Get Mystery Box with random crypto!

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ================= | Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት
=================

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ፦ ጳጉሜን 5/2014 ዓ.ም ( ደማዩ ህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት)

ለሁሉም የዩኒቨርሲቲያችን ማህበረሰብ እና ለመላው የሀገራችን ህዝብ በሙሉ እንኳን ለ2015 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡ በዓሉ የሰላም፣የጤናና የደስታ እንዲሆን እየተመኘሁ ይህን የዘመን መለወጫ በዓል ስናከብር ለዘመናት ተጠብቀው የቆዩትን የመረዳዳት፣ የመተሳሰብና ያለንን ለሌሎች የማካፈል መልካም እሴቶቻችንን በመተግበር በጦርነት የተጎዱና የተፈናቀሉ ወገኖቻችንን በማሰብና በመደገፍ እንድናሳልፍ ለማሳሰብ እወዳለሁ፡፡

በተጨማሪም አሁን ያለው የሀገራችን ነባራዊ ሁኔታና የሰላም እጦት አሳሳቢ መሆኑን ተገንዝበን መለያየት ለጠላት ምቹ ሁኔታን ስለሚፈጥር ሁላችንም አንድ በመሆን የሀገራችንን ሰላም የምንመልስበት ዘመን እንዲሆንልን በመላው የዩኒቨርሲቲያችን ማህበረሰብ ስም ልባዊ ምኞቴን እገልፃለሁ፡፡

ታፈረ መላኩ ዶ/ር
የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት

"የእውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ"

ከታች ያስቀመጥናቸው የዩኒቨርሲቲያችን ትክክለኛ የማህበራዊ ትስስር አድራሻዎቻችን ናቸው። ተራ በተራ ሊንኮቹን እየተጫናችሁ ትወዳጁን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን



ዩቲዩብ https://www.youtube.com/channel/UCqQDHEyYDen3aybySpYsF_Q

ዌብሳይት: www.dmu.edu.et

ቴሌግራም https://t.me/Debre_Markos_University

ፌስቡክ https://www.facebook.com/dmu.edu

ቲዊተር https://twitter.com/dmu_ethiopia

እንስታግራም https://www.instagram.com/dmu_ethiopia/

ሊንክድኢን https://www.linkedin.com/in/dmu-ethiopia/