Get Mystery Box with random crypto!

#የኢትዮጵያ_ክልል_ክለቦች_ሻምፒዮና በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው የኢትዮጵያ ክልል ክለቦች | ዳጉ ስፖርት DAGU SPORT

#የኢትዮጵያ_ክልል_ክለቦች_ሻምፒዮና

በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው የኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፕዮና ወደ ወሳኝ ምዕራፍ የተሸጋገረ ሲሆን በነገው ዕለት የሩብ ፍፃሜ ተጠባቂ ጨዋታዎች የሚደረጉ ይሆናል ።

3:00 ሰዓት በሚጀመረው የዕለቱ መጀመሪያ ጨዋታ የአማራ ክልል ተወካይ የሆኑ ሁለት ቡድኖች ደምበጫ ቲሊሊ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል። ሁለቱ የአንድ ክልል ቡድኖች እርስ በርስ በመገናኘታቸው አንድ ተወካይ በግማሽ ፍፃሜ ክልሉን ወክሎ ማለፉ ማረጋገጥ ተችሏል።

የዕለቱ ሁለተኛ ጨዋታ በ5:00 ሰዓት መታፈሪያ ክፍሌ ደንቢዶሎ የሚያገናኝ ሲሆን የሲዳማ ክልል ተወካይ መታፈሪያ ክፍሌ ጊምቦ ዳዲበንን በማሸነፍ ሩብ ፍፃሜውን የተቀላቀለ ቡድን ነው
የኦሮሚያ ክልል ሻምፒዮና በመሆን ወደ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና ማለፍ የቻለው ደንቢ ዶሎ ከተማ በደርቢ ጨዋታ ጊምቢ ከተማን 1ለ0 በማሸነፍ ወደ ሩብ ፍፃሜ የተቀላቀለ ቡድን ሆኗል ፡፡

የ7:00 ሰዓት ጨዋታ ጎንደር አራዳ ቡልቡላ አሜን የሚያገናኘው ጨዋታ ሁለቱም ቡድኖች በመለያ ምት አሸንፈው ወደ ሩብ ፍፃሜው ያለፉ ቡድኖች ሲሆኑ ነገ ከፍተኛ ፉክክር የሚያደርጉ ጨዋታ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል ።

ልየሩብ ፍፃሜ መጨረሻ ጨዋታ 9:00 ሰዓት መንጌ ቤላሻንጉል ሱሉልታ ቢ መካከል የሚደረግ ሲሆን የቤንሻንጉሉ ተወካይ መንጌ ቤላሻንጉል የደቡብ ክልል ተወካይ የሆነውን ሚቶን በማሸነፍ ሩብ ፍፃሜ ደርሷል ሱሉልታ ቢ በአንፃሩ በደርቢ ጨዋታ አመያን በማሸነፍ ሩብ ፍፃሜ መድረስ ችሏል ።

በእርሶዎ ምልከታ ወደ ግማሽ ፍፃሜ የሚያልፉ 4 ቡድኖች የትኞቹ ናቸው ብለው ያስባሉ ግምቶዎን እና ሀሳባችሁን ያጋሩን!!


Telegram T.me/dagu_Sport