Get Mystery Box with random crypto!

የአማራ ክልል መንግስት ሰንደቅ አላማውን ሊቀይር ነው የአማራ ክልል ብሄራዊ አስተዳደር፤ ከሁለት | Addis Merkato

የአማራ ክልል መንግስት ሰንደቅ አላማውን ሊቀይር ነው

የአማራ ክልል ብሄራዊ አስተዳደር፤ ከሁለት አስርት አመታት በላይ የተጠቀመበትን ሰንደቅ አላማ ሊቀይር መሆኑ ተገለፀ፡፡

የሚቀየረው የሰንደቃላማ አይነትና፤ የሚቀየርበት ጊዜ ከአማራ ህዝብ ጋር በሚደረግ ውይይት እንደሚወሰን የክልሉ የኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች አሳውቋል፡፡

የክልሉ የኮምዩኒኬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶግዛቸው ሙሉነህ፤ የአማራ ህዝብ በቀድሞው የህወሃት አገዛዝ ፖለቲካዊ፣ ማህበረሰባዊና፣ ኢኮኖሚያዊ ጫናዎች እንደነበሩበት ገልፀው፤ ለምሳሌነትም የተለያዩ ከህገ መንግስቱ ጀምሮ፤ በክልሉ የሚገኙ ሐውልቶችና ሰንደቃላማው የሚያመለክተው የታሪክ ትርክት፤ የአማራን ህዝብ ስነ ልቦና የሚገልፅ አይደለም ብለዋል፡፡

ዳይሬክተሩ ክልሉ የሃውልቶች ማስተካከያ እያደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ሰንደቅ አላማውም ምንም አይነት ታሪካዊ ዳራ የሌለውና፤ ሆን ተብሎ ፖለቲካዊ ጫና ለማሳደር የተቀመጠ ነው የተባለ ሲሆን፤ ፖለቲከኞችም ከህዝቡ ጋር የሚያስማማ፤ የአንድነትና የመቻቻልን የሚያሳይ፤ እንዲሁም ለመጪው ትውልድ የሚጠቅም ስራ ሰርተው ማለፍ እንዳለባቸው ም ተመልክቷል፡፡

ህብረተሰቡ በተለያዩ መድረኮች ሰንደቅ አላማው እንዲቀየር፤ ሲያቀር የቆየ በመሆኑ፤ ከህዝቡ ጋርና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን፤ ለጊዜው የክልሉን ህገ መንግስት ሳይቀየር በአዋጅ የክልሉን ሰንደቅ አላማ መለወጥ ይቻላል ተብሏል፡፡

Via waltatv

#የዛሬ_መረጃ #አዲስመረጃ #ትኩስ_መረጃ