Get Mystery Box with random crypto!

የ70 ዓመት ዕድሜ ባለፀጋዋ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለመውሰድ ወደ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ገ | Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የ70 ዓመት ዕድሜ ባለፀጋዋ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለመውሰድ ወደ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ገቡ

================
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፣ መስከረም 29/2015 ዓ.ም ( ህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት) ስማቸው ወ/ሮ አቡኔ ወንዴ ታምር ይባላሉ። በምስራቅ ጎጃም ዞን በደብረ ኤሊያስ ወረዳ ተወለዱ ። ቤተሰቦቻቸው ገና በ7 አመት ዕድሜያቸው ባል እንዳጋቧቸው ይናገራሉ። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን ( ከ1-6ኛ ክፍል ) ከአጎታቸው ጋር ወደ መተሃራ ከተማ በመሄድ ተምረው በከፍተኛ ውጤት ማጠናቀቃቸውን ያስረዳሉ።

በወቅቱ ሲያስተምራቸው የነበሩት አጎታቸው በድንገተኛ ሁኔታ ከዚህ ዓለም በሞት እንደተለዬ የሚናገሩት ወ/ሮ አቡኔ የአጎታቸውን ሞት ተከትሎ ወደ ትውልድ ቀያቸው ቢመለሱም ቤተሰቦቻቸውም እርሳቸውን ለማስተማር የሚያስችል አቅም እንዳልነበራቸውና በዚህም የተነሳ የሚወዱትን የትምህርት ዓለም ለበርካታ አመታት አቋርጠው መቆየታቸውን ገልፀዋል። ገና በለጋነት ዕድሜያቸው ህይወት ፊቷን እንዳዞረችባቸው የሚናገሩት ወ/ሮ አቡኔ በየሰዎች ቤት እንጀራ በመጋገር፣ ደረቆት በመቁላት እና የተለያዩ የቀን ስራዎችን በመስራት ኑሮን እንደነገሩ ሲገፉ መቆየታቸውንም ይጠቁማሉ።

ሆኖም ለትምህርት በነበራቸው ጥልቅ ፍላጎት የተነሳ ለበርካታ አመታት አቋርጠውት የቆዩትን ትምህርት ካቆሙበት ለመቀጠል እድሉን እንዳገኙና በዚህ ዓመትም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለመውሰድ ወደ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ እንደገቡ አስረድተዋል።

ትምህርትን እድሜ እንደማይገድበውና ወጣቶችም ዓላማቸውን ለማሳካት ከአልባሌ ቦታዎች ራሳቸውን አቅበው ትምህርታቸው ላይ ብቻ እንዲያተኩሩም መክረዋል።

ያቋረጡትን ትምህርት እንደገና በጀመሩበት ወቅት ብዙ የስነ ልቦና ጫና የሚያሳድሩ ነገሮች ደርሰውብኛል የሚሉት ወ/ሮ አቡኔ የደብረ ኤሊያስ ወረዳ አመራሮችና አሰሪዎቻቸው እያበረታቷቸው እዚህ ለመድረስ እንደቻሉ በመግለፅ እስካሁን ከጎናቸው ሆነው ላበረታቷቸው ሁሉ ምስጋናቸውንም አስተላልፈዋል።

ለተጨማሪ መረጃዎች



ዌብሳይት www.dmu.edu.et

ቴሌግራም https://t.me/Debre_Markos_University

ፌስቡክ https://www.facebook.com/dmu.edu

ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UCqQDHEyYDen3aybySpYsF_Q

ቲዊተር https://twitter.com/dmu_ethiopia

እንስታግራም https://www.instagram.com/dmu_ethiopia/

ሊንክድኢን https://www.linkedin.com/in/dmu-ethiopia/

"የዕውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ!"

ከእኛ ጋር ሰለሆናችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው!