Get Mystery Box with random crypto!

❝ይድረስ ለኢድ ሶላት ለሚወጡ እህቶች❞ ☞ የኢድ ሶላት ለወንድም ለሴትም | ❥ ዳሩል ኢስላም/Darul Islam ❥

ይድረስ ለኢድ ሶላት ለሚወጡ እህቶች


የኢድ ሶላት ለወንድም ለሴትም የተደነገገ ኢባዳ ነው። ሴቶች ልክ እንደ ወንዶቹ ለኢድ ሰላት መውጣታቸው የተወደደ ተግባር ነው። እንዲወጡም ታዘዋል። ነገር ግን በምትወጣበት ሰአት እነዚህን መስፈርቶች ልትጠብቅ ይገባል።

①⇘ወፍራም፣ ሰፊ፣ ረጅምና ሁሉ ሰውነቷን የሚሸፍን አለባበስ መልበስ አለባት!

②⇘ሽቶ የሚባል ነገር በፍፁም ሊነካት አይገባም!

③⇘አቅሟ በቻለው ሁሉ ከወንዶች መራቅና ከነሱ ጋር ሳትጋፋ የመንገዱን መሀል ሳይሆን ጫፍ ጫፋን ይዛ መሄድ አለባት!

④⇘በተክቢራም ይሁን በሌላ ድምፇን ዝቅ ማድረግ አለባት!

⑤⇘ጫማዋ ከፍ ብሎ ሲንቋቋ ሰውን የሚጣራ መሆን የለበትም!

⑥⇘የልብሷ ከለር ደመቅ ብሎ የሰውን አይን የሚስብና ጌጣ ጌጦች ያሉበት መሆን የለበትም!

⑦⇘እራሷ ከመፈተንና ሰውን ከመፈተን ጥንቃቄ ልታረግ ይገባል!

⑧⇘ በአረማመዷ፣ በአነጋገሯና በእይታዋ ሀያእ የተላበሰች ልትሆን ይገባል!

ምክንያቱም ኸይር እሰራለሁ ብላ ወንጀል ከመሸከም፣ የጀነት ሰበብ አደርሳለሁ ብላ የጀሀነም ሰበብ እንዳታደርስ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባታል።

በአሁን ሰአት ግን ለኢድ ሶላት ብለው በሚመጡ አንዳንድ ሙስሊም እህቶች እያፈርን አንገታችን እየተደፋ ነው። እስልምና እንዲሁም ሙስሊሞችን እያሰደቡ ነው።

ልብሷ ከራሷ ተጣብቆ፣ ሰውነቷን ወጣጥራ፣ ፊቶቿ እግሮቿና እዶቻን ከፍታ፣ ሽቶ ተለቅልቃ፣ ቻፕስቲክ ተቀብታ፣ ቅንድቧን ተቀንድባ፣ የተቀባችውን ሂና እያሳየች፣ የኢትዮጵያ ባንድራ ግምባራ ላይ አስራ፣ ወደ ግራና ቀኝ የሚያወዛውዝ ጫማ ለብሳ፣ ድምፇ ከፍ አድርጋ እየሳቀች፣ ከወንዶች እኩል እየተጋፋች፣ ወንዶችን አፍጣ እያየች፣ በየሱቁ እየተዘዋወረችና ሌሎችም ሙሀለፋቶች በመፈፀም እራሷም ተፈትና ሌላውንም ፈትና፣ እራሷ ወንጀል ውስጥ ከታ ሌላውንም ዘፍቃ የወንጀል መአት ተሸክማ ወደ ቤቷ የምትመለስ አለች።

እንዲህ አይነቷ እህት ምናለ እቤቷ በተቀመጠች!

  【በድጋሜ  የተለቀቀ】
@Darul_Islam_channal
@Darul_Islam_channal