Get Mystery Box with random crypto!

የግል ዋይፋያችን እንዳይጠለፍ እና ለመረጃ ጥቃት እንዳያጋልጠን በምን መልኩ መከላከል እንችላለን? | DaniApps™

የግል ዋይፋያችን እንዳይጠለፍ እና ለመረጃ ጥቃት እንዳያጋልጠን በምን መልኩ መከላከል እንችላለን?

ብዙ ጊዜ ለቤት ዉስጥ አገልግሎትም ሆነ ለመስሪያ ቤት ያስገጠምነዉ ዋይፋይ እኛ ላሰብነዉ አገልግሎት እየሰጠ ከሆነ ስለ ደህንነቱ ብዙም ግድ አይሰጠንም፡፡ ነግር ግን ይሄ ተግባር ፍፁም ስህተት የሆነና ብዙ ችግሮችን ሊያስከትል የሚችል ልምድ ነው፡፡

ለዋይፋዮቻችን ተገቢውን የደህንነት ስርዓት ተግባራዊ የማናደርግ ከሆነ የሳይበር ወንጀለኞች አውታረ-መረቡን /networks/ በመጠቀም ምስጢራዊ መረጃዎችን መመንተፍ እና ዋይፋዩን በሚገባው ፍጥነት እንዳንጠቀም ሊያስተጓጉሉብን ይችላሉ፡፡

በመሆኑም ከአገልግሎት መስተጓጎል እና ከጠላፊዎች ለመጠበቅ የሚከተሉትን አማራጮች መጠቀም ይመከራል፡፡

- 1. ጠንካራ የይለፍ ቃል /password/ ይጠቀሙ
የዋይፋይ ራውተሮች ሲመረቱ ነባሪ መጠቀሚያ ስም /default username/ እና ምስጢራዊ የይለፍ-ቃል ይኖራቸዋል። የራዉተሩ አምራች ከታወቀ እነዚህን የዲፎልት መጠቀሚያ ስሞችን እና ምስጢራዊ የይለፍ-ቃላትን ለመገመት በጣም ቀላል ነው፡፡ በመሆኑም ለግል ዋይፋዮቻችን ደህንነት ለማረጋገጥ ጠንካራ የይለፍ-ቃሎችን መጠቀም ይገባል፡፡

- 2. የበይነ-መረብ አገልግሎት መስጫ መለያ ይቀይሩ /SSID/
እያንዳንዱ ራውተር ከነባሪ መጠቀሚያ ስም ማለትም “ነባሪ” /default/ ጋር ስለሚመጣ የአውታረ መረባችንን አገልግሎት መስጫ መለያ ስም /SSID/ መለወጥ ያስፈልጋል። ይህንን በራውተራችን ገመድ አልባ መሰረታዊ ቅንብር ገጽ /wireless basic setting page/ በመሄድ መጠሪያውን በመለወጥ የዋይፋያችንን ተገማችነት በማስቀረት ለጥቃት እንዳንጋለጥ ማድረግ እንችላለን፡፡

- 3. አውታረ-መረባችንን መመስጠር
የዋይፋይ ራውተራችን ከመረጃ ጠለፋ እና የአገልግሎት መስተጓጎል ለመከላከል የአውታረ-መረብ ምስጠራን መተግበር አስፈላጊ ነዉ፡፡

- 4. ሎጊንግ መፍቀድ (Enable Logging)
ሎጊንግ አማራጭን ስንፈቅድ (Enable) የዋይፋይ ኔትዎርካችንን እንዳይጠለፍ ለማድረግ ከሚያግዙ መንገዶች አንዱ ነዉ፡፡ በዋይፋይ ራውተራችን ውስጥ ያለው የመለያ ባህሪ ሁሉንም የአይፒ አድራሻ ይመዘግባል፡፡ እንዲሁም ሁሉንም የግንኙነት ሙከራዎች ዝርዝር ይሰጣል። ምንም እንኳን ይህን ተግባራዊ ማድረግ ዋይፋያችንን ከጠላፊዎች የማይጠብቅ ቢሆንም ማንኛውንም አጠራጣሪ እንቅስቃሴ ለመከታተል ይረዳናል፡፡ ይህንን ስርዓት "Enable" ማድረግ ይገባናል፡፡

- 5 የዋይፋይ ሲግናል ማስተካከል
የዋይፋይ ሲግናላችን ጠንካራ እና በአጭር የቆዳ ስፋት ብቻ የምንጠቀም ከሆነ የዋይፋዩን ሲግናል አቅም መቀነስ ይኖርብናል፡፡ ይህን ለማድረግ የራውተራችንን ሞድ 802.11n ወይም 802.11b ምትክ 802.11g መጠቀም ይመከራል፡፡

- 6 የራውተራችንን ፈርምዌር ማዘመን
ራውተራችን ፈርምዌር /Firmware/ የሚባል ሶፍትዌር አለው፡፡ ፈርምዌር ጊዜው ያለፈበት እና በወቅቱ ያልዘመነ ከሆነ ለአንዳንድ የደህንነት ሰጋቶች የተጋለጠ መሆኑ አይቀርም፡፡ ምንም እንኳ የዘመናዊ ራውተሮች ፈርምዌር በራሳቸው የሚያዘምኑ ቢሆንም እርግጠኛ ለመሆን በየጊዜው መዘመናቸውን ልናረጋግጥ ይገባል፡፡

- 7 የራውተራችን ፋየርዋል ማንቃት መጠቀም
የራውተራችንን ፋየርዎል/firewall/ ተግባራዊ ማድረግ ወይም ማንቃት ይኖርብናል፡፡ ይህን በማድረጋችን ሊከሰት ከሚችል ተጨባጭ የሳይበር ጥቃቶች እራሳችንን መከላከል እንችላለን፡፡



SUBSCRIBE US ON YOUTUBE

YouTube
https://www.youtube.com/channel/UCksMp0FnUAPLNkTdsBHzG9g

Linkedin Profile
https://www.linkedin.com/in/daniapps/

ElaTech
DaniApps