Get Mystery Box with random crypto!

የሺበላይ በላቸው (ዲ.ን) ዘኢትዮጵያ Deacon yeshibelay Belachew ze Ethiopia official

የቴሌግራም ቻናል አርማ deacon1221 — የሺበላይ በላቸው (ዲ.ን) ዘኢትዮጵያ Deacon yeshibelay Belachew ze Ethiopia official
የቴሌግራም ቻናል አርማ deacon1221 — የሺበላይ በላቸው (ዲ.ን) ዘኢትዮጵያ Deacon yeshibelay Belachew ze Ethiopia official
የሰርጥ አድራሻ: @deacon1221
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 907

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-04-25 02:38:53 የቀድሞው ሳጥናኤል የአሁኑ ሰይጣን ከሰማይ ከብሩ ዙፋን ወደ ጥልቁ የቅጣት ቦታ በርባኖስ ተጥሎ ሲወርድ ሥላሴ ፈርተውኝ ሸሹ። ብሎ ነበር ገና ከእንደዚህ አይነት የእቡይ አስተሳሰብ ያልወጣ ብዙ ወለፈንዲ ሰው አለ።
132 views23:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 22:27:49
"ኁለት ነገሮች ብልህና አዋቂ ያደርጉናል። የምናነባቸው መጽሐፎችና በሕይወት መንገድ ላይ የሚገጥሙን ሰዎች።"
166 views19:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 09:29:41
ውሻና አስመሳይ ሰው!

ውሻ ጭራውን የሚቆላው በእጅህ ላይ ያለውን ዳቦ እስኪያገኝ እንጂ ስላንተ ገዶት አይደለም። አስመሳይ ሰውም ልክ እንደ ውሻ ነው። ካንተ የሚፈልገውን እስኪያገኝ በጓደኝነት ቀርቦ ጥርሱን ያሳይሀል፤ እንደድመት ይተሻሽሀል፤ የልቡን ክፋትና ተንኮል ደብቆ ጭራውን እየቆላ ይቀርብሀል፤ ከዚያም ምቹ ግዜ ጠብቆ ያለህን ሁሉ ሊነጥቅህ፣ መልካምነትህን ሊያጠለሽ፣ በጎነትህን ሊያጠፋ፣ ከጠላት ዲያቢሎስ ጋር ተሰልፎ ጉድጓድ ይምስልሀል።

መውጫ
አንተ አስመሳይ ሰው ሆይ ጉድጓዱን አታርቀው ምናልባት ያንተ መቀበሪያ ሊሆን ይችላልና አፈሩ እንዲቀልልህ።

ዲን የሺበላይ በላቸው
15/08/2015 ዓም
177 viewsedited  06:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 17:40:55 _
፷፩) ጥምቀት የተነሣ ልጅ ያላቸው አባትና እናት በፊት ሁለት ቀን በኋላ ሁለት ቀን ከመገናኘት (ሩካቤ) መከልከል ይገባቸዋል።
_
፷፪) ሩካቤ የሚከለከልባቸው ጊዜያት
√ ሴት በወር አበባዋና በአራስነቷ ጊዜ
√ በጾም ወቅት፣ በሰሙነ ሕማማት
