Get Mystery Box with random crypto!

#ደብረ_ማርቆስ_ከተማ ወደ ፍፃሜ ማለፋቸውን አረጋገጡ ። በኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና የ | ዳጉ ስፖርት DAGU SPORT

#ደብረ_ማርቆስ_ከተማ ወደ ፍፃሜ ማለፋቸውን አረጋገጡ ።

በኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና የሴቶች ውድድር ዛሬ የግማሽ ፍፃሜ የተከናወነ ሲሆን በጨዋታው ደብረ ማርቆስ ከ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ጨዋታቸውን አከናውነው መደበኛውን ደቅቃ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት በማጠናቀቃቸው በተሰጠው የመለያ ምት ደብረ ማርቆስ ከተማ 4ለ3 ጉለሌ ክፍለ ከተማን በመርታት ወደ 2016 ዓም የኢትዮጵያ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ ማደጋቸውን አረጋግጠዋል።

ደብረ ማርቆስ ከተማ በፍፃሜው ጨዋታ ከአምቦ ጎል ፊፋ  ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።

#ደብረማርቆስ 0-0 #ጉለሌ_ክ_ከተማ

#በመለያምት   
#ደብረማርቆስ  
#ገለሌ_ክ_ከ    

    

Telegram @dagu_Sport