Get Mystery Box with random crypto!

የኮማንዶና አየር ወለድ ኃይሎች የጦር ሜዳ ውሎዎች - Commando and Air Borne Battleships

የቴሌግራም ቻናል አርማ commando_and_airborne_battleship — የኮማንዶና አየር ወለድ ኃይሎች የጦር ሜዳ ውሎዎች - Commando and Air Borne Battleships
የቴሌግራም ቻናል አርማ commando_and_airborne_battleship — የኮማንዶና አየር ወለድ ኃይሎች የጦር ሜዳ ውሎዎች - Commando and Air Borne Battleships
የሰርጥ አድራሻ: @commando_and_airborne_battleship
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.35K
የሰርጥ መግለጫ

Addis abeba Ethiopia

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-08 09:57:39
ፎቶ ፦ የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የአመቱ ምርጥ ተጫዋቾች እንዱሁም አሰልጣኝ ሽልማት ትላንት ተካሂዷል።

አሸናፊዎቹ ፦

የጅማ አባ ጅፋር ወጣቱ ግብ ጠባቂ አላዛር ማርቆስ የአመቱ ምርጥ ወጣት ተሸላሚ። የ105 ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት አግኝቷል።

ዶ/ር ሀይለየሱስ ባዘዘው የአመቱ ምርጥ ዳኛ በመባል የተመረጠ ሲሆን 105 ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶለታል።

የቅዱስ ጊዮርጊስ ግብ ጠባቂ ቻርለስ ሉክዋጎ የውድድር ዓመቱ ምርጥ ግብ ጠባቂ በመባል 150ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቶለታል።

የከፍተኛ ግብ አግቢነት በአስራ ስድስት ግቦች ያሸነፈው ይገዙ ቦጋለ የ 200,000ሺህ ብር ተሸላሚ ሆኗል።

የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ የአመቱ ምርጥ አሰልጣኝ በመባል አሸንፏል። የ200 ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶለታል።

የቅዱስ ጊዮርጊሱ የመሐል ሜዳ ተጫዋች ጋቶች ፓኖም የአመቱ ምርጥ በመባል ተመርጧል። 250ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶለታል።

Join : ለተጨማሪ መረጃዎች ከታች ያሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ። ቤተሰብ ይሁኑ! ቴሌግራም፦ #ሼር #join https://t.me/Commando_and_AirBorne_Battleship
200 views06:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 08:13:35
ለተጨማሪ መረጃዎች ከታች ያሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ። ቤተሰብ ይሁኑ! ቴሌግራም፦ #ሼር #join https://t.me/Commando_and_AirBorne_Battleship
197 views05:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 07:54:33
#ሺንዞ_አቤ

የቀድሞው የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ የግድያ ሙከራ ተደረገባቸው

አቤ በጥይት ተመተው ሆስፒታል ገብተዋል
የቀድሞው የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ የግድያ ሙከራ ተደረገባቸው።

ሺንዞ አቤ በምዕራባዊ ጃፓን በሚገኝና ናራ በተባለ ከተማ ጎዳና ላይ ንግግር በማድረግ ላይ ሳሉ ከበስተጀርባቸው በተተኮሰ ሁለት ጥይት ደረታቸውን ተመተው ሆስፒታል ገብተዋል።

በተኩሱ አቤ ለህይወታቸው በሚያሰጋ የጤና ሁኔታ ላይ መውደቃቸውን የዘገቡ የሃገሪቱ ብዙሃን መገናኛዎች የ41 ዓመቱ የግድያ ሙከራው ፈጻሚ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል ብለዋል።
አቤ በተመቱበት ጊዜ ለሊበራል ዲሞክራቲክ ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳን በማድረግ ላይ ነበሩ።

'አቤኖሚክስ' በሚባል የምጣኔ ሃብት ፍልስፍና የሚታወቁት ሺንዞ በጃፓን የመሪነት ታሪክ ሀገሪቱን ለረጅም ጊዜ ያገለገሉ ቀዳሚው ሰው ናቸው።

በቀድሞው የጃፓን ጠቅላይ ሚንስትር ሺንዞ አቤ ላይ የደረሰውን የግድያ ሙከራ ተከትሎ የበርካታ ሀገራት መሪዎች ሀዘናቸውን እየገለፁ ነው።

ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም፦ #ሼር #join
https://t.me/Commando_and_AirBorne_Battleship
201 viewsedited  04:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 21:00:16
“ሄሮን ቲፒ (Heron TP)” ድሮን

