Get Mystery Box with random crypto!

የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ፦ ዛሬ የካቲት 2/2013 ዓ.ም ከቀኑ 6፡20 ጀምሮ 'ሰበር ዜና | Ethio 19

የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ፦

ዛሬ የካቲት 2/2013 ዓ.ም ከቀኑ 6፡20 ጀምሮ 'ሰበር ዜና Breaking News' በሚል በማረሚያ ቤት በሚገኙት በአቶ ጃዋር መሃመድ እና በሌሎችም ግለሰቦች ዙሪያ የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ኮሚሽነር ደብዳቤ እንደጻፈ ተደርጎ በተለያዩ ማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተናፈሰ ያለው ጉዳይ ፍጹም ስህተት እና ከእውነት የራቀ መሆኑን የፌዴራል ማረሚያ ቤት ባወጣው አጭር መግለጫ አሳውቋል።

በደብዳቤው የተካተቱ ቁጥር ፣ ቀን ፣ ሎጎ እንዲሁም ማህተም በፎቶ ሾፕ የተቀነባበሩ እንጂ ከፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን መዝገብ ቤት የወጣ ደብዳቤ እንዳልሆነ ማረሚያ ቤቱ ያረጋግጣል ብሏል።