Get Mystery Box with random crypto!

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 582 ሰዎች ኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው፤ 403 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል ******* | Coronavirus in Ethiopia & The rest

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 582 ሰዎች ኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው፤ 403 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል
*******************

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 6 ሺህ 344 የላቦራቶሪ ምርመራ 582 ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 85 ሺህ 718 ደርሷል።

በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 403 ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 39 ሺህ 307 ሆኗል።

ባለፉት 24 ሰዓታት በኮሮናቫይረስ የ4 ሰዎች ህይወት ማለፉ መረጋገጡን ተከትሎ በበሽታው የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 305 ደርሷል።

በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ ካለባቸው 45 ሺህ 104 ሰዎች መካከል 237 ያህሉ በጽኑ ሕክምና ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

በአገሪቱ እስካዛሬ ድረስ በአጠቃላይ ለ1 ሚሊዮን 363 ሺህ 974 ሰዎች የኮሮናቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።

@coronainethiopia