Get Mystery Box with random crypto!

ዲያቆን ሞገስ አብረሃም|moges abreham

የቴሌግራም ቻናል አርማ deaconmoges17 — ዲያቆን ሞገስ አብረሃም|moges abreham
የቴሌግራም ቻናል አርማ deaconmoges17 — ዲያቆን ሞገስ አብረሃም|moges abreham
የሰርጥ አድራሻ: @deaconmoges17
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 472
የሰርጥ መግለጫ

እግዚአብሔር ቢፈቅድ ይህ ቻናል በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች ላይ እና በተለያዩ ጊዝያቶች ያዘጋጀዋቸውን ኦርቶዶክሳዊ መጣጦፎች ጽሑፎች እና የመጻሕፍት ዳሰሳዎች መማርያ ይሆኑ ዘንድ የማጋራበት ይሆናል።
https://t.me/Mogesabreham
https://t.me/joinchat/AAAAAEczV7heeRJD86ok2g

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-07 09:45:48
89 viewsMoges abreham, 06:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 20:32:08 ++ጥጦስን ባሰብኩት ጊዜ++

ጥጦስን ሚመስለው ማን ነው? ከጌታ በስተቀኝ የተሰቀለው ወንበዴው ጥጦስ እንዴት ያለ ድንቅ ሰው ነው። ጥጦስ እኮ ወንበዴ ነበር በየዱሩ ተመሽጎ የሚኖር ሽፍታ ነበር ። መጸሕፍትን እንደሚያውቁ እንደፈሪሳውያን አልነበረም። በቤተመቅድስ እንደሚኖሩ ካህናትም እግዚአብሔርን የሚያገለግል አልነበረም። ኦሪትንም ተምረው ከክበሩ ሰዎች ወገንም አልነበረም። እርሱ በአጭሩ ወንበዴ ነበር። ነገር ግን እንዴት ያለውን ድንቅ ቃል ተናገር? እግዚአብሔርን እናመልካለን የሚሉት በመስቀል ላይ ጌታቸውን ሲያኖሩ ከቁጥር እንኳን ማይታወሰው ጥጦስ ለጌታው አዘን፤ሌሎች ሲዘባበቱበት እርሱ ግን ለጌታ መሰከረለት። ያልታደለው በግራ የተሰቀለው ወንበዴ ዳክረስ ሲሳለቅበት "እኛስ በበደላችን ነው እርሱ ግን ያለበደሉ ነው" በማለት ለጌታ ንጹህነት መሰከረ። ጌታን ሲከተሉት የኖሩት ያለመሰከሩትን እርሱ ግን በዛ ጭንቅ ሰዓት መሰከረ። ከሁሉ ግን ሚደንቀው በጊዜው አይሁድ ያቃሉ የተባሉት መናገር ያቃታቸውን ቃል እጅግ በትሁት አንደበት እንዲህ ብሎ ተናገረው "ጌታ ሆይ በመንግስትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ" አለ ቅዱስ ያሬድም ይሄንን የጥጦስን ቃል እያደነቀ ጥጦስ ሆይ ይሄን ማን አስተማረህ ይለዋል። ጌታ ለዚህ በጎ እምነቱ እና ሥራው "ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር ትሆናለህ ብሎ ከአዳም እና ከተመረጡ ሰዎች ቀድሞ ገነት እንዲገባ አደረገው። ተመልከቱ ለሰው ደረጃ ምናወጣው እኛ ነን እንጂ እሱስ ሽፍታና ወንበዴዎችንም ይቅር ለማለት የታመነ ነው። በሰዎች ዘንድ የተጠሉ በእግዚአብሔር ዘንድ እጅግ የሚወደዱ ልጆቹ ናቸው እስከ ሞት ድረስ ይጠብቃቸዋል።

ጥጦስ ሆይ በጭንቀት እና በመስቀል ላይ ሆነህ ፈጣሪህን ያመሰገንክበትን ጥንካሬ ለእኔ ይሰጠኝ ዘንድ ለምንልኝ።

ዲ/ን ሞገስ አብረሃም
126 viewsMoges abreham, edited  17:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 23:24:20 Watch "የጌታችን ፈውስ ጠባያት / የጌታችን ፈውስ/ ገጸ ንባብ ክፍል ሁለት" on YouTube


በዲ/ን ሞገስ አብረሃም
182 viewsMoges abreham, edited  20:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-27 16:23:41 እናስተውል

