Get Mystery Box with random crypto!

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ መምህራን፣ ሰራተኞችና ተማሪዎች በግፍ ለተገደለች እናት ልጆች ድጋፍ አደ | Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ መምህራን፣ ሰራተኞችና ተማሪዎች በግፍ ለተገደለች እናት ልጆች ድጋፍ አደረጉ
===============
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፣ መስከረም 20/2015 ዓ.ም (የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት) በደብረ ማርቆስ ከተማ ቀበሌ 05 ልዩ ቦታው ግሪን ፓርክ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በቅርቡ አንድ ግለሰብ የ11 ልጆቹን እናት በአሰቃቂ ሁኔታ እንደገደለ ልጆቹንም ያለአሳዳጊና ተንከባካቢ እንዳስቀራቸው ይታወሳል።

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ መምህራንናሰራተኞች እንዲሁም ተማሪዎች ለሟች ልጆች የምስራቅ ጎጃም ዞንና የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ልዩ ልዩ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት የገንዘብና የአይነት ድጋፍ አደረጉ ፡፡

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ማህበር ፕሬዚዳንት ዳሞት አንተነህ ዶ/ር እንደተናገሩት የመምህራን ማህበሩን አባላት ከተማሪዎች ህብረት ጋር በማቀናጀትና ኮሚቴዎችን ካዋቀርን በኃላ ገንዘቡን ከመምህራንና ሰራተኞች በተጨማሪም ከክረምት ተማሪዎች እንዳሰባሰቡት ተናግረዋል ፡፡ 2 ኩንታል ጤፍ ከደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ መንቆረር አግሮ ኢንዲስትሪ ኢንተር ፕራይዝ ድጋፍ እንደተደረገ ገልፀዋል፡፡

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት ምክትል ፕሬዚዳንት ተማሪ ጌጤነህ ሸገን እንደገለጹት የተማሪዎች ህብረት የተዋቀረው በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎችን ለማገልገል ቢሆንም እንዲህ አይነት አሰቃቂ ሁኔታዎች ሲፈፀሙና የውጩ ማህበረሰብ የእኛን እርዳታ ሲፈልጉ ህብረቱ ይህን አሳዛኝ ክስተት በመገንዘብ የግቢውን ተማሪዎች በማስተባበር ድጋፍ ማድረግ ተገቢ በመሆኑ 40 ሺህ 2 መቶ ብር እንዲሰበሰብ ተደርጓል ብለዋል፡፡ ገንዘቡም ለሟች ልጆች ተሰጥቷል።

የእርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴ አባል እና በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ትምህርት ክፍል መምህር ተዋበ ህብስቱ በበኩላቸው ይህንን ድጋፍ ለማድረግ ያነሳሳን የተፈጠረው ክስተት እጅግ ልብ የሚሰብርና አሳዛኝ በመሆኑ ሰብአዊነት ተሰምቶን ሲሆን የደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ መንቆረር አግሮ ኢንዲስትሪ ኢንተር ፕራይዝ ከደረቅ ምግብ ጀምሮ ለወደፊቱ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።
በተጨማሪም በተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክተር በኩልም የዘይትና ሽሮ እንዲሁም በርበሬ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም የደብረ ማርቆስ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ተመስገን ተድላ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ድርጊቱ ከተፈጸመ ጀምሮ እያደረገ ያለው ድጋፍ ለብዙዎቻችን አስተማሪና አርያነት ያለው ተግባር መሆኑን ጠቅሰው ከመማር ማስተማር ስራው በተጨማሪ ለውጩ ማህበረሰብ አርያ የሆነ ስራ መሆኑን ተናግረዋል ። ድጋፉ ዛሬ ብቻ የተጀመረ አለመሆኑንም ጨምረው ገልፀው ይህ አይነት ማህበራዊ ችግሮች ሲያጋጥሙ ዩኒቨርሲቲው ለአካባቢው ማህበረሰብ ቀድሞ የሚደርስ ተቋም መሆኑንም አክለዋል፡፡

================

ከታች ያስቀመጥናቸው የዩኒቨርሲቲያችን ይፋዊ የማህበራዊ ትስስር አድራሻዎች ናቸው። ተራ በተራ ሊንኮቹን እየተጫናችሁ ትወዳጁን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን

ዌብሳይት www.dmu.edu.et

ቴሌግራም https://t.me/Debre_Markos_University

ፌስቡክ https://www.facebook.com/dmu.edu

ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UCqQDHEyYDen3aybySpYsF_Q

ቲዊተር https://twitter.com/dmu_ethiopia

እንስታግራም https://www.instagram.com/dmu_ethiopia/

ሊንክድኢን https://www.linkedin.com/in/dmu-ethiopia/

"የዕውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ!"