፷፫) በጾም ሩካቤ መከልከሉ ስለጾም የሚሆን ፈቃደ ነፍስ ይፈጸም ዘንድ ነው። ከሰሙነ ሕማማት ውጭ ባሉ አጽዋማት በፍትወት ጾር ድል የተነሣ ሰው ቢኖር የፈቲውን ጾር ማራቅ ይገባዋል። [ሩካቤ ይፈቀዳል። ይህ ግን ላልተቻለው ነው እንጂ ለተቻለውስ ሁሉንም አጽዋማት መታቀብ መልካም ነው]።
_
፷፬) ከሴት ማኅፀን አውጥቶ ከውጭ ዘርዕን መዝራት አይገባም።
_
፷፭) ላለመፀነስ ወይንም የተፀነሰውን ለማስወረድ መድኃኒት መጠቀም አይገባም።
_
፷፮) ሚስቱ እንደሰሰነች የነገሩት ሰው ቢኖርና ድርስ ነገሩን ባያውቅ፣ ድርስ ነገሩን ሊያውቅ ቢወድ ወደ ቤተክርስቲያን ዳኛ ወደ ኤጲስ ቆጶሱ ይውሰዳት። ከታቦቱ ፊት ያቁማት። ካህኑ መንቀል አንስቶ ይያዝ። ከርቤ ይጨምርበት። ከሐመደ ምሥዋዑ ከውሃው ይጨምሩበት። ከዚያ ይህንን በእጁ ይዞ። ክንብንብሽን አውርጂ ይበላት። በእግዚአብሔር ያምላት። ሌላ ሰው አልደረሰብኝም ብትል ባልሽ ከጠረጠረው ነገር የነጻሽ ከሆነ ይህን ውሃ ጠጪ ይበላት። በሐሰት ብትምዪ ግን ይህ የምትጠጪው ውሃ ሥጋሽን ያሳብጠው ይበላት። ሴትዮዋም አሜን አሜን ወአሜን ትበል። በታቦቱ ፊት ሆና ውሃውን ትጠጣ። ንጹሕ ከሆነች ደስ የምትሰኝበትን ልጅ ትወልዳለች።
_
፷፯) ማግባት ርኵስ ነው ብሎ ከጋብቻ የተከለከለ ሰው ኃጥዕ ነውና ከቤተክርስቲያን ይለይ።
_
፷፰) ሴት ልጅ በወር አበባዋ ጊዜ ወደ ቤተክርስቲያን አትግባ። የደሟ ወራት እስኪፈጸም ድረስም አትቁረብ።
_
፷፱) ወንድ የወለደች ሴትም ከወለደች ጀምሮ 40 ቀን ከቤተክርስቲያን ውጭ ትቆይ። ሴት ከወለደች 80 ቀን ትቆይ።
_
፸) [ቁጥር ፱፻፴፮] አዋላጆች ወንድ ካዋለዱ 20 ቀን፣ ሴት ካዋለዱ 40 ቀን እስኪሆናቸው ድረስ ሥጋውን ደሙን አይቀበሉ።
_
፸፩) ባል ያላት ሴት ብትሰስንና ባሏ ባያውቅ ለብቻዋ ንስሓ መቀበል ይገባታል። ባሏ እያወቀ ሊፈታት ባይወድ ግን ሁለቱም ከምእመናን ይለዩ።
_
፸፪) የቄስ ሚስት ባሏ ከሞተ በኋላ ሌላ ብታገባ ንስሓ ይገባታል። በታች መቆም በኋላ መቀበል ይገባታል።
_
፸፫) ጋብቻ በሚከተሉት ነገሮች ይፈርሳል።
√ ባልና ሚስት ተመካክረው ከመነኮሱ
√ አንዱ የአንዱን ፈቃድ አልፈጽምም ቢል
√ አንዱ የአንዱን ሰውነት ሊያጠፋ ቢወድ
√ ባል ከሚስቱ ጋር መገናኘት (ሩካቤ) ካልቻለ
√ ሚስት ከባል ጋር መገናኘት ካልቻለች
(አፈ ማኅፀኗ ጠባብ ሆኖ ለሩካቤ ቢከለክል)
፸፭) ባል ሚስቱን ጋኔን ሲጥላት ቢያገኛት፣ ይህ ሁኔታ ካገባት በኋላ ያገኛት ከሆነ እርሱ መርዳት መታገሥ ይገባዋል። እርሱንም እንዲህ ያለ ነገር ቢያገኘው እርሷ መርዳት መታገሥ ይገባታል። ከማግባቷ በፊትም እያመማት ሳለ ደብቀው ቢያጋቡትና ቆይቶ ቢያውቅ መፍታት ይችላል።
_
፸፮) ከተጋቡ በኋላ ከሁለቱ አንዱን ደዌ ሥጋ ቢይዘው አንዱ ከአንዱ ሊለይ ቢወድ መለያየት አይገባውም። ሊፈታት ቢወድ ግን ትልወቷን ማጫዋን ሁሉ መስጠት ይገባዋል።
_
