Get Mystery Box with random crypto!

እናስታውስዎ! ቀነ ገደቡ በመጠናቀቅ ላይ ነው! የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እ.ኤ.አ ኦገስት 27፣ 2 | Commercial Bank of Ethiopia - Official

እናስታውስዎ!
ቀነ ገደቡ በመጠናቀቅ ላይ ነው!
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እ.ኤ.አ ኦገስት 27፣ 2021 ጀምሮ ሁሉም ባንኮች የደንበኞቻቸውን መረጃ በአግባቡ አጣርተው እንዲያደራጁ ያወጣውን መመሪያ ተከትሎ ባንካችን የደንበኞቹን መረጃ የማጥራትና የማደራጀት ተግባር ሲያከናውን ቆይቷል፡፡ በአሁኑ ጊዜም አብዛኞቹ ደንበኞቻችን መረጃቸውን ወቅታዊ ማድረግ ችለዋል።
መረጃን የማጥራትና የማጠናቀር ስራው ብሔራዊ ባንክ ባወጣው ቀነ ገደብ ሊጠናቀቅ ቀናት የቀሩ ሲሆን፣ የተወሰኑ የባንካችን ደንበኞች አሁንም መረጃችሁን ወቅታዊ አለማድረጋችሁን መመልከት ችለናል፡፡ ስለሆነም መረጃችሁን ወቅታዊ ያላደረጋችሁ ደንበኞቻችን የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ በመያዝ አቅራቢያችሁ በሚገኝ ቅርንጫፍ ተገኝታችሁ መረጃችሁን ወቅታዊ እንድታደርጉ እናስታውሳለን፡፡
በመጨረሻ ቀናት የሚፈጠርን አላስፈላጊ መጨናነቅ ለማስቀረትም ከአሁኑ ወደ ባንካችን እንድትመጡ  ለማስታወስ እንወዳለን፡፡
መረጃቸውን በተሰጠው የጊዜ ገደብ ማቅረብ ያልቻሉ የባንካችን ደንበኞች የሞባይል ባንኪንግ፣ የኢንተርኔት ባንኪንግ እና የካርድ ባንኪንግ አገልግሎቶች በጊዚያዊነት የሚቋረጥባቸው ሲሆን፣ ሒሳባቸውን ማንቀሳቀስ የሚችሉት በአካል የባንኩ ቅርንጫፍ በመገኘት ብቻ መሆኑን እንገልጻለን።
 
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