Get Mystery Box with random crypto!

ዳሸን ባንክና የአሜሪካ ኤምባሲ “አይኮግ ኤኒ ዋን ካን ኮድ” ያዘጋጀውን የፈጠራ ውድድር በአጋርነት | Dashen Bank

ዳሸን ባንክና የአሜሪካ ኤምባሲ “አይኮግ ኤኒ ዋን ካን ኮድ” ያዘጋጀውን የፈጠራ ውድድር በአጋርነት አስጀመሩ

ዳሸን ባንክና የአሜሪካ ኤምባሲ “አይኮግ ኤኒ ዋን ካን ኮድ” የተሰኘ ድርጅት ለሶስተኛ ጊዜ የሚያካሂደውን “ሶልቭ ኢት” የተሰኘ የቴክኖሎጂ ዘርፍ የስራ ፈጠራ ውድድር በአጋርነት በይፍ አስጀምረዋል፡፡

የዳሸን ባንክ የማርኬቲንግና ሰርቪስ ኳሊቲ አሹራንስ ዳይሬክተር አቶ እንዳለ ገብረስላሴ ውድድሩ በይፋ በተጀመረበት ወቅት ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ዳሸን ባንክ ምንም እንኳን የራሱን የፈጠራ ውድድር እየተገበረ ቢሆንም “አይኮግ ኤኒ ዋን ካን ኮድ” ላዘጋጀው ተመሳሳይ አላማ ላለው ለዚህ ውድድር አጋር እንዲሆን ጥያቄ ሲቀርብለት አዎንታዊ ምላሽ ለመስጠት እንዳላመነታም አመልክተዋል፡፡

ባንኩ ለውድድሩ ስኬት የበኩሉን ድጋፍ እንደሚያደርግም ጠቁመዋል፡፡

የአሜሪካ ኤምባሲ ፐብሊክ አፌይርስ ኦፊሰር  ሩትአን ስቴቨንስ ክሊትዝ  በበኩላቸው ውድድሩ ቴክኖሎጂ ባልደረሰባቸው የአገሪቱ አካባቢዎች ያሉ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ የፈጠራ ውጤቶችን ለማግኘት እንደሚያስችል አመልክተዋል፡፡

ኤምባሲውም ለውድድሩ ስኬት የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰው ለሶስተኛው ዙር ውድድርም አስፈላጊውን ድጋፍ ለማበርከት ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ለሶስተኛ ጊዜ የሚካሄደው ሶልቭ ኢት የቴክኖሎጂ ዘርፍ የፈጠራ ውድድር በአዲስ አበባ፣ ባህር ዳር፣ ድሬዳዋ፣ ጅማ፣ ደሴ እና ወላይታ ከተሞች ይካሄዳል፡፡