Get Mystery Box with random crypto!

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ለተለያዩ ትምህርት ክፍሎች የመፅሐፍ ስጦታ ተበረከተላቸው ========= | Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ለተለያዩ ትምህርት ክፍሎች የመፅሐፍ ስጦታ ተበረከተላቸው
==============
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ፣ መስከረም 24/2015 ዓ/ም (ህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት) አቶ በሃይሉ ሽፈራው ይባላሉ ፤ በሀገረ በአሜሪካ የሶስተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙ ሲሆን 250 መፅሐፍትን በወንድማቸው በአቶ ሶሎሞን ሺፈራው አማካኝነት ለዩኒቨርሲቲያችን የማህበራዊ ሳይንስና ስነ ሰብ ኮሌጅ አስረክበዋል።

በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ላይ የማህበራዊ ሳይንስና ስነ ሰብ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር አማረ ሰውነትን ጨምሮ የተለያዩ የስራ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን ይህ የመፅሐፍ ስጦታ እንዲገኝ ያስተባበሩት ደግሞ በዩኒቨርሲቲያችን የጋዜጠኝነትና ተግባቦት ትምህርት ክፍል መምህር ዶ/ር ሃይማኖት ጌታቸው መሆናቸው ተገልጿል።

የተበረከቱት ሐፅሐፍትም በተለይም ለአማርኛ፣ ለጋዜጠኝነትና ተግባቦት ፣ ለቲያትር ጥበባት እና ለፖለቲካ ሳይንስ ትምህርት ክፍሎች ማጣቀሻነት እንደሚያገለግሉ ተነግሯል።

የዕውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ!