2021-08-26 15:36:41
الحمد لله، وأشهد أن لا إله إلا الله وحده لا شريك له، وأشهد أن محمدًا عبده ورسوله.
•
ክፍል አንድ
ለወንድም ዐሊ ሑሴን ሰሞኑን በኡስታዝ ሳዳት ከማል፣በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወርና በኡስታዝ ሰዒድ ሙሳ (ሐፊዞሁሙሏሁ ጀሚዓን) ላይ ረድ በማለት ለቀጠፈባቸው ቅጥፈት የተሰጠ መልስ
•
በሀገራችን ኢትዮዽያ የሰለፊያ ዱዐቶች እጅግ በጣም የሚረዳቸው ባስፈለገበት ጊዜ የተለያዩ የጥመት አካለት ውድቀታቸውን በሚመኙበት ወቀት ወጣቱን ከተለያዩ የጥመት አካላት ለማትረፍ ደፋ ቀና እያሉ ሌላው እንኳ ቢቀር በዱዐ ሊረዱ በሚገባቸው ጊዜ! ወንድም ዐሊ ሁሴን ሶስት ክፍል በያዘ ድምፅ ረድ ብሎ ደንገት መጣ! እንዳሐቂቃ ረዱ የጥመት አካላትን ያስደሰት ሰለፊዩችን ያስደነገጠ ነበር።
•
ኢንሻ አሏህ በዚህ ፁሁፊ ወንድም ዐሊ ላነሳቸው የተወሰኑ ነጥቦችን በማንሳት መልስ እሰጣለሁ
•
ላነሳቸው ሀሳቦች መልስ ከመስጠቴ በስተፊት ሁለት መግቢያዎችን ላስቀድም
•
አንደኛ:- መልስ እንድፅፍለት ያነሳሱኝ ሀሳቦች
መልስ ለመፃፍ ያነሳሱኝ ሶስት ነጥቦች ናቸው።
1, የመልእክተኛው (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም)
«من رد عن عرض أخيه رد الله عن وجهه النار يوم القيامة»، أخرجه الترمذي (1932) وحسنه.
"ከወንድሙ ክብር ላይ የመለሰ አሏህ የውመልቂያማ ከፊቱ ላይ እሳትን ይመልስለታል" የሚለው ሐዲሥ
2, ወደመንሐጅ ሰለፍ አድስ የገቡ ልጆች ሹብሃ ስለሚወድቅባቸው ሹብሃቸውን ለማስወገድ
3, ወንድም ዐሊ ባደረገው ረድ የተለያዩ የሰለፊያ ዐሊሞችን ስለተቸ እንድሆም የፍላጎቱን ስለተናገሩለት የተለያዩ የጥመት ባለቤቶችን ለሀገራችን ወጣት እያስተዋወቀ ስለሆነ ከዚህ ድርጊቱ ይቆጠብ ዘንድ በዚህም ስህተቱ ሰለፊዮች እንዳይከተሉት በማሰብ ከዚህ በታች እንደሚከተለው ላነሳቸው የተወሰኑ ነጥቦች መልስ እሰጣለሁ።
•
ሁለተኛው መግቢያ: ካነሳሃቸው ሃሳቦች መካከል መልስ የምሰጠው በቻናሎቻቸው ለቀውት በነበረው ፅሁፎች ዙሪያ እንጅ ከአንተ ጋር በግል እሄን ብለውኛል እንድህ ጠይቀውኛል ምናምን እያልክ ስለምታነሳው የግል ወሬ አይደለም።
በግል እንድህ ብለውኛል እያልክ ላነሳሀቸው ነጥቦች መልስ አልሰጥም ምክኒቱም
ውሸትህን ይሆን ወይንም ያሉህን ያለአግባብ ተረድተህው ይሆን ማረጋገጥ ስለሚያስፈልግ።
በተለይ ኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ (ሐፊዞሁሏህ) የፃፏት አጭር ፅሁፍ እንደዋሸህ ትጠቁማለች ስለዚህ ለውሸትህ መልስ መስጠት እኔን አይመለከትም እነኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ የሚመልሱትን እንጠብቃለን
አይደለም በግል አውረተውኛል ያልከው ይቅርና እዚህም ከፅሁፋቸው አየመዘዝክ ሀሳብ ስታወጣ ሃሳብ የመለጠጥ ፅሁፉን የማይሸከመውን ሀሳብ እሄን ያስይዛል እያልክ ማሸከም ስለሚታይ ስላልሰማነው እውሸት ይሁን እውነት ስላላረጋገጥነው ነጥብ መልስ አልሰጥም
አሏህን ለመልካሙ ነገር ሁሉ እንዲገጥመኝ ሐይልና ብርታትን እንዲሰጠኝ እየተማፀንኩ ወዳነሳሃቸው ሃሳብ አልፋለሁ
_____ 1, "አሁን በጣም እሰለፍዩ መሃል ላይ ፊትና የሆነው ሳዳት የኢብኑ ሙነወር ፊትና ነው።" አልክ
•
መልስ:-
ኡስታዝ ሳዳት ከማልና ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ምንአይነት ፊትና ሁነው ነው? እንዲህ እንደታላቅ አጀንዳ "ፊትና የሆኑት" ብለህ የምታነሳው። እኛ እነዚህን ሁለት ኡስታዞች በሰለፍያ ላይ የመጣን ፊትና ለክብራቸው ሳይጨነቁ የባጢል ሰዎች ዛቻ ሳይንበረከኩ መመለሳቸውን ነው የምናውቀው። ቢገባህ በሰለፊዮች መሀል ትልቅ ፊትና የከፈተው የሰሞኑ ያንተ ረድ ነው።
እንደው እንደምትለው ተሳስተዋል ሊታረሙ ይገባቸዋል ብትል እንኳ በዚህ መልኩ ርእስ መክፈት በኡስታዞች ላይ ድንበር ማለፍ ነው የሚሆነው። ወንድሜ ጥፋት ካገኘህ መልስ ስጥ ግን ድንበር አትለፍ!!