፸፯) ሰው በእሥራት ሳለ ወይም ባልታወቀ ምክንያት ቢጠፋ ግቢው ይፍረስ አንልም። መፈታትና አለመፈታቱ እስኪታወቅ ድረስ ባልና ሚስት ሆነው ይኑሩ እንጂ።ከአምስት ዓመት በኋላ ግን እንደ ፈቃዳቸው ይሆናል።
_
፸፰) ባል ዘማች ቢሆን እስከ ሁለት ዓመት ሚስቱ ትጠብቀው። ሚስት ስለ ባሏ ህልውና ምንም ዓይነት ዜና ካልሰማች፣ መሞቱንም ከመኳንንት ካልሰማች አታግባ። ሌሎች ሰዎች ሞቷል ብለው ቢናገሩ ለምስክርነት በመካከላቸው ወንጌል ያኑሩና ያምሏቸው። ድርስ ነገሩ ከታወቀ ከዚህ በኋላ ዳዊት እያስደገመች ቁርባን እያስቆረበች አንድ ዓመት ትጠብቅ። ከዚያ በኋላ ማግባት ትችላለች። ምስክሮች በሐሰት ሞቷል ብለው ቢመሰክሩ አሥር ወቄት ወርቅ ይክፈሉ። ሞተ ብለው ያወሩበት ወታደርም ከወደደ ሚስቱን መልሶ ወደ ቤቱ ያግባት።
_
፸፱) ባሏ ሳይፈቅድላት ከሌላ ወንድ ጋር ብትጠጣ፣ ወደ መሸታ ቤት ገብታ ብትስቅ ብትጫወት፣ ከቤቷ ወጥታ ከውጭ ከባዕድ ቤት ብታድር ይፍታት።
_
፹) ሚስት ባሏን ለመግደል ብትሞክር ወይም ሌለች ሊገድሉት እንደሆነ እያወቀች ዝም ካለችው ጋብቻቸው ይፈርሳል።
_
፹፩) ሚስት ያገባ ሰው በእርሱና በሚስቱ መካከል ክፉ ነገር ቢገኝ፣ ከምክንያት ወገን ማናቸውም ምክንያት ቢኖርበት ይታገሣት። ከክፋት ወደ በጎነት እስክትመለስ ድረስ ይምከራት ያስመክራት። መክሯት አስማክሯት ባትመለስ ወደ ደግ ቄስ ይውሰዳት። ቄሱም በመካከላቸው ሆኖ ያስታርቃቸው። ቄሱን አይሆንም ብትለው ኤጲስ ቆጶሱ አብረሽ ኑሪ ብሎ ይፍረድባት። ለኤጲስ ቆጶሱም ባትታዘዝ ባሏን ጥላ ብትሄድ ሁለተኛ አባብሎ ይመልሳት። በእምቢተኝነቷ ከጸናች ባሏ የወደደውን ማድረግ ይገባዋል። ሌላ ሊያገባ ቢወድ ያግባ። በንጽሕና መኖር ከፈለገ ይመንኩስ። እርሱ ገፊዋ ጠላቷ እንደሆነ ከታወቀና የቤት ቀጋ የሜዳ አልጋ ቢሆንባት ቃሉን አይቀበሉት። ግድ አብረህ ኑር ብለው ይፍረዱበት።
_
፹፪) ባል ከሚስቱ ሌላ ሴት ጋር ሲዘሙት ቢገኝ (ሴትም ከባሏ ሌላ ወንድ ጋር ስትዘሙት ብትገኝ) ዝሙቱን ባይተው ጋብቻው ይፈርሳል። ባልና ሚስት የሆኑ ዘማውያንን አያፋቷቸው። ካህናት ቀኖና ሰጥተው ያስታርቋቸው እንጂ።

አንቀጽ ፳፭
ይህ አንቀጽ እቁባት ማኖር እንደማይገባ ይናገራል።
፩) በኦሪት ነበር እንጂ በወንጌልስ እቁባት ማኖር አይገባም [የተከለከለ ነው]። ዕቁባት ማኖር ዝሙት ነው።
_
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
ክፍል ፲፱ ይቀጥላል
መ/ር በትረማርያም አበባው
231 views14:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 17:40:55 _
፳፭) እብድ ማግባት አይገባውም።
_
፳፮) አካላትን የሚቆራርጥ ደዌ ሥጋ ያለባቸው ሰዎች ማግባት አይገባቸውም።
_
