Get Mystery Box with random crypto!

ለአዲስም ሆነ ለነባር መምህራን አጫጭር የሙያ ላይ ስልጠናዎች በየጊዜው ቢሰጡ ብቁ ዜጋ ለማፍራት እ | Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

ለአዲስም ሆነ ለነባር መምህራን አጫጭር የሙያ ላይ ስልጠናዎች በየጊዜው ቢሰጡ ብቁ ዜጋ ለማፍራት እንደሚያስችል መምህራን ገለፁ

ደብረ ማርቆስ ዩንቨርሲቲ፡- የካቲት 22/2015 ዓ.ም (ህዝብ ግንኙነትና ኮምኒኬሽን ዳይሬክቶሬት) ዩንቨርሲቲው በመምህርነት ሙያ ሳይመረቁ ወደ መምህርነት ሙያ ለሚሰማሩ አዲስ ለተቀጠሩና በዝውውር ለመጡ መምህራን አጫጭር የሙያ ላይ ሥልጠናዎችን ሰጥቷል፡፡

አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ይኼይስ አረጉ (ዶ/ር) የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ በመጀመሪያ ባለሙያዎችን ማብቃት ወሳኝ በመሆኑ አጫጭር ስልጠናዎችን መስጠት አስፈላጊ መሆኑን ገልፀው የማስተማር ሙያ ሣይንስን መግለፅ፣ ብቃትን ማሳየትና ልምድን ማካፈል በመሆኑ ዕውቀት በወረቀት ተጀምሮ በወረቀት የሚያልቅ ሳይሆን ህይወታችንን የሚነካና ተግባር ላይ የሚውል መሆን እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡ መምህራን ትውልድ የመቅረፅ ትልቅ አደራ ስላለባቸው ኃላፊነታቸውን ባግባቡ መወጣት እንደሚገባቸውም አሳስበዋል፡፡

የስልጠናው ተሳታፊ መምህር በዕውቀቱ አየለ የሙያ ላይ ስልጠናው መሰጠቱ እንዳስደሰታቸውና ሰው ሙሉ ስላልሆነ በየጊዜው ተከታታይ ስልጠናዎች ቢሰጡ የተሻለ ትውልድ ለመቅረፅ እንደሚያስችላቸው ገልፀዋል፡፡

ሌላው አስተያየታቸውን የሰጡን መምህር ዮሀንስ መንግስት ከዚህ በፊት የመምህርነት ሙያን ባለመሰልጠናቸውና ለሙያው አዲስ በመሆናቸው ወደ ስራ ለመግባት ተቸግረው እንደነበርና ስልጠናው በመሰጠቱ ክፍተታቸውን እንደሞላላቸው አንስተዋል፡፡
ይህንን ስልጠና ላመቻቸላቸው ዩንቨርሲቲውና ስልጠናውን ለሰጡት መምህራንም ምስጋናቸውን አቅርበው ከስልጠናው በተጨማሪ የማስተማርያ ግብዓቶች እንዲሟሉላቸው አሳስበዋል፡፡

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የዕውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ

ለተጨማሪ መረጃዎች



#ዌብሳይት www.dmu.edu.et

#ፌስቡክ https://www.facebook.com/dmu.edu

#ቴሌግራም https://t.me/Debre_Markos_University

#ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UCqQDHEyYDen3aybySpYsF_Q