Get Mystery Box with random crypto!

በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው ከ50% በላይ በማስመዝገብ ዩኒቨርሲቲያችን | Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው ከ50% በላይ በማስመዝገብ ዩኒቨርሲቲያችንን የመጀመሪያ ምርጫቸው ላደረጉ ተማሪዎች ከዶክተር ታፈረ መላኩ (የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ) የተላለፈ አጭር የምስጋና መልዕክት

===============

አዲስ ገቢ ተማሪዎቻችን እንኳን ደስ አላችሁ!

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲን የመጀመሪያ ምርጫችሁ ስላደረጋችሁትም እጅግ አድርገን እናመሰግናለን! ዩኒቨርስቲያችን ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ እጅግ መልካም የሚባል የመማር -ማስተማር ባህል የገነባ ተቋም ነው። በመሆኑም ተመራቂዎቻችን በየትኛውም የሥራ ዘርፍ ውድድር አሸናፊዎች ናቸው።

ለሙያቸው ክብር የሚሠጡና በሚችሉት አቅም ሁሉ ተማሪዎቻቸውን ለማገዝ ሌት ተቀን የሚሠሩ መምህራን ስላሉንም በእጅጉ እንኮራለን፤ እናንተም አድለኞች ናችሁ። ሀገራችን ኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ በላይ በዘረኝነት ሥካር ውስጥ በወደቀችበት በዚህ ክፉ ሰዐት ሰውን በሰውነቱ ብቻ በሚመዝነው ደጉ የደብረማርቆስ ከተማና የአካባቢው ሕዝብ መሐል መገኘታችሁ ደግሞ እጅጉን መታደል ነው።

የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብና የአካባቢው ማህበረሰብ የአደራ ልጆቻቸው በመሆናችሁ እንደ ሁሌው አቅፈውና ደግፈው ለወግ ማረግ ያበቋችኋል።

መልካም የትም/ዘመን እንዲሆንላቸው እየተመኘሁ በድጋሜ እንኳን ደስ አላችሁ እላለሁ !

ታፈረ መላኩ (ዶ/ር)

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝደንት

"የዕውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ"


ዌብሳይት www.dmu.edu.et

ቴሌግራም https://t.me/Debre_Markos_University

ፌስቡክ https://www.facebook.com/dmu.edu

ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UCqQDHEyYDen3aybySpYsF_Q

ቲዊተር https://twitter.com/dmu_ethiopia

እንስታግራም https://www.instagram.com/dmu_ethiopia/

ሊንክድኢን https://www.linkedin.com/in/dmu-ethiopia/

ከእኛ ጋር ሰለምትሆኑ ምስጋናችን የላቀ ነው!