ዓለም ምን ያህል እንደወደቀች ተመልከቱ። ብልጭልጯ ዓለም ምን ያህል እንደረከሰች አስተውሉ። ይህች ለሰው ጊዝያዊ መኖርያ ሆና የተሰጠችው ምድር ሰይጣን በሚፈልገው መልክ እንዴት እንደ ሰራት ተመልከቱ? ዓለም በጨለማው ገዢ እጅ መውደቋን ከምናየው በላይ ምን ዓይነት ምስክርነት ማቅረብ ይቻለናል። መጸሐፍ ቅዱስን ተመልክተህ ከሆነ አንድ አንድ የዓለምን እውነታዎችን መረዳት ትችላለህ። በኖኅ ዘመን የነበሩ ሰዎች የፈላው ውኃ አንገታቸው ላይ እስኪደርስ ድረስ እግዚአብሔርን ሲገዳደሩ ተመልክተናል እጅግ የተዋበችና ያመረች ሰዶም በተባለች ሃገር ይኖሩ የነበሩ ሰዎች በተመሳሳይ ጾታ ሲገናኙ እግዚአብሔር በዲን እሳት እንዲጠፋቸው አንብበናል። የባቢሎን ሰዎች እግዚአብሔርን ወጋነው ብለው ክፉ ቃል ሲያወጡ ሰምተናል የእግዚአብሔር ልጆች ከሰው ልጆች ጋር ከተዋህዶ በኋላ ምን ያህል ለምድር የከበዱ ፍጡራን እንደተወለዱ አይተናል። ተመልከቱ እነዚህ ከብዙ ሺ አመታት በፊት የነበሩ ሰይጣን የተጠቀመባቸው ትውልዶች ናቸው። አሁን እነዚህን የሚያስንቅ ትውልድ አለ። በፊልሞቻቸው በዘፈናቸው ሰይጣናዊ ተከታዮችን ለመውለድ ጥረት የሚያደረጉ ኅብረቶች ተፈጥረዋል። እነዚህ ኅብረቶች በማወቅም ባለማወቅም ካለባበሳችን አንስቶ ሰይጣንን ወደማምለክ ዝንባሌ እያደረሱን ነው። ዓለም ከየትኛውም ጊዜ በላይ ሰልጥናለች ይህ ስልጣኔ ግን ለሰይጣን አምልኮ እንዲመቹ ተደረገው ተሰርተዋል። እጅግም ተጨንቃለች ከሕመም ይልቅ በሰው ሰራሽ ምክንያት በየቦታው ደሙ የሚፈሰው ለሰይጣን መስዋዕት ሆኖ ይቀርባል። ተወዳጆች ሆይ ከየትኛውም ጊዜ በላይ እምነታችን ሚፈተንበት ጊዜ አሁን ያለንበት ወቅት ነው። ከኖኅ ዘመን ከሰዶም እና ከባቢልን ሰዎች ታሪክ እንማር። እጅግ የሚያስጨንቅ ወሬ የሰማን እንደሆነ አብዝተን እንጸልይ። ይህች አሁን ያለችው የዓለም መሪዎች ሰይጣናዊ ጥንስስ በየቤታችን መድረሱ የማይቅረ ነውና። ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ግንኙነት እናጠንከር። ለአንድ ቀንም ቢሆን ከቤቱ አንለይ። አሁን በፊት የምንወድቅበት ዘመን ነው።

ዲ/ን ሞገስ አብረሃም
246 viewsMoges abreham, 13:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 21:46:24 ይህ ትውልድ ከሰዶም ሰዎች በምን ተሻለ? ይህ ትውልድ የእግዚብሔርን ከተደፋፈሩ ከባቢሎን ሰዎች በምን ተሻለ? ይህ ትውልድ ፈጣሪያቸውን ዘንግተው ጥጃ ካመለኩ ሙሴ በነበረበት ዘመን ከነበሩ ከእስራኤላውያን በምን ተሻለ? ይህ ትውልድ ከልበ ደንዳናው ፈርኦን በምን ተሻለ ? ይህ ትውልድ ናቡቴን ካሰቃየችው ከኤልዛቤል በምን ተሻለ? ይህ ትውልድ የገዛ ወንድሙን ከገደል ከቃዬል በምን ተሻለ? ይህ ትውልድ በራሳቸው ከሚመጻደቁ ከፈሪሳውያን በምን ተሻለ? እነዚህ ሁሉ ቅጣትን ያገኙ ነበር የሁሉንም በደል ጠቅልሎ የሚፈጽመው ይህ ትውልድ ፍዳው ምን ይሆን?።
196 viewsMoges abreham, 18:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-17 23:34:23 ++ከሳሾችህ..+++

