Get Mystery Box with random crypto!

ነገረ-ክርስቶስ ሲፈተሽ

የቴሌግራም ቻናል አርማ christolgycritic — ነገረ-ክርስቶስ ሲፈተሽ
የቴሌግራም ቻናል አርማ christolgycritic — ነገረ-ክርስቶስ ሲፈተሽ
የሰርጥ አድራሻ: @christolgycritic
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 864
የሰርጥ መግለጫ

እንዴት ናችሁ የነገረ ክርስቶስ ቻናል ታዳሚያን በዚህ ቻናል የምንማማረው ኢንሻአላህ ክርስቲያን ወገኖች በኢየሱስ ዙሪያ በሚያነሷቸው እያንዳንዱ ነገሮች ነው። ምሳሌ:--ኢየሱስን አምላክ ያደርጋሉ ብለው የሚነሷቸውን የባይብል ጥቅሶች ከታሪካዊ አመጣጣቸው ስለ ስላሴ ስለ ስቅለት ስለ አፈጣጠሩ ወዘተ....
ብዙ ትምህርቶች እንማማራለን ኢንሻአላህ እናንተ ቻናሉን ሸር በማድረግ ለወገኖች የሂዳያ ስበብ እንሁን።

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-04-23 23:12:45 ከላይ ያለውም ጹሁፍ በድምጽ
ተብራርቷል

አድምጡ ሸርም አድርጉ ለወገኖች

በወንዲም አብዱል ፈታህ ኸድር


ነገረ-ክርስቶስ ሲፈተሽን ቻናል ይቀላቀሉ
@Christolgycritic
445 views20:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-22 13:46:52 አዲስ ትምህርት በዩትዩብ ቻናላችን ላይ ጳውሎስ ማን ነው? ክፍል ሁለት ተለቆላችኋል ገብታችሁ ኮምኩሙ፦





ሼርና ሰብስክራይብ ማድረግዎን አይርሱ!
366 views10:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-10 03:28:45 አዲስ ትምህርት በዩትዩብ ቻናላችን ተለቆላችኋል ገብታችሁ ኮምኩሙ፦




ሼርና ሰብስክራይብ ማድረግዎን አይርሱ!
493 views00:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-07 13:25:31 ይቀጣን ይሆን?


ፈጣሪ እዚህ ምድር ላይ ስንኖር በብቸኝነት እርሱን እንድንገዛው ይፈልጋል፤ ለዚያም ነው ነቢያቶችን በየህዝቡ እየላከ ከጥፋት መንገድ(ገሃነም እንዳይገቡ) የታደጋቸው። አዎን አምላክ የግዴታ እንድናመልከው ከፈለገ እንዲሁም እርሱን ማምለኩ ለእኛ መዳንና መጥፋት ወሳኝ ነገር ከሆነ፣ እንድናመልከው "አምልኩኝ" በማለት ቀጭን ትዕዛዝ መስጠት አለበት። ለምሳሌ እናውቀውና እናመልከው፣ እናስተውለው ዘንድ በግልፅ ሁኔታ እንዲህ ማለት አለበት፦

“እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦…… እኔም እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ በላቸው።”
— ዘጸአት 16፥11-12

“ታውቁና ታምኑብኝ ዘንድ እኔም እንደሆንሁ ታስተውሉ ዘንድ፥ እናንተ የመረጥሁትም ባሪያዬ ምስክሮቼ ናችሁ ይላል እግዚአብሔር፤ ከእኔ በፊት አምላክ አልተሠራም ከእኔም በኋላ አይሆንም።”
— ኢሳይያስ 43፥10

إِݧَّݧِي أَݧَا اݪݪَّهُ ݪَا إِݪَـٰهَ إِݪَّا أَݧَا ڣَاعْبُدْݧِي ۅَأَقِݦِ اݪصَّݪَاةَ ݪِذِكْڔِي

(ሱረቱ ጣሀ - 14)
«እኔ አላህ እኔ ነኝ ያለ እኔ አምላክ የለምና ተገዛኝ፡፡ ሶላትንም (በእርሷ) እኔን ለማውሳት ስገድ፡፡

ۅَݦَا أَڔْسَݪْݧَا ݦِن قَبْݪِكَ ݦِن ڔَّسُۅݪٍ إِݪَّا ݧُۅځِي إِݪَيْهِ أَݧَّهُ ݪَا إِݪَـٰهَ إِݪَّا أَݧَا ڣَاعْبُدُۅݧِ

