Get Mystery Box with random crypto!

የቃለ መጠይቅ ፈተና ጥሪ ለደብረ ብርሀን ዲስትሪክት ጀማሪ የባንክ ባለሙያ (Bank Trainee) | Commercial Bank of Ethiopia - Official

የቃለ መጠይቅ ፈተና ጥሪ
ለደብረ ብርሀን ዲስትሪክት ጀማሪ የባንክ ባለሙያ (Bank Trainee) አመልካቾች
=====================
በኢትዮዽያ ንግድ ባንክ ደብረ ብርሃን ዲስትሪክት ለጀማሪ የባንክ ባለሙያ (Bank Trainee) ክፍት የሰራ ቦታ አመልክታችሁ ታህሳስ 23 ቀን 2014 ዓ.ም የፅሁፍ ፈተና የወሰዳችሁና ዉጤታችሁ 45 እና ከዛ በላይ ለሆነ ተፈታኞች ሐሙስ ሚያዝያ 27 እና ዓርብ ሚያዝያ 28 ቀን 2014 ዓ.ም የቃለ መጠይቅ ፈተና ይሰጣል፡፡

የቃለ መጠይቅ ፈተናውን የምትወስዱ አመልካቾች ስም ዝርዝር በባንካችን የቴሌግራም ገጽ ላይ የተቀመጠ ሲሆን፣

1ኛ) ከተራ ቁጥር 1-100 ያላችሁ ሚያዝያ 27 ቀን 2014 ዓ.ም

2ኛ) ከተራ ቁጥር 101-186 ያላችሁ ሚያዝያ 28 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ደብረ በርሃን ከተማ ፃድቃኔ ህንፃ 2ኛ ፎቅ በመገኘት ፈተናውን እንድትወስዱ እናሳስባለን፡፡

ለቃለ መጠይቅ ፈተናው ያለፋችሁ አመልካቾች ስም ዝርዝራችሁን ከተያያዘው ዶክመንት መመልከት ትችላላችሁ፡፡