“ሄሮን ቲፒ” አደገኛው የእስራኤል የውጊያ ድሮን

በሰዓት በሰዓት 370 ኪ.ሜ የሚጓዘው ድሮኑ ለ30 ሰዓታት አየር ላይ መቆየት ይችላል።

“ሄሮን ቲፒ (Heron TP)” ድሮን የእስራኤል አየር ኃይል ከታጠቃቸው አደገኛ የአውደ ውጊያ መሳሪያዎች ውስጥ በቀዳሚነት ዪጠቀስ ነው።

በእስራኤል ኤሮስፔስ ኢንዱስትሪ የተመረተው ድሮኑ በተለያዩ ወታደራዊ ትልእኮዎች ላይ መሳተፍ ብቃቱን ማስመስከር እንደቻለ ይነገርለታል።

ሄሮን ቲፒ ድሮንን ከእስራኤል በተጨማሪ እንደ ጀርመን፣ አውስትራሊያ፣ ፈረንሳይ፣ ደቡብ ኮሪያ እና ካናዳ ያሉ ሀገራት እንደታጠቁጥ ይነገራል።

“ሄሮን ቲፒ (Heron TP)” ድሮንን ምን የተለየ ያደርገዋል…ʔ

ሄሮን ቲፒ ድሮን በየትኛውም አይነት የአየር ፀባይ ለ30 ሰዓታት ያክል መስራ ይችላ የተባለ ሲሆን፤ በሰዓት 370 ኪሎ ሜትር ፍጥነት መጓዝ እንደሚችልም ተነግሯል።

ድሮኑ ለተልዕኮ በሚሰማራበት ወቅት አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ከባህር ጠለል በላይእስከ 45 ሺህ ጫማ ድረስ ከፍ ብሎ በመብረር ከራዳር እይታ ውጪ ጥቃት መሰንዘር ይችላል።

ያለ ሰዎች ንክኪ በራሱ መነሳት እና ማረፍ የሚችው ድሮኑ፤ የሳተላይተ ግንኙነት ቴክኖሎጂ ስለሚጠቀምም ከመቆጣጠሪያ ጣያው ከ1 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ ርቆ መጓዝ ይችላ ተብሏል።


ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም፦ #ሼር #join
https://t.me/Commando_and_AirBorne_Battleship
299 viewsedited  18:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 20:37:37
ኢትዮጵያ በዩኔስኮ የማይዳሰሱ የባህል ቅርሶች በይነ መንግስታት ኮሚቴ አበል ሆና ተመረጠች።

ኢትዮጵያ የማይዳሰሱ የባህል ቅርሶች በይነ-መንግስታት ኮሚቴ አባል ሆና ተመርጣለች። ምርጫው የተካሄደው እ.ኤ.አ. ከጁላይ 5 እስከ 7 ቀን 2022 ዓ.ም. በመካሄደው የዩኔስኮ የማይዳሰሱ ቅርሶች ጥበቃ ኮንቬንሽን አባል አገራት 9ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ነው።

ኢትዮጵያ አባልነት ዘመኗ በዩኔስኮ የሚመዘገቡ የማይዳሰሱ ቅርሶች ዝርዝር ሚዛናዊና የዓለማችንን ውበት እና ብዝሃነት የሚያንፀባርቁ እንዲሆኑ ትሰራለች ሲል የቅርስ ባለሥልጣን አስታውቋል።

ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም፦ #ሼር #join
https://t.me/Commando_and_AirBorne_Battleship
273 viewsedited  17:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 15:50:57
#BorisJhonson

• ጠ/ሚ ቦሪስ ጆንሰን በገዛ ፍቃዳቸው የጠቅላይ ሚኒስትርነት ስልጣናቸውን ለቀቁ።

• አዲስ ጠ/ሚ እስኪሰየም ቦሪስ ጆንሰን ቦታው ላይ ይቆያሉ።

ከምክር ቤት እና ከካቢኔ ሚኒስትሮቻቸው ድጋፍ ማግኘት ያልቻሉት የብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስተር ቦሪስ ጆንሰን ከወግ አጥባቂ ፓርቲያቸው መሪነት እንዲሁም ከጠ/ሚ ስልጣናቸው ለቀቁ።

ለፓርቲው መሪነት የሚደረገው ፉክክር በቅርቡ የሚደረግ ሲሆን በቀጣይ ዓመት ጥቅምት ወር ላይ ደግሞ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስተር ይሰየማል ተብሏል።

አስከዚያው ድረስ ግን ቦሪስ ጆንሰን በአገሪቱ የጠቅላይ ሚኒስትር መንበር ላይ ይቀጥላሉ።

ጆንሰን በአመራራቸው ላይ በርካታ ትችቶች ሲቀርብባቸው ቆይቶ በርካታ ባለሥልጣኖቻቸው በፈቃዳቸው ሥልጣናቸውን ከለቀቁ በኋላ ነው ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሱት።