(ሱረቱ አል-አንቢያ - 25)
ከአንተ በፊትም እነሆ "ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና" "ተገዙኝ" በማለት ወደርሱ የምናወርድለት ቢኾን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡

ካለበለዚያ ስለምን ጥፋተኛ እንባላለን? ስለምንስ ባልታዘዝነው ነገር እንቀጣለን? ሕመሙን ያልተናገረ መድሐኒቱ አይገኝለትምና! እውን ኢየሱስ አምላክ ከሆነ እኔ አምላክ ነኝ አምልኩኝ ለምን አላለም? እኔ ኢየሱስን ባላመልከው ምንድን ነው ሚጠብቀኝ? ገነት ወይስ ገሃነም? ገሃነም ከሆነስ እንዴት ሆኖ? አምልኩኝ ሳይለን እንዴት አመልከዋለሁ? "ቸር" ሲባል ለምን ቸር ትሉኛላችሁ? ቸር ከአንዱ አምላክ በቀር ቸር የለምና በማለት እርሱ አንዱ አምላክ እንዳልሆነ ነግሮን ሳለ! እንዴት እርሱን አምላክ ብዬ አመልከዋለሁ? "ሳይደግስ አይጣላም" እንዳሉት አበው! ስላላመለኩትስ ለምን ይቀጣኛል? ምክንያቱም እራሱን ከአንዱ አምላክ ውጭ ያለ ሰው መሆኑን ነግሮኝ ሳለ መቅጣቱ ፍትሃዊ ነውን? በእኔ ማመን ማለት በላከኝ ማመን ነው እንጂ "በእኔ አይደለም" ሲልስ ምን ማለቱ ነው? አሁንስ የላኪውን በብቸኝነት መመለክ ፈልጎ አይደለምን እንዲህ ማለቱ? ስለዚህ ኢየሱስ አምላካችሁ ነው እርሱን አምልኩ እያላችሁ አትስበኩና! በቃ! ምክንያቱም፦

1ኛ ኢየሱስን ማምለክ ግዴታ ስላልሆነና ያላመለከውም ሠው ቅጣት ስለሌለው።

2ኛ እርሱ ራሱ አይደለም መመለክን ሊፈልግ ቀርቶ እንደ ፍጡርነቱ መጠን የአንዱን አምላክ ክብር መጋፋት ስለማይፈልግ።

ሉቃስ 18
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁸ ከአለቆችም አንዱ፦ ቸር መምህር፥ የዘላለምን ሕይወት እንድወርስ ምን ላድርግ? ብሎ ጠየቀው።
¹⁹ ኢየሱስም፦ ስለ ምን ቸር ትለኛለህ? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ቸር ማንም የለም።

“ኢየሱስም፦ ስለ ምን ቸር ትለኛለህ? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ቸር ማንም የለም።”
— ማርቆስ 10፥18

“ኢየሱስም ጮኸ፥ እንዲህም አለ፦ በእኔ የሚያምን በላከኝ ማመኑ ነው እንጂ በእኔ አይደለም፤”
— ዮሐንስ 12፥44


አሁንም አቋሜ ይሄው ነው፤ አዎ! አላመልከውም! አላመልከውም! እኔ የማመልከው የኢየሱስን ብቸኛ አምላክ ብቻ ነው።

Brother Kedir Ibnu Muhammad


https://t.me/Christolgy_critic
551 views10:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-25 17:30:24 የጳውሎስ ነገር!
.
አንድ ባለፀጋ ሰው ወደ ኢየሱስ በመምጣት የዘላለም ህይወት ያገኝ ዘንድ ምን መልካም ነገር መስራት እንዳለበት እንደ ጠያቀው መፅሐፍ ቅዱስ ያወገናል፦

(የማቲዎስ ወንጌል19)
=
16 እነሆም፥ አንድ ሰው ቀርቦ። መምህር ሆይ፥ የዘላለምን ሕይወት እንዳገኝ ምን መልካም ነገር ላድርግ? አለው።
17 እርሱም። ስለ መልካም ነገር ለምን ትጠይቀኛለህ? መልካም የሆነ አንድ ነው፤ ወደ ሕይወት መግባት ብትወድ ግን ትእዛዛትን ጠብቅ አለው።
18 እርሱም። የትኞችን? አለው። ኢየሱስም። አትግደል፥ አታመንዝር፥ አትስረቅ፥ በሐሰት አትመስክር፥
19 አባትህንና እናትህን አክብር፥ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ አለው።

