Get Mystery Box with random crypto!

“እኔ የእህቴ ጠባቂ ነኝ ” በሚል መሪ ቃል የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በደብረ ማርቆስ ዩ | Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

“እኔ የእህቴ ጠባቂ ነኝ ” በሚል መሪ ቃል የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተከበረ

=================

ደብረ ማርቆስ ዩንቨርሲቲ | የካቲት 30/2015 ዓ.ም | ህዝብ ግንኙነትና ኮምኒኬሽን ዳይሬክቶሬት |
በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ112ኛ ጊዜ፣ በሀገራችን ለ47ኛ ጊዜ የተከበረውን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን (March 8 ) “እኔ የእህቴ ጠባቂ ነኝ ” በሚል መሪ ቃል የካቲት 29/2015 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲያችንም በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ተከብሮ ውሏል፡፡

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ሴቶች፣ ወጣቶች እና ኤች አይቪ ኤድስ መከላከል ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን (March 8) የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ መምህራንና ሰራተኞች፣ ተማሪዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር እንግዶች በተገኙበት ተከብሯል፡፡

በጉባዔው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ታፈረ መላኩ (ዶ/ር) ሴቶችን ወደ ኃላፊነት በማምጣቱ ረገድ እንደ ተቋም ምቹ ሁኔታዎችን መሻሻሎች እንዳሉ ጠቁመው እንደ ሀገር ፍትህና ሰላም እንዲሰፍን የሴቶችን የነቃ ተሳትፎና አበርክቶ ከፍ እንዲል ማስቻል ያስፈልጋል ሲሉ ገልፀዋል። በዚህ ረገድ ደግሞ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ያሉ ሴቶች ሁለንተናዊ በሆነ መንገድ የተሻለ ንቃተ ህሊና አላቸው ተብሎ ስለሚታሰብ ሀገርንም፣ ተቋምንም፣ መሞገት የሚችሉ ሴቶችን መፍጠር ብንችል መልካም ነው ሲሉም አክለዋል፡፡

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ማህበራዊና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ሶሾሎጅ ትምህርት ክፍል መምህር አቶ ደግ አረገ ዋለ "የሴቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት በምስራቅና ምዕራብ ጎጃም ዞን ተተኩሪነት" በሚል ርዕስ መነሻ ጽሁፍ አቅርበው የመርሃ ግብሩ ተሳታፊዎች ሀሳብና አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የሴቶችና ወጣቶች እና ኤች አይቪ ኤድስ መከላከል ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላም መክብብ በበኩላቸው ሴቶችን እኩል ተሳታፊ ማድረግ ተገቢ እንደሆነ ገልፀው ፍትሃዊነት ላይ ጠንክሮ መስራትና ሴቶች በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ኋላ የሚቀሩባቸው ተፈጥሯዊም ሆነ ማህበረሰባዊ ችግሮች እንዳሉባቸውም አንስተዋል።

የደብረ ማርቆስ ከተማ ሲቢኤም ኢትዮጵያ ደርጅት ሃላፊ አቶ ገረመው አቅሌሳ እንደተናገሩት ድርጅታቸው በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ስራ ከጀመረ ጀምሮ ብዙ ስራዎችን ያከናወነ መሆኑን ጠቅሰው ዛሬ የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን (March-8) ምክንያት በማድረግ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ 3 ሴት ተማሪዎች ድርጅቱ የገንዘብ ሽልማት እንዳዘጋጀም ገልፀዋል ፡፡

በዚህም መሠረት፦
1ኛ. ከኢኮኖሚክስ ትምህርት ክፍል ተማሪ ፋሲካ ካሳሁን 3.99 ውጤት በማምጣት 4200 ብር ፣
2ኛ. ከአካውንቲንግና ፋይናንስ ትምህርት ክፍል ተማሪ ትዕግስት ታረቀኝ 3.96 ውጤት በማምጣት 3700 ብር
3ኛ. ከኢኮኖሚክስ ትምህርት ክፍል ተማሪ ስንዴ ክንዴ 3.92 ውጤት በማምጣት 3200 ብር ተሸልመዋል።

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የዕውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ

=============

ለተጨማሪና አዳዲስ መረጃዎች


#ፌስቡክ https://www.facebook.com/dmu.edu

#ቴሌግራም https://t.me/Debre_Markos_University

#ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UCqQDHEyYDen3aybySpYsF_Q

#ዌብሳይት www.dmu.edu.et