Get Mystery Box with random crypto!

ዳሸን ባንክ ታላቁን የረመዷን ወር አስመልክቶ የጋራ ኢፍጣር መርሃ-ግብር አዘጋጀ ዳሸን ባንክ በ | Dashen Bank

ዳሸን ባንክ ታላቁን የረመዷን ወር አስመልክቶ የጋራ ኢፍጣር መርሃ-ግብር አዘጋጀ

ዳሸን ባንክ በዛሬዉ ዕለት በሸራተን አዲስ ሆቴል በእስልምና ዕምነት ተከታዮች ዘንድ ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠውን የረመዳን የጾም ወርን አስመልክቶ የኢፍጣር መርሃ ግብር አዘጋጀ፡፡

የጾምና የኢባዳ ወር በሆነው ረመዷን በየዓመቱ የሚያዘጋጀዉ ይህ የኢፍጣር መርሃ-ግብር ባንኩ ለደንበኞቹ ያለውን ክብር የሚገልጽበትና የእንኳን አደረሳቸሁ መልዕክት የሚያስተላልፍበት ነዉ ፡፡

በረመዷን ወር ምዕመኑ በጾም እና ሌሎች የአምልኮ ተግባራት (ኢባዳ) የሚተጋበት እንደመሆኑ ዳሸን ባንክ ጾመኞች በጋራ እንዲያፈጥሩና ዱዓ እንዲያደርጉ ይህን የአብሮነት መርሃ-ግብር አዘጋጅቷል፡፡ በዚህ የኢፍጣር መርሃ-ግብር ላይ የባንኩ ደንበኞችን ጨምሮ የባንኩ የቦርድ አባላት፣ የውጭ ሃገር ኤምባሲ ተወካዮችና ሌሎች የክብር እንግዶች ታድመዋል፡፡

ዳሸን ባንክ በቅርቡ ሸሪክ የተሰኘውን ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት 6ተኛ ዓመት በድምቀት ማክበሩ ይታወሳል፡፡