፳፯) ስትሰስን ተገኝታ የተፈታችውን ሴት ንስሓ መግባቷ እስኪታወቅ ድረስ፣ ጎረቤቶቿ መመለሷን እስኪመሰክሩላት ድረስ። ከተመሰከረለት በኋላ ፍትሐት ዘወልድ ተደግሞላት ታግባ።
_
፳፰) ሚስት ባሏ ከሞተ ከ፲ ወር በፊት ሌላ ማግባት አይገባትም። በዚህ በ፲ ወር ውስጥ መተጫጨት ግን ይቻላል።
_
፳፱) ከሐፃኒ ከመጋቢ በታች ያለ ሕፃን ሐፃኒ መጋቢ ሳይፈቅድለት ማጨት አይገባውም። በባልና በሚስት ፈቃድ ነው እንጂ ያለሁለቱ ፈቃድ ጋብቻ አይጸናም አይፈጸምም።
_
፴) አካለ መጠን ያልደረሰችን ሴት ማግባት አይገባም። ከመተጫጨት ግን አይከለክልም።
_
፴፩) ያጨ ሙሽራ ማጫ ከሰጠ በኋላ ሊመነኩስ ቢወድ ለሙሽራይቱ የሰጠውን ማጫ መቀበል ይገባዋል።
_
፴፪) ለማግባት አስቀድሞ መተጫጨትና ቃል መጋባት በፍጹም ምክር በፍጹም ፈቃድ ይፈጸም ዘንድ ነው። መልኩን ግብሩን ጸባዩን አጥንቱን ለመመርመር ነው። ለሠርግ የሚያስፈልገውን ለማዘጋጀት ነው።
_
፴፫) ባልና ሚስት እርሱም ሌላይቱን እርሷም ሌላውን ሳያውቁ የተጋቡ እንደሆነ ፍቅር ይጸናል።
_
፴፬) መነኵሴን ማግባት አይገባም። ከስልሳ ዓመት በላይ የሆናትን ሴት ማግባትም አይገባም።
_
፴፭) ማጨት ቃል ኪዳን መጋባት ነው። ከጋብቻ አስቀድሞ የሚሆን አለኝታ ነው። በደብዳቤም ያለ ደብዳቤም ይሆናል። በእጮኝነት ጊዜ ካህናት እጅ ለእጅ አያይዘው፣ አንድ የሚያደርጋቸውን መስቀል አስጨብጠው፣ አንድ ቀለበት አድርገው በደብዳቤ ይወስኑላቸው።
_
፴፮) ያለ ትልወት፣ ያለ ማጫ ማግባትም ይገባል [ይቻላል]።
_
፴፯) ሰባት ዓመት ላልሞላው ሕፃን ማጨት አይገባም።
_
፴፰) አጭቶ ለማግባት ቀን ያልወሰነ ሰው በሀገር ያለ ቢሆን ሁለት ዓመት ይጠብቁት። ሩቅ ሀገር የሄደ ቢሆን ሦስት ዓመት መጠበቅ ይገባል። በታወቀ ምክንያት የቀረ ቢሆን አራት ዓመት መጠበቅ ይገባል። ከዚህ ያለፈ ቢሆን ግን ለሌላ ማጋባት ይገባል።
_
፴፱) በፈቃዷ የምትኖር ሴት የፈለገችውን መርጣ ማግባት ትችላለች። በእናት በአባቷ ቤት ያለች ከሆነች ግን በቤተሰቦቿ ፈቃድ ይሁን።
_
፵) የሚጋቡ ሰዎች አካለ መጠን ያላደረሱ እናት አባት አሳዳጊ የሌላቸው ድኆች ቢሆኑ ፲፭ ዓመት እስኪሆናቸው ይጠብቁ። ከዚያ የፈቀዱትን ያድርጉ።
_
፵፩) አንዲትን ሴት ከታጨች በኋላ ሌላ ወንበዴ አስገድዶ ቢደፍራት እና ያጫት አልቀጥልም ካለ አስገድዶ የደፈራት ሚስት የሌለው ከሆነ ከወደደችው ሊያገባት ይገባል።
_
፵፪) ወንዶች ፈጽመው አካለ መጠን የሚያደርሱበት 20 ዓመት ነው። ይህም ባይሆን 25 ዓመት ነው። ሴቶች ደግሞ 12 ዓመት ነው። ይህም ባይሆን 15 ዓመት ነው።
_
፵፫) ከተጫጩ በኋላ የአንደኛው ግብሩ ጠባዩ የከፋ መሆኑን ተረድቶ እምቢ ቢል ይችላል። እምቢ ያለች ሴቲቱ ከሆነች ዓረቦኑን እጥፍ አድርጋ ትመልሳለች። ከሰጠ በኋላ አላገባም ያለ ወንዱ ከሆነ ዓረቦኑ ይቀርበታል።
