Get Mystery Box with random crypto!

ነሐሴ 23 ቀን 2014 ዓ.ም 'አየር ኃይሉ መክፈል የሚገባውን መስዋዕትነት ሁሉ ከፍሎ ኢትዮጵያ | የኮማንዶና አየር ወለድ ኃይል ጠቅላይ መምሪያ _ Commandos and Airborne Head Quarter

ነሐሴ 23 ቀን 2014 ዓ.ም

"አየር ኃይሉ መክፈል የሚገባውን መስዋዕትነት ሁሉ ከፍሎ ኢትዮጵያ ታፍራና ተከብራ እንድትኖር ለማድረግ በላቀ የዝግጁነት ደረጃ ላይ ይገኛል።"
፦ ሌተናል ጀኔራል  ይልማ መርዳሳ

የኢፌዲሪ አየር ኃይል አካዳሚ በኤሌክትሮኒክስ፣ በአውሮፕላን አካል እና ሞተር ጥገና እንዲሁም በመሰረታዊ የአቪዬሽን ሙያ  ያሰለጠናቸውን የሰራዊት አባላት አስመርቋል።

በምርቃ ስነ -ስርዓቱ ተገኝተው በትምህርታቸው ብልጫ ላመጡ ሰልጣኞች ሰርተፍኬትና የማበረታቻ ሽልማት በመስጠት መልዕክት ያስተላለፉት የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ይልማ መርዳሳ ሲሆኑ አየር ኃይሉ ከሀገራዊ ለውጡና  ከተቋማዊ ሪፎርሙ በኋላ  የዝግጁነት አቅሙን ለማሳዳግ በሰው ኃይል ግንባታ፣ በዘመናዊ ትጥቆች እና ቴክኖሎጂ ብሎም ሰፋፊ የውጊያ መሰረተ ልማቶችን በማሟላት በትኩረት መስራት መቻሉን ገልፀዋል።

ተመራቂዎች  ያለንበትን  ወቅት በመረዳትና የተማራችሁትን ሙያ ወደ ተግባር በመቀየር ሀገራዊ ግዴታችሁን መወጣት አለባችሁ ሲሉ አሳስበዋል።

አየር ኃይላችን መከፈል የሚገባውን መስዋዕትነት ሁሉ በመክፈል ኢትዮጵያ ታፍራና ተከብራ እንድትኖር ለማድረግ  በላቀ የዝግጁነት ደረጃ ላይ ይገኛል ሲሉም አረጋግጠዋል ።

ለታላቅ ሀገር ታላቅ ተቋም በመገንባት ብሎም  ብቃትና ጥራት ያላቸውን ባለሙያዎችን በማፍራትና የኢትዮጵያን ጠላቶች ድባቅ በመምታት አየር ኃይሉ የጀግኖች መፍለቂያ  መሆኑን በተግባር እያስመሰከረ እንደሚገኝም ዋና አዛዡ ተናግረዋል ።

የኢፌዲሪ አየር ኃይል አካዳሚ አዛዥ ኮ/ል ገዛኸኝ ነጋሽ በበኩላቸው በአስተሳሰብና ክህሎት ብቁ የሆነ የሰው ኃይል በመፍጠር ዘመኑ የሚጠይቀውን ዕውቀት መሸከም የሚችል ፓይለትና ቴክኒሽያን እንዲሁም ሌሎች ሙያተኞችን በማፍራት  በአካዳሚው በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ገልፀዋል።

የአካዳሚ አዛዡ አክለውም በቀጣይ ኮሌጁን በቴክኖሎጂ ይበልጥ በማዘመን ከአፍሪካ ቀዳሚ የአቪዬሽን ተቋም ለማድረግ በትጋት እየሰራን እንገኛለን ብለዋል ።

ከተመራቂ ሙያተኞች መካከል አንዳንዶች በሰጡት አስተያየት ዘመኑ የሚጠይቀውን የአቪዬሽን እውቀት መቅሰማቸውን ጠቁመው በዚህም የሚጠበቅባቸውን ሁሉ በማድረግ ሀገራዊ ግዳጃቸውን በብቃት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ቤተሰብ ይሁኑ!

https://t.me/CommandoAndAirborneHeadQurter