ቻንስለር ናዲም ዛሃዊን ጨምሮ ከፍተኛ ካቢኔ አባሎቻቸው “ በክብር የሥልጣን መንበራቸውን እንዲለቁ ” ለጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ጥያቄ አቅርበው ነበር።

ቦሪስ ጆንሰን ሥልጣን እንዲለቁ የቀረበላቸውን ጥያቄ እስከ ሐሙስ ረፋድ ድረስ ሳይቀበሉት ቆይተው ነበር ፤ ነገር ግን የፓርላማ አባሎቻቸውን ድጋፍ ማግኘት ሳይችሉ በመቅረታቸው በመጨረሻ ወስነዋል።

ሚኒስትሮቻቸው በገዛ ፈቃዳቸው ስልጣን በመልቀቃቸው እና የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ ከፓርላማ አባላት ማግኘት ያልቻሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ከፓርቲ መሪነትና ከጠ/ሚ የስልጣን መንበራቸው በፍቃዳቸው መልቀቃቸውን በይፋዊ ጋዜጣዊ መግለጫ አሳውቀዋል።

ከወራት በኋላ የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ቦታ ያስረክባሉ።

#SkyNews #BBC
ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም፦ #ሼር #join
https://t.me/Commando_and_AirBorne_Battleship
326 viewsedited  12:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 13:05:54
የቀጠለ ...

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከመሠረተ ልማት ግንባታ በተጨማሪ ሌሎች የሰራቸው ስራዎች ፦

የተሳካ አገልግሎት ለማቀረብ አንዲሁም የሙያ እና የክህሎት ሽግግርን ለማጠናከር ብቃት ያለው የአመራሮች ሰብስቦ አዋቅሯል።

የሰው ኃብቱን ወደ 500 ያሳደገ ሲሆን ከዚህም ውስጥ 320ዎቹ ኢትዮጵያዊያን ናቸው። በቀጣይም ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል የተውጣጡ ሠራተኞች እንዲኖሩት ለማድረግ እየሰራ ነው።

50 አዲስ ተመራቂ ተማሪዎችን መልምሎ ጊዜውን የዋጁ ኃሳቦችን እና መፍትሔዎችን ሊጠቁም የሚችሉ ዲጂታል የፈጠራ ክህሎት ያላቸው ኢትዮጵያዊያንን ለመፍጠር ጥረት እያደረገ ሲሆን ተጨማሪ 100 አዲስ ተመራቂዎችን ለመመልመል በልዩ ልዩ ክልሎች ውስጥ ካሉ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በትብብር እየሠራ ነው።

በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች ሊያዳርሱ የሚችሉ 29 አከፋፋዮችን በአቅራቢነት በመያዝ ድርጅቶቹ አቅማቸውን እንዲያጎለብቱ እየተሰራ ነው።

አገልግሎት መስጠት ለመጀመር ያዘጋጀነው ዕቅድ የችርቻሮ መደብሮችን እንዲያካትት በማድረግ በአቅርቦት ሰንሰለቱ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያዊ ድርጅቶች ጋር አጋርነት ለመፍጠር የሚያስችሉ ጨረታዎች አውጥቷል።

ማህበራዊ ኮንትራቱን ማዘጋጀት የቀጠለ ሲሆን 'ዲጂታልን በመጠቀም ሕይወትን የማሻሻል' ርዕዩን በሚያሳካ መንገድ ለዚህ መሠረት ለመጣል የሚያስችሉ እቅዶችን አውጥቷል።

#SafaricomEthiopia
ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም፦ #ሼር #join
https://t.me/Commando_and_AirBorne_Battleship
328 viewsedited  10:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 12:48:11
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ማብራሪያ ዋና ዋና ነጥቦች

የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች አክቲቪስቶች ግድያ ሲፈጸም አየሩን ይሞሉታል፤ ፖሊስ እርምጃ ሲወስድ ህጋዊ ነገር ሲከበር ግን የሉም፤

