Get Mystery Box with random crypto!

በፈተና ንድፍ አዘገጃጀት (Test Blue Print Preparation ) ላይ ትኩረት ያደረገ ስል | Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

በፈተና ንድፍ አዘገጃጀት (Test Blue Print Preparation ) ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና ለመምህራን ተሰጠ

=================

ደብረ ማርቆስ ዩንቨርሲቲ | የካቲት 29/2015 ዓ.ም | ህዝብ ግንኙነትና ኮምኒኬሽን ዳይሬክቶሬት | በያዝነው አመት ለሁም የዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች የሚሠጠውን የመውጫ ፈተና ውጤታማ ለማድረግ ዩኒቨርሲቲያችን የተለያዩ ዝግጅቶችን በማድረግ ላይ ይገኛል።

በዛሬው ዕለም የፈተና ንድፍ አዘገጃጀት ላይ (Exam Blue Print Preparation) በተቋማዊ ጥራት ማረጋገጫ ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ለመምህራን ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚደንት ይሄይስ አረጉ (ዶ/ር) ምንም እንኳ በሀገራችን የተለያዩ ችግሮች ቢለዋወጡም ብቁ ትውልድ በማፍራት ታላቋን ኢትዮጵያ ለመፍጠር ሙያዊ ኃላፊነታችንን መወጣት አለብን ብለዋል፡፡

የተቋማዊ ጥራት ማረጋገጫ ዳይሬክተር አባትሁን አለኸኝ (ዶ/ር) የሚወጣው ፈተና መምህራን ከሚያስተምሩት የትምህርት ዓይነት ዓላማና ግብ ጋር መጣጣሙን ለመለካት የፈተና ንድፍ ማዘጋጀት አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመው መምህራን የሚመሩበትን የፈተና ንድፍ ማዘጋጀት እንዲችሉ በመጀመሪያ ስልጠና መስጠት አስፈላጊ እንደሆነ ገልፀዋል::

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የዕውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ

=============

ለተጨማሪ አዳዲስ መረጃዎች


#ዌብሳይት www.dmu.edu.et

#ፌስቡክ https://www.facebook.com/dmu.edu

#ቴሌግራም https://t.me/Debre_Markos_University

#ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UCqQDHEyYDen3aybySpYsF_Q