Get Mystery Box with random crypto!

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከመስከረም 30 ቀን 2015 ጀምሮ እንደሚሰጥ ተገለጸ የ2014 የት | Deborah School

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከመስከረም 30 ቀን 2015 ጀምሮ እንደሚሰጥ ተገለጸ

የ2014 የትምህርት ዘመን ብሔራዊ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ማጠቃለያ ፈተና ከመስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ፡፡

ፈተናው ከመስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚሰጥ የአገልግሎቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከዚህ ቀደም እንደገለጹት÷ የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና በኦንላይን መስጠት እስከሚጀመር ድረስ በዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጥ ይሆናል።

የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርሲቲ እንዲሰጥ የተወሰነው÷ የፈተና ሰርቆትና ማጭበርበርን ለማስቀረት ታስቦ መሆኑን መናገራቸው ይታወሳል፡፡