_
፵፬) ልጁ በንጽሕና እኖራለሁ ካለ አባት ግድ አግባ ማለት አይገባውም።
_
፵፭) 25 ዓመት በላይ የሆናት ሴት ብትኖር አባት እናቷ ከማጋባት ቸል ቢሏት እርሷ ወደ ዳኞች አቤት ማለት ይገባታል። ራሷን የቻለች ከሆነች ግን ራሷ ማግባት ይገባታል።
_
፵፮) ጋብቻ ያለቁርባን አይጸናም።
_
፵፯) ለተጋቢዎች አንድ ልብስ ያለብሷቸዋል፣ ከጣታቸው አንድ ቀለበት ያገቡላቸዋል ጠባብ ከሆነ ፊት እርሱ አግብቶ ለእርሷ ይሰጣታል፣ አንድ መስቀል ያስጨብጧቸዋል። አንድ ዘውድ ይደፉላቸዋል እርሱ ደፍቶ ለእርሷ ይሰጣታል። ከዚያ እርሱ ቆርቦ ልብሱን ለእርሷ ይልክላትና ትቆርባለች። እሷም ከእናት ከአባቷ ቤት እርሱም ከእናት ከአባቱ ቤት ይቆያል። እንዲህ እያሉ ፵ ቀን ከኖሩ በኋላ ሠርግ ያደርጉላቸዋል። ልብስ የልጅነት፣ ቀለበት የሃይማኖት፣ ዘውድ የክብራቸው፣ መስቀል የመከራቸው ምሳሌ ነው።
_
፵፰) ሁለተኛ የሚያገቡ ካህናት ቢሆኑ ከሹመታቸው ይሻሩ። ከዚያ በኋላ ሦስተኛ ካገቡ ግን ርኩሳን ይሆናሉ።
_
፵፱) ሴት ስልሳ ዘመን ከሆናት በኋላ ተመልሳ አገባለሁ ብትል ከምእመናን ትለይ።
_
፶) ንጽሕ ጠብቀን ከሴት ርቀን እንኖራለን ብለው ከተሳሉ በኋላ ዳግመኛ የሚያገቡ ሰዎች ሕግ አፍራሾች ናቸው።
_
፶፩) አግብቶ ለፈታ ሰው መጽሐፈ ተክሊል ማድረስ አይገባም። ፍትሐት ዘወልድ ተደግሞለት በቁርባን ያገባል እንጂ።
_
፶፪) [ቁጥር ፱፻፮] ከሚጋቡት ሰዎች አንዱ ድንግል ቢሆን ለብቻው ተክሊል ያድርሱለት።
_
፶፫) ከሦስተኛ ጊዜ በላይ ማግባት የታወቀ ዝሙት ነው። ከአራተኛ ግቢ የተወለዱ ልጆች ለክህነት ለርስት አይገቡም።
_
፶፬) ብዙ ሴት ማግባት ዝሙት መውደድ ነው። በአንድ ጊዜ ሁለት ሴት ማኖር ለማንም አይገባውም። ይህን ያደረገ ካለ ግን ሁለተኛይቱን እስኪፈታት ድረስ ሥጋውን ደሙን ከመቀበል ቤተክርስቲያን ከመግባት ይከልከል።
_
፶፭) በሚስቱ ላይ ዕቁባት ያኖረ ካህን ቢሆን ከሹመቱ ይሻር፣ ጨዋ ቢሆን ከምእመናን አንድነት ይለዩት።
_
፶፮) ያመነች ሴት ያላመነውን ወንድ ብታገባ ከምእመናን ትለይ። ከእርሱ ተለይታ ንስሓ ብትገባ ግን ይቀበሏት። ልጁን ለኢአማኒ የዳረ ቢኖር ከምእመናን ይለይ።
_
፶፯) ወንድ ሚስቱ ከሞተች ጀምሮ አንድ ዓመት ሳይሆነው ማግባት አይገባውም። ዓመት ሳይሆነው ቢያገባ ግን ሚስቱ ከተወችው ሊወርሰው ከሚገባ ገንዘብ ሁሉ ይከልከል።
_
፶፰) ሴትም ባሏ ከሞተ ጀምሮ አሥር ወር ሳይሆናት ባል ብታገባ ከገንዘቡ ምንም ምን አትውረስ።
_
፶፱) ሳትሰስንበት ሰነፈች ደረቀች ብሎ ሚስቱን የፈታ ሰው ኃጥዕ ተብሎ ይፈረድበታል። በነውር የተፈታችውንም ንስሓ ሳትገባ ያገባት ሰው ቢኖር ኃጥዕ ተብሎ ይፈረድበታል።
_
፷) ባል ለሚስቱ የሚገባውን ፍቅር ያድርግላት፣ ሴትም ለባሏ የሚገባውን ፍቅር ታድርግለት።