ሸኔ የኦሮሞ ቀንደኛ ጠላት ነው፤ ሸኔ ለማንም የማይመለሱ አውሬዎች ናቸው፤

ለምንድን ነው አውሬ የሆኑት የሚለው ጥናት ይፈልጋል፤ የፖለቲካ አላማ ግን የላቸውም፤

የሸኔ ዓላማው አገር ማፍረስ ነው፤

ሁለት ልጆችህን አገር ሊታደጉ ዘምተዋል ተብለው አባት በሸኔ ተገድለዋል፤

የመከላከያ ሰራዊት አመራሮች ቤተሰቦች ተገድለዋል፤ በመቶ የሚቆጠሩ አመራሮች ተገድለዋል፤

ሸኔ የኦሮሞ ተወካይ አይደለም፤ ቀንደኛ ጠላት ነው፤ በሸኔ ምክንያት ወለጋ ውስጥ ልማት ቆማል፤

ይሄንን ጠላት የሁላችንም ጠላት ነው ብለን ከተነሳን እናጠፋዋለን፤

ለሸኔ የሚራራ የሚያዝን የተለየ ስሜት የለንም፤ እንደ ሸኔ ያሉ ኃይሎች ዋና ፍላጎታቸው ፓርላማው ሚዲያው ዓለም ስለእነሱ እንዲያወራ ነው፤

ለእናንተ ባንናገርም በእያንዳንዱ ደቂቃ እየተዋጋናቸው ነው፤

ሁሉም ኢትዮጵያዊ በእኩልነት የሚኖሩባት ኢትዮጵያን ለመመስረት ነው ፍላጎታችን እየሰራን ያለነወም ለዚያ ነው፤

ጽንፈኞች በየትኛው ሰፈር ይደራጁ ሁለት መርዝ አላቸው፤ አንደኛው የእኔ ብቻ ጥሩ ነው የሚለው ነው፤ ሁለተኛው በጣም የበዛ የራስ ሀዘኔታ፤ የነገሮች ሁሉ ማዕከል ራስን ብቻ ማድረግ ነው፤

ጽንፈኝነት ዓለምን አልጠቀመም ኢትዮጵያን አይጠቅምም፤ መግረፍና ማፈን ከብልጽግና ጋር አብሮ አይሄድም፤
ለጠላት ተገማች አንሁን፤
ተጨማሪ ይዘን እንመለሳለን

ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም፦ #ሼር #join
https://t.me/Commando_and_AirBorne_Battleship
292 viewsedited  09:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 12:16:20
ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም

የኮማንዶና አየር ወለድ ኃይል በዘመቻ ሙያ ያሰለጠናቸውን የሰራዊት አባላት አስመረቀ፡፡

በምርቃ ፕሮግራሙ ላይ በመገኘት ለተመራቂዎች የስራ መመሪያ ንግግር ያደረጉት የኮማንዶና አየር ወለድ ኃይል ስነልቦና ግንባታ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮሎኔል ገዛኸኝ ነጋሽ ናቸው፡፡

የዘመቻ ሙያተኛ እራሱን አብቅቶ ሌሎችን በማብቃት ሠራዊቱን ለድል የሚያበቃ እና በግዳጅ ውስጥ ወሳኝ ሚናን የሚጨወት መሆኑን በማስገንዘብ ተመራቂዎቹም በዚህ ደረጃ ያለባቸውን ኃላፊነት ተገንዝበው የተጣለባቸውን ሙያዊ ግዴታ በብቃት እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

የኮማንዶና አየር ወለድ ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ ኮሎኔል ኤፍሬም ዘገዬ በበኩላቸው ስልጠናው በክፍሉ ተደማሪ አቅምን ለመፍጠር ያለመ መሆኑን በመግለፅ ውጤቱ በሚፈለገው ደረጃ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ከተመራቂዎች መካከልም መሠረታዊ ወታደር አቤል ታደሰ እና መሠረታዊ ወታደር አለማየሁ ግዛቸው በሰጡት አስተያየት በስልጠና ቆይታቸው በቶፖግራፊ እና አጠቃላይ የዘመቻ ስራ በቂ እውቀት ማግኘታቸውን ተናግረው በሰለጠኑበት ሙያም በሰንደቅ አላማው ፊት በፈፀሙት ቃለ መሀላ መሠረት ግዳጃቸውን በቁርጠኝነት እንደሚወጡ ገልፀዋል፡፡

ለተጨማሪ መረጃዎች ከታች ያሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ።
ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም፦ #ሼር #join
https://t.me/Commando_and_AirBorne_Battleship
284 views09:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 12:05:32 ሳፋሪ ኮም ኢትዮጵያ ከነሀሴ ጀምሮ የቴሌኮም አገልግሎት መስጠት ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ

ድርጅቱ የመጀመሪያ አገልግሎቱን በድሬዳዋ ከተማ እንደሚጀምር ገልጿል። እስከ ሚያዝያ 2015 ዓ.ም ድረስ ለ25 ከተሞች የቴሌኮም አገልግሎት ለመስጠት እቅድ ማስቀመጡን አስታውቋል።
https://am.al-ain.com/article/new-telecom-service-to-start-in-ethiopia

ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም፦ #ሼር #join
https://t.me/Commando_and_AirBorne_Battleship
256 viewsedited  09:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