Get Mystery Box with random crypto!

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ሴቶች ፣ወጣቶች እና ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ዳይሬክቶሬት ለሴት መምህራን ስለ | Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ሴቶች ፣ወጣቶች እና ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ዳይሬክቶሬት ለሴት መምህራን ስለ ፕሮጀክት ቀረጻ አጻጻፍ ስልጠና ሰጠ

================

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ፥ የካቲት 22/2015 ዓ.ም ( ህዝብ ግንኙነትና ኮምንኬሽን ዳይሬክቶሬት ) በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ሴቶች ፣ወጣቶች እና ኤች. አይ.ቪ /ኤድስ ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት በዩኒቨርሲቲው በማስተማር ላይ ለሚገኙ 30 ሴት መምህራን ስለ ፕሮጀክት ቀረጻና አጻጻፍ የካቲት 21 ና 22/2015 ዓ.ም ለሁለት ተከታታይ ቀናት ስልጠና ተሰጧል ፡፡

በስልጠና ፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ይኸይስ አረጉ እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው እንዲህ ያሉ ስልጠናዎች ለሴት ምህራን ሲሰጥ የቆየ ቢሆንም ተግባር ላይ ከማዋል አንጻር ግን ውስንነት እንዳለ ጠቁመው ሴትነት አሸናፊነት ነው ፤ ሴትነት ጀግንነት ነው ፤ ሴትነት ታላቅነት ነው ፤ ሴትነት ስኬት ነው ፤ ሴትነት ውጤታማነትና መሪነት ነው ፤ ስለዚህ ይህን ስልጠና በአግባቡ በመከታተልና ወደ ተግባር በመግባት ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት ራሳችውን ማዘጋጀት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል ፡፡


የስልጠናውን ዓላማ በተመለከተ ሀሳባቸውን የሰጡት በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የፕሮጀክት ቀረጻ ትብብር ዳይሬክቶሬት ዶ/ር አበበ በላይና በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ግብርናና ተፈጥሮ ሃብት መምህር ዶ/ር አማረ ተስፋው የፕሮጀክት ቀረጻና አጻጻፍ ፡- ዓለማቀፍ ፕሮጀክቶችን እንዴት ማሸነፍ እንደሚቻል ፣ አንድ ፕሮጀክት ምን ምን ነገሮችን ማሟላት እንዳለበት ፣ ፕሮጀክቱን ለማሸነፍ የትኞቹ አጋር አካላት መካተት እንዳለባቸው ግንዛቤ ለማስጨበጥና ተነሳሽነት በመፍጠር እንስት መምህራን ወደ ፕሮጀክት ቀረጻ ስራ እንዲገቡ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን ገልፀዋል ፡፡


በስልጠና መረሃ ግብሩ ላይ ሲሳተፉ ያገኘናቸው በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የባዮ ቴክኖሎጂ ትምህርት ክፍል መምህርት ብርቱካን ሲሳይና በግብርናና ተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ የዕጽዋት ሳይንስ ትምህርት ክፍል መምህርት አለምነሽ እስከዚያ እንደገለጹት ይህ ስልጠና በጣም አስፈላጊና በጉጉት ሲጠብቁት እንደነበር ጠቁመው ከስልጠናውም ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ ማህበረሰብን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችል ግንዛቤ ማግኘታቸውን ገልፀዋል።

ከተለያዬ የሙያ መስክ መሰባሰባቸው ደግሞ መረጃ ለመለዋወጥ ፣ልምድ ለመካፈልና በጋራ ለመስራት ዕድል እንደፈጠረላቸውም ጨምረው ተናግረዋል።

ከዚህ ስልጠና በኋላም በሀገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ሀገሮች ፕሮጀክቶች ላይ ለመሳተፍና ፕሮጀክቶችን ለማዘጋጀት ከፍተኛ ተነሳሽነት ተፈጥሮብናል በማለት ገልፀዋል። በመጨረሻም ይህን ስልጠና ላመቻቸላቸው ለደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ሴቶች፣ ወጣቶች፣እና ኤች.አይ.ቪ /ኤድስ ዳይሬክቶሬት ምስጋና አቅርበዋል ፡፡

=============
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የዕውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ


ለተጨማሪ መረጃዎች



#ዌብሳይት www.dmu.edu.et

#ፌስቡክ https://www.facebook.com/dmu.edu

#ቴሌግራም https://t.me/Debre_Markos_University

#ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UCqQDHEyYDen3aybySpYsF_Q