151 views14:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 17:40:55 _ፍትሐ ነገሥት ክፍል ፲፰__
አንቀጽ ፳፬ ስለ እጮኝነት፣ ስለ ጋብቻ ይናገራል።
፩) የጋብቻ ዓላማ ዘር ለመተካት ልጅ ለመውለድ፣ የፍትወት ጾርን ለማጥፋት እና ለመረዳዳት ነው።
_
፪) ወንድ ከሴት ሄዶ ማጨት ይገባዋል። አኮ መፍትው ትሑር ብእሲት ኀበ ብእሲሀ አላ መፍትው ይሑር ብእሲ ኀበ ብእሲቱ እንዲል።
_
፫) የፍትወት ጾር የጸናበት ሰው ካለ ማግባት ይገባዋል። በፈቲው ጾር ሲነዱ ከመኖር ማግባት ይሻላልና።
_
፬) የፍትወትን ፆር ድል መንሣት የተቻለው ሰው ማግባትን መተው ይገባዋል። ሚስት የሌለው ሰው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝበትን ሥራ ያስባል።
_
፭) ማግባት በኦሪትም በወንጌልም የታዘዘ ነው። አንተ ሰው ሚስት ብታገባ ልፍታት አትበል።
_
፮) በድንግልና እኖራለሁ ብሎ ከተሳለ በኋላ ማግባት እጅግ ያሳፍራል። ኃፍረት ነው። ቢያገባ ግን ሁለተኛ ሚስት እንዳገባ ሰው ፍርድ ይሆናል።
_
፯) በሁለተኛ ግቢ ፍትሐት ዘወልድን ደግመው ያጋቧቸዋል እንጂ ሥርዓተ ተክሊል አይደረግም።
_
፰) ካህናት ሁለተኛ ካገቡ ክህነታቸው ይሻራል። ከሦስተኛ ግቢ በኋላ መጽሐፍ አላዘዘም።
_
፱) በሰው በእንስሳዊ ባሕርዩ የፈቲው ጾር ቢጸናበት ማግባት ይገባዋል። [ቁጥር ፰፻፳፯]። የፈቲው ጾር በሰው ባሕርይ እንደ ጭቃ ተለውሳ እንደ ነሐስ ተንሳ ትኖራለች [ሐተታ ቁጥር ፰፻፴፮]
_
፲) ከቅዱሳን አባቶቻችን ማግባትን ለዝሙት የሚሻ አላገኘንም። ዘእንበለ ለከዊነ ዘርዕ ባሕቲቱ። ልጅ ለመውለድ ብቻ ነው እንጂ።
_
፲፩) ፅንስ ከገፋ ሆድ ከሰፋ በኋላ ወንድ ከሚስቱ የደረሰ ቢሆን ይህ ሥራ የማይገባ ነው።
_
፲፪) የሚያጭ ሰው ራሱ ፈቅዶ ሂዶ ማጨት ይገባዋል። እርሱ ካልሄደ ሽማግሌ ልኮ፣ ወይም ደብዳቤ ሰዶ ማጨት ይገባዋል። ማጫ መስጠት ግን ለአሳዳጊው ወይም ለመጋቢው ይገባል።
_
፲፫) የሥጋ ዘመድን ማግባት አይገባም። መጽሐፍ ካላዘዘው ጋብቻ የተወለዱ አይጋቡ። ማግባት የማይፈቀድባቸው የሥጋ ዝምድናዎች:-
√ የልጅ ልጅ ልጅ
√ የልጅ ልጅ
√ ልጅ
√ እናት፣ አባት
√ አያት
√ ቅድመ አያት
√ አጎት፣ አክስት
√ ወንድም፣ እህት
√ የወንድም ልጆች፣ የእህት ልጆች
፲፬) ሐዋርያትም፣ ሠለስቱ ምእትም ከአራተኛው ትውልድ እና ከዚያ በላይ መጋባትን አልከለከሉም። [እስከ ሰባት ያለው ትውፊት ነው]። ይህንን መክፈል መጨመር ለኤጲስ ቆጶሳት ተገባቸው። ስለሆነም ዓላውያን በዝተው ከሰባት ትውልድ በላይ ባያገኙ ግብፃውያን በአራተኛው ማግባትን ፈቅደዋል።
_
