Get Mystery Box with random crypto!

በኢትዮጵያ 712 ተጨማሪ ሰዎች ኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው፤ 858 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል ******* | Coronavirus in Ethiopia & The rest

በኢትዮጵያ 712 ተጨማሪ ሰዎች ኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው፤ 858 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል
***************
ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 7 ሺህ 121 የላቦራቶሪ ምርመራ 712 ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 86 ሺህ 430 ደርሷል።

በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 858 ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 40 ሺህ 165 ሆኗል።

ባለፉት 24 ሰዓታት በኮሮናቫይረስ የ7 ሰዎች ህይወት ማለፉ መረጋገጡን ተከትሎ በበሽታው የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 1312 ደርሷል።

በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ ካለባቸው 44 ሺህ 951 ሰዎች መካከል 230 ያህሉ በጽኑ ሕክምና ላይ መሆናቸው ተገልጿል።
በአገሪቱ እስካዛሬ ድረስ በአጠቃላይ ለ1 ሚሊዮን 370 ሺህ 095 ሰዎች የኮሮናቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።


@coronainethiopia