ክርስቶስ የሰራቸውን መልካም ሥራዎች ማየት የተሳነው ዓይን እንዴት ያለ ዓይን ነው? ክርስቶስ የተናገረውን ለእኩይ ዓላማ የሚሰማ ጆሮ እንዴት ያለ ጆሮ ነው። አይሁድ ክርስቶስ ሚናገረውን ይከታተሉ የሚሠራውን ያዩ ነበር። ነገር ግን ምክንያት ፈልገው ሊያካስሱት እንጂ ወደውት አለመሆኑ ግልጽ ነው። ተመልከቱ አንድ አንድ ጊዜ ምን እንደምንል መስማት የሚሹ የምንሠራውን ሁሉ ሚከታተሉ ሰዎች በተጠንቀቅ ይቆማሉ። ይህን የሚያደርጉት ግን ቅኖች ብቻ አይደሉም። ለነቀፉ የሚሰሙ ለትችት የሚመለከቱ ስንት አይሁዶች ዙርያችን ከትመዋል። ክርስቶስ በሰንበት ሲፈውስ በፈውሱ ከመደነቅ ይልቅ ሰንበትን ሻረ ብለው ተናገሩት።አይሁድ ጌታችን ከሚሠራው መልካም ሥራ ሳይቀር ክስ የማውጣት ልምድ አላቸው። ክርስቶስ ከእነርሱ በፊትም በኋላም ያልታየ ታላቅ ሥራ አሳይቷቸው እንኳን ከማመን ይልቅ ጥቃቅን ስህተቶችን ሲለቅሙ ንሩ። በየሔዱበት ለወጪ ወራጁ ሁላ ነቀፌታቸውን ይናገራሉ። እነዚህ አይሁዶች ከእነርሱ በላይ አዋቂ እንዲመጣባቸው አልወደዱም። ብዙውች የሚከተሉት አካል ማየትን አልወደዱም። ጌታችን ለእኛ አብነት ነው። ከመልካም ሥራህ ላይ እንኳን ትርጉም እየሰጡ የሚነቅፉህ አይሁዶች ከጎንህ አይጠፉም። እንደ አይሁድ ከበው ስህተትህንና ድክመትህን እየለዩ የሚጽፉ ብዙ ናቸው። ከሁሉ ሚደንቀን ግን በክርስቶስ ይህን ያደረጉት በጊዜው ያሉ ካህናት የእግዚአብሔር ሰዎች ነን የሚሉ መሆናቸው ነው። መንፈሳዊ ቦታ ከሚኖር ሰው የሚገኝ ነቀፌታ እንዴት የከፉ ነው? የተበላሸውን አቅንቶ ማየት አለመቻል ምን አይነት ክርስትና ነው? ክርስቶስ ግን ከሚጠሉት ይልቅ በሚወዱት ሰዎች ተስቦ ነበር። ከሚከሱት ይልቅ ጆሮ ለሰጡት ያስብ ነበር። የእግዚአብሔር ሰዎች ነን ብለው ከሚኮፈሱትና ከሚነቅፉት ይልቅ ቤቱ የጋበዙት ቀራጮችን መርጧል። ከማይጠቅሙ ሞጋቹች ይልቅ ርዳታህን ለሚሹ ሰዎች ከፊት ይልቅ ትጋ። አይሁድ ካሉበት መሥመር ቀና ሳይሉ በትችት እና በክፋት እንደቀሩ ክርስቶስ ግን ተሰቅሎ ሞቱ ተነሥቶ ፍጹም ድኅነት ሰጠ። ነጥቡ እዚህ ጋር ነው ምትሰራውንና ዓላማህን ከተረዳህ የአይሁድ ጫጫታ አያዘናጋህም እነሱ እየጮሁ ባሉበት እንደቆሞ አንተ ከላይ በክብር ትቀመጣለሀ።