፲፭) በትውልድ አቆጣጠር የአጎት ልጅ አራተኛ ነው። አቆጣጠሩም ፩ኛ አባቴ እኔን ወለደኝ፣ ፪ኛ አያቴ አባቴን ወለደ፣ ፫ኛ አያቴ አጎቴን ወለደው፣ ፬ኛ አጎቴ ልጁን ወለደ ይላል። [ሐተታ] በሀገራችን ግን በአንድ ወገን ሰባት፣ በአንድ ወገን ሰባት ተከልክሎ በስምንተኛው መጋባት ነው።
_
፲፮) በክርስትና ከተዛመዱ በኋላ መጋባት አይገባም። ይህ ዝምድና መንፈሳዊ ዝምድና ይባላል። የሚከተሉትን የሚከለከሉ ጋብቻዎች ናቸው።
√ አንሺ፣ ከተነሺ (ሴት ወንድን ብታነሣ)
√ ባል የሚስቱን ክርስትና ልጅ፣
√ ሚስት የባሏን ክርስትና ልጅ፣
√ የአንሺ እናት አባት ከተነሽ እናት አባት፣
√ የአንሺ ወንድም ከተነሽ ወንድም፣
√ የአንሺ ልጅ ከተነሽ ልጅ፣
√ የአንሺ የሚስት ልጅ ከተነሽ የሚስት ልጅ፣
፲፯) ሴት ከሌላ የወለደቻት ልጇን ባሏ ክርስትና ላነሣው ልጁ ማጋባት አይገባትም። ወንዱም ቢሆን ከሌላ የወለዳት ልጁን ሚስቱ ክርስትና ላነሣቸው ልጅ ማጋባት አይገባውም።
_
፲፰) መንፈሳዊ ዝምድናን ያፈረሰ ቀኖናው ሚስቱን ፈትቶ ምንኵስና ነው።
_
፲፱) በማሳደግና በማደጎ ከተዛመዱ በኋላ መጋባት አይገባም። የሚከተሉት የሚከለከሉ ጋብቻዎች ናቸው።
√ አሳዳጊ ከአዳጊ ጋር፣
√ የአሳዳጊ ልጅ ከአዳጊ ጋር፣
√ የአሳዳጊው ልጅ ከአዳጊ ልጅ ጋር፣
√ የአሳዳጊ እናት አባት ከአዳጊ እናት አባት፣
√ የአዳጊ አያት ከአሳዳጊ አያት፣
√ የአዳጊ አክስት አጎት ከአሳዳጊ አክስት አጎት
፳) በጋብቻ ከተዛመዱ በኋላ መጋባት አይገባም። የሚከተሉት የሚከለከሉ ጋብቻዎች ናቸው።
ልጅ የአባቱን ሚስት፣ ልጅ የእናቷን ባል፣
የልጅ ልጅ የአያቱን ሚስት/ባል፣
ልጅ የአባቱን ሚስት እኅት፣
የልጅ ልጅ የአያቱን ሚስት እኅት፣
ልጅ የአባቱን ሚስት እናት፣
የልጅ ልጅ የአያቱን ሚስት እናት፣
ልጅ የአባቱም ሚስት አያት፣
የልጅ ልጅ የአያቱን ሚስት አያት፣
አባት የልጁን ሚስት፣
አያት የልጅ ልጁን ሚስት፣
አጎት የወንድሙን ልጅ፣
ወንድም የወንድሙን ልጅ፣
አባት የልጁን ሚስት እኅት፣
አያት የልጅ ልጁን ሚስት እኅት፣
አባት የልጁን ሚስት እናት፣
አያት የልጅ ልጁን ሚስት እናት፣
አባት የልጁን ሚስት አያት፣
አያት የልጅ ልጁን ሚስት አያት፣
ወንድም የወንድሙን ሚስት፣
አጎት የወንድሙን ልጅ ሚስት፣
ወንድም የወንድሙን ሚስት እኅት፣
አጎት የወንድሙን ልጅ ሚስት እኅት፣
ወንድም የወንድሙን ሚስት እናት፣
አጎት የወንድሙን ልጅ ሚስት እናት፣
ወንድም የወንድሙን ሚስት አያት፣
አጎት የወንድሙን ልጅ ሚስት አያት
ባል የሚስቱን ዘመዶች
፳፩) የጌታ ሚስት ባሏ ነጻ ያወጣውን ባሪያ ማግባት አይገባትም። [ሐተታ] ልጇን ማግባት ነውና።
_
፳፪) በሃይማኖት የማይመስለንን/የማትመስለንን ማግባት አይገባም።
_
