Get Mystery Box with random crypto!

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ #የ2014 ዓ.ም የስራ ዓመት መገባደድን #የ2015 ዓ.ም የስራ ዘመን | Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ #የ2014 ዓ.ም የስራ ዓመት መገባደድን #የ2015 ዓ.ም የስራ ዘመን መተካትን አስመልክቶ ውይይት ተካሄደ

==============

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፦ (ደማዩ ህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት)

እንደ ዩኒቨርሲቲ 2014 ዓ.ም እንዴት አለፈ? ምን ጥንካሬዎች ነበሩን? ምን እጥረቶች ነበሩ? በ2015 የስራ ዘመንስ ምን እናስባለን? በሚሉትና ሌሎችም ወሳኝ የውይይት ነጥቦች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።

ይህ ውይይት በዩኒቨርሲቲያችን ህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት እና በሊቀ ማርቆስ የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ በጋራ ትብብር የተዘጋጀ ልዩ የምክክርና የውይይት መርሃ ግብር ሲሆን በውይይቱ ላይም ሞላልኝ ታምሩ (ዶ/ር ) የአስተዳደርና ተማሪዎች ጉዳይ ምክትል ፕሬዚደንት ፣ እሱባለው መኩ (ዶ/ር ) የፕሬዚደንት ጽ/ቤት ኃላፊ ፣ ድርቧ ደበበ (ዶ/ር ) የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር ፣ መልካሙ በዛብህ (ዶ/ር ) የምርምርና ቴክኖሎጅ ሽግግር ዳይሬክተር ፣ አበበ በላይ (ዶ/ር ) የፕሮጀክት ቀረፃና ትብብር ዳይሬክተር ፣ ደምሳቸው ሽታሁን (ረ/ፕ ) የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክተር እና እንዲሁም የተለያዩ የስራ ክፍል ኃላፊዎች፣ መምህራንና ባለሙያዎች በውይይቱ ተሳታፊ ሆነዋል።

ይህ ልዩ ዝግጅት ሰኞ ምሽት ከ2:30 - 3:00 ባለው ጊዜ ውስጥ በአሚኮ ቴሌቪዥን የሊቀ ማርቆስ የቴሌቪሽን ፕሮግራም የሚቀርብ በመሆኑ መሉ ዝግጀቱን እንድትከታተሉ በአክብሮት እናሳሰባለን።

"የእውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ"

ከታች ያስቀመጥናቸው የዩኒቨርሲቲያችን ትክክለኛ የማህበራዊ ትስስር አድራሻዎቻችን ናቸው። ተራ በተራ ሊንኮቹን እየተጫናችሁ ትወዳጁን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን



ዩቲዩብ https://www.youtube.com/channel/UCqQDHEyYDen3aybySpYsF_Q

ዌብሳይት: www.dmu.edu.et

ቴሌግራም https://t.me/Debre_Markos_University

ፌስቡክ https://www.facebook.com/dmu.edu

ቲዊተር https://twitter.com/dmu_ethiopia

እንስታግራም https://www.instagram.com/dmu_ethiopia/

ሊንክድኢን https://www.linkedin.com/in/dmu-ethiopia/