____
2, "ቅርብ ጊዜ ራስን ማየት የሚል ፅሁፍ ለቀቅ
ወደሰዎች ከማየት በፊት ወደሰዎች ከማነፃፀር በፊት ሰዎች እከሌ እንድህ ነው እከሌ እንድህ ነው ከማለት በፊት እራሳችንን መገምገም እራሳችንን ማየት ፉላን አላን ከማለት በፊት የሚል በዚህ ዙሪያ ላይ ያለ በተለይ በአህለል ቢድዐ ስለመናገር አህለል ቢድዐን ስለማስጠንቀቅ አህለል ቢድዐን እንድህ ነው ማለት እስመልክቶ ሰፊ የሆነ ነገር ፃፈ"አልክ
•
መልስ:-
1, አትዋሽ ያልተፃፈ አታንብብ ካነበብከው ውጭ እውስጥህ በታመቅ ጭፍን ጥላቻ አትረዳ ፅሁፉ እንዲህ አይልም
"እራስን መመልከት" የሚለውን የኡስታዝ ኢብኑ ሙነወርን ፅሁፍ ከጥላቻ ርቆ ያነበበ ሰው ያልከውን እንዳልፃፈ በደንብ ይረዳል
•
2, የኡስታዝ ፅሁፍ ስጨምቀው የሚወጣው ሰውን በጭፍን አትከተሉ አንድን ሃሳብ ከመውሰዳችሁ በፊት በመረጃ አረጋግጡ የሚል ጥቅል መልእክት ይሰጣል ታዲያ እሄ ከምኑ ላይ ነው ጥፋቱ!
በጭፍን መከተልን መቃወም የኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ብቻ አቋም አይደለም! ቢገባህ ከድሮ እስከዘንድሮ ያሉ የሰለፊይ ዑለሞች ዳዒዎች አቋም ነው በኪታቦቻቸው በዳዕዋዎቻቸው እሄን አጥብቀው ያስተምራሉ
•
3, "በተለይ በአህለል ቢድዐ ስለመናገር አህለል ቢድዐን ስለማስጠንቀቅ አህለል ቢድዐን እንድህ ነው ማለት አስመልክቶ ሰፊ የሆነ ነገር ፃፈ አልክ"
•
ከፅሁፉ ውስጥ እሄን ያለበትን መዘህ እስኪ አምጣ ??? ለምን በአደባባይ እየዋሸህ አቅልህን የዑቀላዎች መሳቂያ ታደርጋለህ ??
ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ነው በአደባባይ አጥፌዎችን ማጋለጥን የሚቃወመው??? መፃሐፎቹ፣ ፖስቶቹ፣መሐደራዎቹ፣ዱሩሶቹና በተለያየ አጋጣሚ ያደረጋቸው ስራዎቹ በአደባባይ በመረጃ አጥፌዎችን ስም እየጠራ ለማጋለጡ ሒያው ምስክር ናቸው።
አይ እሄ ድሮ ነበር ዛሬ ተቀይሯል ተአቋሞ ተንሸራቱ "በአጥፊዎች ላይ ባደባባይ መናገርን" መቃወም ጀምሯል እንኳ እንዳትል በቅርቡ
"ደፋሩ ዐብዱልቃዲር ኑረዲን" በሚል ርእስ ስሙን ጠቅሶ በአደባባይ ላጠፋው ጥፋት መልስ ጥፏል። እኔ የሚገርሞኝ እሄን ውሸትህን እየተቀባበሉ ሸር የሚያደርጉት ናቸው። እንደው ከውስጣችሁ አሏህን እንፍራ እሄ ውሸት ነው የሚል እንኳ እንዴት ይጠፋል!!
ወንድምህ ላይ ያላለውን ብሏ በማለት ከወንጀል ውጭ ምንም አታተርፍም አሏህ እንዲህ ይላል:-
•
وَالَّذِينَ يُؤْذُونَ الْمُؤْمِنِينَ وَالْمُؤْمِنَاتِ بِغَيْرِ مَا اكْتَسَبُوا فَقَدِ احْتَمَلُوا بُهْتَانًا وَإِثْمًا مُّبِينًا
እነዚያንም ምእምናንንና ምእምናነትን ባልሰሩት ነገር (በመዝለፍ) የሚያሰቃዩ ዕብለትንና ግልጽ ኃጢአትን በእርግጥ ተሸከሙ፡፡")
ያልፃፉትን ፅፈዋል፣ያላሉትን ብለዋል እያልክ በክብራቸውላይ መፀዳዳት እነሱን አዛ ማድረግ ነው።
•
እኔምልህ በሰለፍያ እንቁ ኡስታዞች ላይ ያላሉትን በለዋል እያሉ ባደባባይ ከማውራት የበለጠ ምን ፊትና የሚፈጥር አለና ነው? ሰለፊያ ላይ ፊትና እንደሆኑ አድርገህ የምታወራው!!
•
ወንድሜ እሄ በውሸት ሰለፊዮች ላይ ያላሉትን በለዋል የፃፉትን እሄን ያስይዛል እያሉ የራስን ሃሳብ በማሸከም ረድ መስጠት ዑለሞች ዘንድ የተወገዘ ነው።
915 viewsH, 12:36