Get Mystery Box with random crypto!

ከ እለታት በአንዱ ቀን ነው ኢትዮጵያ ቡና ከመከላከያ ጋር የ ሲቲ ካፕ ዋንጫ የደረጃ ጨዋታ ለማየ | አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና - አደገኞቹ

ከ እለታት በአንዱ ቀን ነው ኢትዮጵያ ቡና ከመከላከያ ጋር የ ሲቲ ካፕ ዋንጫ የደረጃ ጨዋታ ለማየት ፉዋ ፍክት ብዬ ከቤት ወጣው።ገና ከቤቴ ብዙም ሳልርቅ ነበር የ ከተማ ተቀናቃኛችን የ እነ እገሌ ደጋፊ የነበሩት የ ሰፈራችን ልጆች እያዩኝ ተሳሳቁ እፈር እሄን ማልያ ስታረግ አሉኝ ያ ማልያ ማለት ለኔ ክብሬ ኩራቴ መሆኑ አልገባቸውም ነበር።አንዱ ቀጠለና ምን አቃጠለህ የ ሸገር ድምቀት የሆነው በዋንጫ የተሞላው የኛ ቲም ነው ና ወደኛ ተቀላቀል አለኝ አንድ መልስ መልሼለት ነበር መንገዴን የቀጠልኩት እነሱም ዝም ያሉት"እኔ በኢትዮጵያ ውስጥ ለ ክለቡ ሙዋች እና በሽፈትም በ አሸናፊነትም እስከ ጥግ መስዋት የሚከፍለው የ 12 ለባሹ የ ኢትዮጵያ ቡና ደጋፊ ነኝ እናቴን እደማልለውጣት ቡንዬንም አልውጠውም " ነበር መልሴ እነሱ የማይገባቸው ለኛ ግን የሚገባን ጥልቅ የሆነ ፍቅር የተሞላበት ክለብ አለኝ ቡና ቅኔ ነው ለተፈቀደለት ብቻ የሚፈታ ቡና ፍቅር ነው ለዘላለም ላይሻር በልባችን ያደገ ለዘላለም የሚኖር ጥልቅ ፍቅር ወዳጄ እመነኝ በምንም ተአምር አንገትህን የምትደፋበት ቲም አደለም እርግጥ ነው ውጤት የለም ግን እኛ እደነሱ ውጤት ሲጠፋ ማልያችንን አውልቀን አንደብቀውም ምክንያቱም ማልያችን ክብራችን ነው ማንነታችን ነው መገለጫችን ነው አሁን ላይ ሁሉም የ 12 ለባሹ የ ኢትዮጵያ ቡና ደጋፊ በጉጉት የሚጠብቀው መስከረም 29 በሚደረገው 6ተኛው ዙር ቤተሰባዊ እሩጫ ላይ በ ህብረት የ ክለቡን ስም እየጠራ በሸገር ጎዳናዎች ላይ ደምቆ ለመዋል ጊዜውን እየተጠባበቀ ነው ያቺን ቀን ያቅርብልን!!!


ኢትዮጵያዊ ቡና ከ ክለብ በላይ ነው

ለማንኛው ሀሳብና አስተያየት @Ljdavaa ማድረስ ትችላላችሁ መልካም ቀን

አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ
@coffeefc
@coffeefc