ዲ/ን ምገስ አብረሃም
272 viewsMoges abreham, edited  20:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 23:28:21 የጌታችን ፈውስ በተሰኘው የዲ/ን ተመስገን ግርማይ መጸሐፍን መነሻ በማድረግ ስለ ተዓምርና ስለ ደዌ ምንነት ከተዋሕዶ ሚድያ ጋር ያደረኩት ቆይታ።ክፍል 1



305 viewsMoges abreham, edited  20:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 10:10:22
የድኅነታችን መጀመርያ
283 viewsMoges abreham, 07:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-05 21:51:22 Watch "0091 ብስራተ-ገብርኤል-ዲን-ሞገስ-አብርሃም Or annunciation-of-st-Gabriel" on YouTube


294 viewsMoges abreham, 18:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-31 23:13:17 ++እግዚአብሔር ሳቅ አድርጎልኛል+++
{የሳቅ ቅድመ ነገሮች በአሥራው መጻሕፍት}

(ሳቅ ጥርጣሬህ የሚገለጸበት አንዱ መንገድ ነው......)

በእርጅና ምክንያት ከመውለድ የተገታች ሣራ በእግዚአብሔር ቃል መሳቋን እናስታውሳለን። ነገሩ እንዲህ ነው ከድንኳኑ ደጅ ከአብርሃም ኋላ ቆማ ሳለች እግዚአብሔር እንደ ዛሬ ተመልሼ በረድኤት ወደ አንተ በመጣሁ ጊዜ ሳራ ወንድ ልጅን ትወልዳለች ሲል ሰምታ "ሲያረጁ አምባር ይዋጁ" እንዲሉ እስከዛሬ ድረስ ገና ቆንጆ ነኝን ጌታዬም አርጅቷል ብላ በመጠራጠሯ ብቻዋን ሳቀች። ሳቅ የጥርጣሬ ምልክት መሆኑን በሣራ ታሪክ ውስጥ እንመለከታለን። ጥርጣሬ የሚወልዳቸው እምነት ከመጉደል የሚመጡ ሳቆች አሉ። ካለመኖር ወደመኖር ያመጣ እግዚአብሔርን ተጠራጥሮ መሳቅ ደግሞ ይበልጥ የከፉ ነው። ሳቅህ ጥርጣሬ የወለደው እንይሆን ተጠንቀቅ። ቃል ኪዳን ለተገባለት ለአብረሃም ሚስቱ የምትሆን ሣራ ይህ ሳቋ አስወቅሷታል። ሳራ ለብቻዋ የሳቀችውን ሳቅ እግዚአብሔር በጥበቡ በግልጥ ተመለከተ። ሰውን ተደብቆ ሰው ላይ መሳቅ ይቻል ይሆናል ሰውን ተደብቆ መሸሽ ይቻል ይሆናል ገደል ጠፈር ጣራ ግድግዳ የማይገድበው የእግዚአብሔር ሥራ ላይ ተደብቆ መሳቅና መሸሽ ግን አይቻልም። እግዚአብሔርም አብረሃምን ሳራ ብቻዋን ለምን ተጠራጠረች በውኑ እግዚአብሔር ክረጁ በኋላ እንዲወልዱ ማድረግ እግዚአብሔር ይሳነዋልን። ብሎ ሣራ ለሳቀችበት ጉዳይ መልስ ሰጣት። በተያያዥ መንገድ አለማመንን ተከትሎ የሚመጣ ፌዝ መገለጫ ሳቅ ሊሆን ይችላል። ሳቅህ ጥርጣሬህን ገልጦ እንዳያስወቅስህ ለሚመለከትህ ሰው ደግሞ እያፌዝክበት መሆኑን አስቦ እንዳያዝንብህ ተጠንቀቅ።


(ሳቅ ነቀፌታህና ንቀትህ ሚገለጥበት መንገድ ነው.....)