፳፫) አባለ ዘሩ ሩካቤ ማድረግ የማይችል ወንድ ማግባት የለበትም። ፈናፍንታምም ማግባት የለበትም። ፈናፍንት ማለትም የወንድና የሴት አካል ያለው ነው። የሚጠመቅበት ቀን የሚሸናበት ጾታ ታይቶ ይሆናል። በወንድ አካሉ የሚሸና ከሆነ በ፵ ቀኑ፣ በሴት ከሆነ በ፹ ቀኗ ትጠመቃለች።
_
፳፬) ሴት ልጅ በማኅፀኗ ሩካቤን የሚከለክል አፅም ካለባት ማግባት አይገባትም።
133 views14:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 19:15:51
47 views16:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 19:15:02 ስድብ በቀጠሮ
አባ ገብረኪዳን
https://t.me/deacon1221

ሴትየዋ በሰፈሩ ውስጥ የታወቀች ተሳዳቢና ተንኳሽ ናት። ወቅቱ የአቢይ ጾም መግቢያ አካባቢ ነው "አሁንስ በጾም በጸሎት ተወስኜ መኖር አለብኝ" ብላ ለራሷ ቃል ትገባና የንስሐ አባቷን ታማክራለች።

የንስሐ አባቷም በውሳኔዋ ተደስተው መልካም ማድረጓን ገልጸው እንዲህ ሲል ይመክሯታል። "ልጄ አደራሽን ይህ የሱባዔ ወቅት ሁላችንም በጾምና በጸሎት ወደ ፈጣሪያችን የምንመለስበትና ስለ ኃጥያታችን የምናለቅስበት ነው እኛ ክርስትያኖች በዚህ ጊዜ እንኳንስ እርስ በእርስ ልንጣላ ይቅርና ጠላታችንን የምንወድበት፣ ስንበድል ይቅርታን የምንልበት የንስሐ ጊዜ ነው። ስለዚህ እንኳን አንቺ ቀድመሽ ልትናገሪ ቢናገሩሽም እንኳን በትዕግስት ማለፍ ይኖርብሻል። አደራ ልጄ በርቺ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ይሁን። ብለው ባርከው ያሰናብቷታል።

ጾሙ ተጀመረና በሦስተኛው ቀን ሴትየዋ የከሰዓቱን ቅዳሴ አስቀድሳ ወደ ቤቷ ስትገባ "አንዴ ሌባ ካሏት ብትቆርብም አያምኗት" እንደተባለው የመንደሩ ሴት በነገር ጠመዳት። እስኪ ተመልከቷት አሁን ላያት ሰው እውነተኛ ክርስቲያን አትመስልም?? ወገኛ......እያሉ ዘለፏት እሷ ግን የንስሐ አባቷ የመከሯትን አስታውሳ እንዳትሳደብም ጾም በመሆኑ እንዲህ አለች "እሺ አሁን ስደቡኝ ግድ የለም ይህ ጾም ይፈታና እያንዳንድሽን ልክ አስገባሻለሁ። .......

ሁሌም ቢሆን ተናግሮ አናጋሪውን ያዝልኝ ማለት ደግ ነው ቢሆንም ግን የብዙዎች ክርስትና እንደ ፋብሪካ ሠራተኛ በሽፍት(በፈረቃ) ነው። በጾም ጊዜ ወደ ቤተክርስቲያን እንገሰግሣለን ለፋሲካ ግን የመጠጥና ጭፈራ ቤቱን እናጨናንቃለን።

የሁዳዴ ክርስቲያን የፋሲካ ዘፋኝ መሆን አይገባንም ።
"በጊዜውም አለጊዜውም ጽና "
50 views16:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 15:39:35
61 views12:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 15:39:14
61 views12:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