Get Mystery Box with random crypto!

ተማሪዎቻችን እንኳን ደህና መጣችሁ! የአቅም ማሻሻያ ተጠቃሚ ተማሪዎች ወደ ግቢ በመግባት ላይ ይገ | Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

ተማሪዎቻችን እንኳን ደህና መጣችሁ!

የአቅም ማሻሻያ ተጠቃሚ ተማሪዎች ወደ ግቢ በመግባት ላይ ይገኛሉ

============
ደብረ ማርቆስ ዩንቨርሲቲ | የካቲት 29/2015 ዓ.ም |ህዝብ ግንኙነትና ኮምኒኬሽን ዳይሬክቶሬት |
የትምህርት ሚኒስቴር በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ከፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው ውጤታቸው ከግማሽ በታች የሆነባቸው ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ገብተው የአቅም ማሻሻያ/ ሪሚዲያል ተጠቀሚ እንዲሆኑ በወሰነው መሰረት ዩኒቨርሲቲያችን 3 ሺህ 91 ተማሪዎችን #በዋናው_ግቢ ፣ #በጤና እና #በቡሬ ካምፓሶች በመቀበል ላይ ይገኛል፡፡

የእነዚህ ተማሪዎች የመጨረሻ መግቢያ ቀን ነገ በ30/2015 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ የሬጂስትራር ዳይሬክቶሬት ቀደም ሲል ማሳወቁ ይታወቃል።

===========

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የዕውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ

=============

ለተጨማሪ አዳዲስ መረጃዎች



#ዌብሳይት www.dmu.edu.et

#ፌስቡክ https://www.facebook.com/dmu.edu

#ቴሌግራም https://t.me/Debre_Markos_University

#ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UCqQDHEyYDen3aybySpYsF_Q