Get Mystery Box with random crypto!

በኢትዮጵያ 665 ተጨማሪ ሰዎች ኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው፤ 640 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል ******* | Coronavirus in Ethiopia & The rest

በኢትዮጵያ 665 ተጨማሪ ሰዎች ኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው፤ 640 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል
***************
ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 6 ሺህ 569 የላቦራቶሪ ምርመራ 665 ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 87 ሺህ 834 ደርሷል።

በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 640 ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 41 ሺህ 628 ሆኗል።

ባለፉት 24 ሰዓታት በኮሮናቫይረስ የ12 ሰዎች ህይወት ማለፉ መረጋገጡን ተከትሎ በበሽታው የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 337 ደርሷል።

በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ ካለባቸው 44 ሺህ 867 ሰዎች መካከል 301 ያህሉ በጽኑ ሕክምና ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

በአገሪቱ እስካዛሬ ድረስ በአጠቃላይ ለ1 ሚሊዮን 383 ሺህ 649 ሰዎች የኮሮናቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።

@coronainethiopia