Get Mystery Box with random crypto!

መፍትሔው የችግሩ እውቀት ነው! ፨፨፨፨፨፨፨//////////////፨፨፨፨፨፨ በቅድሚያ ችግሩን አሳደ | ስነ-ልቦናዊ መፍትሔ

መፍትሔው የችግሩ እውቀት ነው!
፨፨፨፨፨፨፨//////////////፨፨፨፨፨፨
በቅድሚያ ችግሩን አሳደህ አግኘው፣ እወቀው፤ በመቀጠል መፍትሔውን ፈልግ። አስር አይነት መፍትሔ አንድን ያልታወቀ ችግር አይፈታውም። ችግርህን ሳታውቅ ብዙ አማራጭ መፍትሔዎችን ብትፈልግ በፍፁም ልትቀርፈው አትችልም። ያለበትን ችግር ምንንነት ያወቀ አንድ ሰው ከመፍትሔው ለመድረስ ከግማሽ መንገድ በላይ እንደተጓዘ ይቆጠራል። ስለታመምክ የምትወስደው መድሃኒት ሁሉ አያድንህም፤ ለመዳን የህመምህ አይነት መታወቅ ይኖርበታል። ብዙ ስለደከምክ ሃሳብህን አታሳካም፤ የሃሳብህን ምንንነት ማወቅ፣ መረዳት ግድ ይልሃል።

አዎ! መዳረሻ የሌለው ሰው በፈለገው መንገድ መጓዝ ይችላል ምክንያቱም ማረፊያውንና የሚያስኬደውን መንገድ አያውቅምና። እንዲሁ ችግሩን ያላወቀ ሰው ምንም እንኳን ብዙ አማራጭ መፍትሔዎችን ቢሞክርም ትክክለኛውን መፍትሄ ሊያገኝ አይችልም። ከየትኛውም መፍትሔ በፊት የቸግሩ ምንጭ፣ የችግሩ ምንነት መታወቅ አለበት። ሃገራዊ ችግር ይሁን፣ ግላዊ ችግር ምንም የተፈለገው መፍትሔ ቢሞከር መሰረቱ እስካልታወቀ ከድካም ውጪ ትርፍ አልባ ነው።

አዎ! ለመታረቅ የፀቡ መንስዔ መታወቅ አለበት፣ ለመስማማት ልዩነት ፈጣሪ ሃሳቦች ግልፅ ሊሆኑ ይገባል፤ ወደፊት ለመራመድ የጋራ መግባቢያ ሃሳቦች ይፋ መውጣት አለባቸው። እያንዳንዱ ከባድ ጉዳይ በጥቃቅን ሃሳቦች የተዋቀረ ነው። የመፍትሔ ሰው ነው የሚባል ሰው መፍትሔ በመዘርዘር የሚታወቅ ሰው አይደለም። በምትኩ ችግሮችን በመፈልፈል፣ መንስዔያቸውን በመለየት የሚታወቅ ነው።

አዎ! ጀግናዬ..! መፍትሔው የችግሩ እውቀት ነው። ችግርህን ካላወክ መፍትሔውን እንዳታስበው፤ ችግሩን ከተረዳህ ግን በእርግጥም መፍትሔው በእጅህ ነው። የፍቅር ህይወትህ ዋናው ችግር ምንድነው? መንሰኤውስ? የቤተሰብህ ትልቁ ችግር ምንድነው? መነሻውስ? የእራስህ ችግር ምንድነው? ምክንያቱስ? እነዚህን ጥያቄዎች ከመለስክ መፍትሔው ሊጠፋብህ አይችልም። ችግርህን ለመቅረፍ ችግርህን እወቅ፤ ወደፊት ለመጓዝ መሰናክሎችህን አስቀር፤ ህልምህን ለማሳካት ሰበበኛ ሃሳቦችህን ተሻገር።

https://telegram.me/counselingA