤
*የራሱን ገቢ እንዲያመነጭ ማስቻል፤
የማህበረሰብ የሬዲዮ ጣቢያን ሚናና ተግባር በግልጽ ለይቶ ማስቀመጥና የመሳሰሉት ሲሆኑ

የማህበረሰብ ሬድዪ ጣቢያ ዘላቂ እንዳይሆን የሚያደርጉ ተግዳሮቶች :-
* የጋዜጠኝነት ሙያ በትክክል አለመረዳት፤
*በሙያው በቂ የሆነ እውቀት እና ክዕሎት አለመኖር የሚሉት ነጥቦች ተጠቅሰዋል።

በሁለተኛው ርዕሰ ጉዳይ በምርመራ ጋዜጠኝነት ምንነትና አተገባበሩ ላይ የተነሱ ነጥቦች :-
*የምርመራ ጋዜጠኝነት ተግዳሮቶች፤
*የምርመራ ጋዜጠኝነት ደረጃዎች ፤
*በመርመራ ጋዜጠኝነት ዙርያ ለሚሰሩ ጋዜጠኞች ሊደረግ የሚገባ ጥበቃ እና ደህንነት ፤
*የምርመራ ጋዜጠኝነት መሰረታዊ ኳሊቲዎች፤
*የምርመራ ጋዜጠኝነት በኢትዮጵያ ያሉ ፈተናዎች፤
*የምርመራ ጋዜጠኝነት ሙያ ሊተገበሩ የሚገቡ ነገሮች የሚሉት አንኳር ጉዳዮች ተነስተዋል።

ስልጠናው ዛሬም የሬዲዮ መጽሔት ፕሮግራም ቅጽ አዘገጃጀት ላይ ትኩረት እንደሚያደርግም ተጠቁሟል።

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የዕውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ

ለተጨማሪና ወቅታዊ መረጃዎች



https://t.me/Debre_Markos_University

https://www.facebook.com/dmu.edu

#ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UCqQDHEyYDen3aybySpYsF_Q

#ዌብሳይት www.dmu.edu.et