Get Mystery Box with random crypto!

Pm. D.r Abiy Ahmed Ali. ጉዟችን ኢትዮጵያን ወደ ቀጣዩ ከፍታ ማሻገር ነው። የዐድዋ | Ethio 19

Pm. D.r Abiy Ahmed Ali.

ጉዟችን ኢትዮጵያን ወደ ቀጣዩ ከፍታ ማሻገር ነው። የዐድዋን ሪከርድ መስበር ነው። እንደምንችል አረጋግጠናል፤ እንደምንችል ማሳየት ግን ይቀረናል። ሰንኮፎቻችን ሁሉ ቀስ በቀስ እየተነቀሉና መንሳፈፊያ ክንፎቻችን እየተዘረጉ ሲመጡ ያለ ጥርጥር ዘመናችን ብሩኅ ይሆናል፤ ጉዞውን ጀምረናል። ወደ ዐድዋ መድረሻው መንገድ ፈታኝ ነበር፤ የዐድዋ ድል ግን ጣፋጭ ነው። ወደ ብልጽግና መድረሻ መንገዳችን ፈታኝ ይሆን ይሆናል። ብልጽግናችን ግን እንደ ዐድዋ ሁሉ አይቀሬ ድል ነው። ኢትዮጵያ ከዐድዋ በታች አትወርድም። ከዐድዋ በላይ ወዳለው ከፍታ ደግሞ አንድ ሆነን እኛ እናወጣታለን።

መልካም የድል በዓል ለሁላችንም ይሁን።

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትሩር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
የካቲት 22፣ 2013 ዓ.ም

Link
@coronaethiopiaa @coronaethiopiaa