Get Mystery Box with random crypto!

ለአዲስ ገቢ መደበኛ ተማሪዎች አጠቃላይ ገለፃ ተሰጠ ደብረ ማርቆስ ዩንቨርሲቲ ፡- የካቲት 22/ | Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

ለአዲስ ገቢ መደበኛ ተማሪዎች አጠቃላይ ገለፃ ተሰጠ

ደብረ ማርቆስ ዩንቨርሲቲ ፡- የካቲት 22/2015 ዓ.ም (ህዝብ ግንኙነትና ኮምኒኬሽን ዳይሬክቶሬት) በ2015 ዓ.ም በተሰጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና ከ50% በላይ በማስመዝግብ ዩንቨርሲቲያችንን መርጠው ለገቡ አዲስ መደበኛ ተማሪዎች ስለመማር ማስተማሩ፣በዩንቨርሲቲው ውስጥ ስለሚያገኟቸው አገልግሎቶች፣ ማክበር ስለሚገባቸው ህግና ደንቦች በሚመለከት የአካዳሚክ አመራሮች ዝርዝር ገለፃ ተሰጠ፡፡

በዩንቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ኤክስክዩቲቭ ዳይሬክተር በለጠ ያዕቆብ (ዶ/ር) ተማሪዎችን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት በዩንቨርሲቲ ቆይታቸው በስነምግባር የታነፁ፣ ጠንካራና ለዓላማቸው ቁርጠኛ በመሆን ለስኬት መብቃት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡በተጨማሪም የተቋሙን ህገ ደንብ በማክበር፣ ተቻችለው፣ተከባብረውና ተረዳድተው መኖር እንዳለባቸው ጠቁመው መልካም የትምህርት ዘመን እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል፡፡

የተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንት ተማሪ ጌጤነህ ሸገን እስካሁን በዩንቨርሲቲ ቆይታው ስለዩንቨርሲቲው፣ስለመምህራንና አካባቢው ማህበረሰብ የተመለከተውን ምስክርነት በመስጠት የተማሪዎች ህብረት ስለሚያከናውናቸው ተግባራትና አዲስ ተማሪዎችን ለማብቃት እገዛ እንደሚያደርጉ ተናግሯል፡፡

የአስተዳደርና ተማሪዎች ጉዳይ ኤክስክዩቲቭ ዳይሬክተር ጥላሁን ድረስ ( ረ/ፕሮፌሰር ) በበኩላቸው በዩንቨርሲቲ ውስጥ ትምህርት ብቻ ሳይሆን መልካም ስነምግባርም ወሳኝነት እንዳለው ገልፀው ስለሚያገኟቸው አገልግሎቶችና ማክበር ስላለባቸው ግዴታዎች ዝርዝር ማብራሪያዎችን ሰጥተዋል፡፡ ባጠቃላይ ከተማሪዎች ጋር በስፋት የሚገናኙ የስራክፍሎች ሁሉም የየራሳቸውን ገለፃ አድርገዋል፡፡

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የዕውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ

ለተጨማሪ መረጃዎች



#ዌብሳይት www.dmu.edu.et

#ፌስቡክ https://www.facebook.com/dmu.edu

#ቴሌግራም https://t.me/Debre_Markos_University

#ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UCqQDHEyYDen3aybySpYsF_Q