ቅዱስ ዳዊት “በሰማይ የሚኖር እርሱ ይሥቃል፥ ጌታም ይሣለቅባቸዋል።” ይለናል። እግዚአብሔር ይሥቃል? ክብር ይግባውና እርሱ በሰዎች አንጻር እንደምናየው አይነት ሳቅ የሚስቅ አይደለም። ነገር ግን ሳቅ መንቀፍን መናቅን ማቃለልን ይወክላል በሥራቸው ይስቃል ይሳለቅባቸዋል ስንል ሥራቸውን ተመልክቶ ይነቅፉቸዋል ይንቃቸዋል ማለቱ እንደሆነ ልብ በሉ። ስለዚህ በእግዚአብሔር አንጻር ስንመለከተው ተገቢ ሳቅ ነው። በሌላ አገላለጽ በሰዎች ሥራ ማዘንን በራሱ በአግርሞት ሳቅ ሊገለጽ መቻሉ ርግጥ ነው። እግዚአብሔር በሥራችን ቢነቅፈን አምላክነቱ ጌትነቱ ነው። ማንም የቆመ ቢመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ እንዳለው ግን መቆማችን ሳናውቅ በወደቁት የምንስቅ ከሆነ በደል ይሆንብናል። ስለዚህ ሳቅ መናቅን መንቀፍን የሚገልጽ እንቅስቃሴ ነው።

(ሳቅህ እግዚአብሔር በሚሰጥህ ነገር ስትደሰት የምትገልጥበት መንገድ ነው .......)

አስቀድማ ተጠራጥራ የሳቀችው ሣራ “እግዚአብሔር ሳቅ አድርጎልኛል፤ ይህንንም የሚሰማ ሁሉ በእኔ ምክንያት ይስቃል።" ሳራ ካረጀች ሙቀት ልመላሜ ከተለያት በኋላ በመወለዷ መደሰቷን ሳቅ አደረጎልኛል ብላ ተናገረች። ይህንን የመወለዷን ነገር የሰሙ ዘመዶቿ ሁሉ ስለ እርሷ እንደተደሰቱ ለመግለጽ ደግሞ ሰው ሁሉ በእኔ ምክንያት ይስቃል አለች። በስተርጅና የወለዱትን ልጅ ስሙን "ይስሐቅ" አሉት ይህም "ትፍስሕት" ደስታ ማለት ነው ቀድማ ትወልጂያለሽ ሲላት ተጠራጥራ የሳቀችው ሳራ ዳግመኛ አምና በወለደችው ልጅ የደስታ ሳቅ ሳቀች። በሷ ሳቅም ያያት ሁሉ ሳቅ። ተመልከቱ ደስታ ፊትን ያበራል በእኛ የደስታ ሳቅ ውስጥ ደስ ምናሰኛቸው ሰዎች አሉ። በጥቅሉ ሳቅ የሆናትን ልጅ እግዚአብሔር ሰጣት። እግዚአብሔር ባደረገልን ነገር ስንስቅ ደስታችን እንገልጻለን።

(ቢሆንም ግን ከሳቅ ለቀሶ ከደስታ ሀዘን ሳይሻል አይቀርም........)

ያዕቆብ "ወላሕዉ ወብክዮ" እዘኑ አልቅሱ ይላል። ሳቃችሁን ወደ ለቅሶ ደስታችሁንም ወደ ኃዘን መልሱት ማለት ነው። ተድላ ደስታን ትቶ ማልቀስ አንዱ የጽድቅ መንገድ ነው። በተለይ የጥበብ መጻሕፍት በተደጋጋሚ ያነሳሱታል። ጠቢቡ ሰሎሞን ይህን እንዲህ ብሎ ገልጾታል "ወደ ግብዣ ቤት ከመሄድ ወደ ልቅሶ ቤት መሄድ ይሻላል፤ እርሱ የሰው ሁሉ ፍጻሜ ነውና፥ ሕያውም የሆነ በልቡ ያኖረዋልና።ከሳቅ ኀዘን ይሻላል፥ ከፊት ኀዘን የተነሣ ልብ ደስ ይሰኛልና። የጠቢባን ልብ በልቅሶ ቤት ነው፤ የሰነፎች ልብ ግን በደስታ ቤት ነው።" ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ሀዘን ቀድሞ ሲመጣ በፍጻሜው ሳቅ እንደሚሆን ይነግረናል "ብፁዓን እለ ትበክዩ ይእዜ እስመ ትስሕቁ።" ዛሬ የምታለቅሱ የተመሰገናችሁ ናችሁ ትስቃላችሁ ደስ ይላቹሀል። ይለናል። ሀዘን ይዞት የሚመጣ ሳቅ አለ ይህ ፍጹም ደስታ ያለበት ሳቅ ነው።

"በወንድሙ መሳቅ ለሚወድ ሰው ወዳጅ አትሁን" ማር ይስሐቅ

ዲ/ን ሞገስ አብረሃም
23/10/2014
328 viewsMoges abreham, edited  20:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