Get Mystery Box with random crypto!

ታሪክ ለመስራት ምንም የሚያግደን ነገር የለም ፤ ታሪክ መስራት ከአባቶቻችን የወረስነው ተፈጥሯዊ ፀ | Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

ታሪክ ለመስራት ምንም የሚያግደን ነገር የለም ፤ ታሪክ መስራት ከአባቶቻችን የወረስነው ተፈጥሯዊ ፀጋችን ነው" ( ዶ/ር ይኸይስ አረጉ የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚደንት)

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፦ ( ህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት)

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ም/ቤት ጽ/ቤት እና የኢትዮጵያ ታሪክ ባህል ቅርስ አድን ድርጅት በጋራ የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች፣ መምህራን እና ሰራተኞች በተገኙበት ታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ ህዝባዊ የንቅናቄ መድረክ ተካሄደ ።

የመድረኩን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚደንት ዶ/ር ይኸይስ ሀረጉ ሲሆኑ በንግግራቸውም
"ታሪክ ለመስራት ምንም የሚያግደን ነገር የለም ታሪክ መስራት ከአባቶቻችን የወረስነው ተፈጥሯዊ ጸጋችን ነው ፤ ዛሬም ወደ ፊትም ታሪክ እየሰራን እንቀጥላለን" ሲሉ ገልፀዋል።

አባቶቻችን የአድዋ ድልን በማስመዝገብ ፣ የአክሱም ሃውልትን በማቆም ፣ የላሊበላ ውቅር አቢያተ ክርስቲያናትን በማነጽ እና ሌሎችንም አስደናቂ የታሪክ ቱርፋቶችን ሰርተውልን አልፈዋል።

ታላቁ የህዳሴ ግድብ ደግሞ የነገው ትውልድ እኛን የሚያከብርበት ፣ የሚዘክርበት እና ልማት የሚረጋጥበት የዚህ ትውልድ አሻራ ነው የሚል እምነት እንዳላቸው ጠቁመዋል።

ይህንን የንቅናቄ ጉዞም እንደ ተቋም በአድናቆት እንደሚንቀበሉት እና የሚጠበቅባቸውን ሁሉ እንደሚያደርጉም ቃል ገብተዋል፡፡

ኢንጅነር ነጮ ወርቁ የኢትዮጵያ ታሪክ ባህል ቅርስ አድን ድርጅት ፕሮጀክት ማናጀር እና የጉዞው አስተባባሪ እንደገለፁት የኢትዮጵያ ታሪክ ባህል ቅርጽ አድን በጎ አድራጎት ድርጅት ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ጋር በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ህዝባዊ ንቅናቄን በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በመንቀሳቀስ ቅስቀሳዎችን በማድረግ ፣ የህዳሴ ግድቡ ግንባታ የደረሰበትን ደረጃ መረጃ የመስጠትና ገቢም የማሰባሰብ ተግባር እንደሚያከናውን ጠቁመዋል።

በመሆኑም የተጀመረውን ለመጨርስ እና ግንባታውን ለማፋጠን ኢትዮጵያውያን እንደዚህ ቀደሙ በቦንድ ግዥ አና "በ8100A" አስተዋፅኦ እንዲያበረክት ጥሪ አቅርበዋል፡፡
==========
ለተጨማሪ መረጃዎች ከታች የተቀመጡትን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ!

ዌብሳይት www.dmu.edu.et

#ቴሌግራም
https://t.me/Debre_Markos_University

#ፌስቡክ https://www.facebook.com/dmu.edu

#ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UCqQDHEyYDen3aybySpYsF_Q