Get Mystery Box with random crypto!

ቀን 4 “መልሰን፣ አድሰን” ባለፉት ቀናት ስለ ኃጢአትችን ምህረትን ለመቀበል ወደ ጸጋው ዙፋን ቀ | የህይወት ቃል / Word of life

ቀን 4
“መልሰን፣ አድሰን”
ባለፉት ቀናት ስለ ኃጢአትችን ምህረትን ለመቀበል ወደ ጸጋው ዙፋን ቀርበልና። ዛሬ ደግሞ ያለፈ የበደል ዕዳችን እንዲሰረዝ ብቻ ሳይሆን፣ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ለመመለስና ከእርሱ ጋር ያለን ሕብረት እንዲታደስ ከነብዩ ኤርሚያስ ጋር እንዲህ ብለን እንጸልይ ፦
“አቤቱ መልሰን እኛም እንመለሳለን፤ ዘመናችንን እንደቀድሞ አድስ።”
አምላካችን እግዚአብሔር ከገባንበት የከንቱ ህይወት አዘቅት ውስጥ የሚያወጣን እንደዚሁም እንደገና አስቀድሞ ወዳዘጋጀልን ክብር ሊመልሰን የሚፈልግ አፍቃሪ አባት ነው።
የጠፋው ልጅ ወደ አባቱ ሲመለስ ከአባቱ ባሪያዎች አንዱ ሆኖ ለመስራት ነበር የተመኘው! አባቱ ግን ወደ ቀድሞ የልጅነት ክብሩና ስልጣኑ መለሰው። በአመጽ ከቤቱ ኮብልሎ ያጣውን ሁሉ አደሰለት።
አምላካችን ለእኛም ተመሳሳዩን ሊያደርግልን “ወደ እኔ ኑ” ይለናል። እኛም ለዚህ ጥሪው ምላሽ በመስጠት “አቤቱ፣ መልሰን፣ አድሰን” እንበለው። ህይወታችንን በትክክል ሊያድስና ሊያስተካክል የሚችለው አስቀድሞ የፈጠረን እርሱ ብቻ ነው ።
ምንም እንኳን ህይወታችን ነብዩ ህዝቅኤል እንደተመለከታቸው የደረቁና የተበታተኑ አጥንቶች እንደገና የመታደስ ተስፋ የሌለው ቢመስልም፣ ለእግዚአብሔር ግን የሚሳነው እንደሌለ እናስታውስ።
እርሱ እነዚያን ዐጥንቶች እንደገና ገጣጥሞ ስጋ አልብሶ፣ እስትንፋስ ዘርቶ፣ ታላቅ ሰራዊት አድርጎ ያቆመ ሁሉን ቻይ አምላክ ነው። ይህንን በማመን፣ ከእርሱ የራቀውን ህይወታችንን ወደ እርሱ ልመሶ፣ የተመሰቃቀለውን ህይወታችንን እንዲያድስልን “አቤቱ ወደ አንተ መልሰን፣ አድሰን።” ብለን እንጸልይ።
አባት ሆይ፣ መልሰን እኛም ወደ አንተ እንመለሳለን፤ ዘመናችንን እንደ ቀድሞ አድስልን። አሜን።