Get Mystery Box with random crypto!

ካሴሜሮ! ብራዚላዊው ድንቅ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ካሴሜሮ ማን ዩናይትድን ሊቀላቀል እጅጉን ተቃርቧ | dagi sport ዮጵ

ካሴሜሮ!

ብራዚላዊው ድንቅ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ካሴሜሮ ማን ዩናይትድን ሊቀላቀል እጅጉን ተቃርቧል! እስኪ ስለ ካሴሜሮ አንዳንድ ነገሮች ጀባ ልበላችሁ!


ካሴሚሮ በዋነኝነት የሚጫወተው እንደ ተከላካይ አማካኝ ነው ወይም ደሞ DM ተብሎ የሚጠራበት ቦታ... በዚህ ቦታ ከሚጫወቱ ተጨዋቾች የላቀ ደረጃ ላይ ደርሶ ከግማሽ አስር አመታት በላይ ቆይቷል።

ከኳስ ጋርም ያለ ኳስም አስተዋይ፣ አካላዊ ብቃቱ እጅግ የተሟላ፣ ጠንከር ባለ አጨዋወት እና ታክሎቹ የሚታወቅ ብራዚላዊ አማካይ ነው።

ይህ ተጨዋች በዋነኛነት የሚታወቀው በቡድኑ ላይ ከፍተኛ የሆነ የመከላከል መረጋጋትን በማምጣት ወይም ደሞ የቡድኑን ሚዛን የመጠበቅ ከፍተኛ ችሎታ ያለው ልጅ በመሆኑ ነው!

አንድ ለአንድ ግንኙነቶችን ለማሸነፍ የማይቸገር ተጨዋች ሲሆን ከሳጥን ውጪ የሚመታቸው ምቶች የጎል እድልን የመፍጠር እድላቸው ከፍ ያለ ነው!!

የእርሱ የመከላከል ሚና እጅግ ከፍ ያለ ነው...በመሃል ሜዳ ላይ ጠንካራ የተከላካይ ሀይልን መስጠት የሚችልም ተጨዋች ነው!

...በዩናይትድ ቤት የእርሱ መኖር ከፍ ያለ ጥቅምን ይሰጣል!
በደብል ፒቮት ወይም በእርሱ ብቻ ይጫወት እንደሆነ ወደፊት የሚታይ ይሆናል።

ያም ሆነ ይህ የዩናይትድ ትልቁ ጉዳይ ለዓመታት ሲፈልገው የነበረውን ጠንካራ የተከላካይ አማካይ ማግኘቱ ነው!

ካሴሚሮ የተከላካይ ክፍሉን እጅግ ያግዛል...በሽግግር ወቅት (ማለትም ተቃራኒ ቡድን በካውንተር አታክ ሲመጣ) ሽግግሮችን በማስቆም ተከላካዮቻችን በተደጋጋሚ ወደ ጎል እንዲመለሱ የሚገደዱበትን ሁኔታ ይቀንሳል።

በተጨማሪም እንደ ፈርናንዴዝ እና ኤሪክሰን ያሉ ተጫዋቾች ለአጥቂዎች እድሎችን የመፍጠር አቅማቸውን ከፍ ያደርጋል።

በየትኛዉም መልኩ ብትመለከቱት ካሴሚሮ የቡድኑን ድንቅ ነገር በመጨመር ዩናይትድ ለአስር አመታት ያህል የጎደለዉን ገጽታ ይጨምራል!!!

MUFP በተጨማሪም @dagii30 አቀርብኩኝ