Get Mystery Box with random crypto!

እነ አቶጃዋር መሃመድ ላንድ ማርክ ሆስፒታል ተወሰዱ ! እነ አቶ ጃዋር መሃመድ ፣ አቶ በቀለ ገር | Ethio 19

እነ አቶጃዋር መሃመድ ላንድ ማርክ ሆስፒታል ተወሰዱ !

እነ አቶ ጃዋር መሃመድ ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ደጀኔ ጣፋ፣ አቶ ሃምዛ ቦረና ዛሬ ጥዋት ላንድ ማርክ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የኦሮሞ የፖለቲካ እስረኞች ጠበቆች ቡድን አሳውቋል።

ትላንት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በአቶ ጃዋር ፣ አቶ በቀለ ፣ በአቶ ሀምዛ እና አቶ ደጀኔ የህክምና ጉዳይ ላይ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ በመሻር ቀደም ሲል የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ባዘዘው መሰረት ወደ ላንድማርክ ሆስፒታል እንዲወስዱ ትዕዛዝ መስጠቱን ይታወሳል።

በረሃብ አድማ ከ30 ቀናት በላይ የሆናቸው እነ አቶ ጃዋር መሃመድ ዛሬ ጥዋት በገቡበት በላንድ ማርክ ሆስፒታል አከባቢ ከፍተኛ የሆነ የጸጥታ ሀይል እነደተሰማራ ተዘግቧል።

PHOTO : Addis Standard

Join our channel
@coronaethiopiaa @coronaethiopiaa