"""""ከአንቀፁ የምንረዳው ጭብጥ"""""

ኢየሱስ ለበላፀጋው ሰው ከሰጠው ምላሽ የምንረዳው ነጥብ ቢኖር ሰው የዘላለምን ህይወት ያገኝ ዘንድ ትዕዛዝን መጠበቅ እንዳለበት ነው።
--
ጳውሎስ ግን ፅድቅ በሕግ እንደማይገኝ በመናገር በኢየሱስ ተቃራኒ ሕግ ፋይዳ ቢስ መሆኑን ይናገራል፦

"በሕግ ልትጸድቁ የምትፈልጉ ከክርስቶስ ተለይታችሁ ከጸጋው ወድቃችኋል።(ገላቲያን5፥4)
.
ኢየሱስ ነው ወይስ ጳውሎስ ነው ትክክል? የሚለውን ለጊዜው እንተወውና፣ ጳውሎስ ከኢየሱስ አስተምህሮ ጋር መቃረኑን ክፉኛ ተቃውሞ የወረፉት እንዳሉ መፅሐፍ ቅዱስ ያወገናል፦

«አንተ ከንቱ ሰው፥ እምነት ከሥራ ተለይቶ የሞተ መሆኑን ልታውቅ ትወዳለህን?» (የያዕቆብ መልዕክት 2፥20)

ከንቱ መባልስ ያንሰዋል ስቶ አሳታቸው
https://t.me/Christolgy_critic
639 views14:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-25 11:11:42 ኢየሱስ በቁርአን እና በመጽሐፍ ቅዱስ

ብዙ ክርስቲያን ወገኖቻችን ለኢየሱስ በእሥልምና ምንም አይነት ክብር የለውም በማለት ይናገራሉ እውነታው ግን በምድር ላይ እንደ እሥልምና ለኢየሱስ ተገቢውን ክብር የሰጠው ምንም አይነት ሀይማኖት የለም።

የትኛው መጽሐፍ ነው ኢየሱስን ያከበረው?
መጽሐፍ ቅዱስ ወይስ ቁርአን?

እስቲ ነጥብ በነጥብ እንመልከት!!

>መጽሐፍ ቅዱስ
ኢየሱስ በከብት በረት የከብት ሽንት እና ኩበት በሞላበት ቦታ ተወለደ።
( ሉቃስ 2:7)

>ቁርአን ኢየሱስ የቴምር ዛፍ እና ወንዝ ባለበት ደስ በሚል ለምለም ቦታ ተወለደ
{ 19:23-24}

የትኛው መጽሐፍ ነው ለኢየሱስ ክብር የሰጠው?
እርሶስ የትኛውን መጽሐፍ ይከተላሉ?

>መጽሐፍ ቅዱስ
ኢየሱስን ተአምር ምንም ማድረግ ያቅተው ነበር።
( ማርቆስ 6:5)

>ቁርአን
ኢየሱስ እኔ ከጌታዬ ዘንድ በተአምር መጣሁ።
{ 3:49}

የትኛው መጽሐፍ ነው ለኢየሱስ ክብር የሰጠው?
እርሶስ የትኛውን መጽሐፍ ይከተላሉ?

>መጽሐፍ ቅዱስ
ኢየሱስን ራሱ የመረጣቸው ሐዋርያት ለጠላት አሳልፈው ሰጡት።
{ ዮሐንስ 13:21}

>ቁርአን
ኢየሱስን ሐዋርያት አሳልፎ አልሰጡት እንደውም እኛ ረዳቶችህ ነን አሉት።
{ 3:52}

የትኛው መጽሐፍ ነው ለኢየሱስ ክብር የሰጠው?
እርሶስ የትኛውን መጽሐፍ ይከተላሉ?

>መጽሐፍ ቅዱስ
ኢየሱስ እንዳይሞት ፈጣሪውን እያለቀሰ ብለምንም ፈጣሪ ግን ለጠላት አሳልፈው ሰጠው።
{ ማቴዎስ 27:35}

>ቁርአን
ኢየሱስ ሳይሰቀል ሳይገደል ፈጣሪው በክብር ወደ ሰማይ አስነሳው።
{ 4:157-159}

የትኛው መጽሐፍ ነው ለኢየሱስ ክብር የሰጠው? እርሶስ የትኛውን መጽሐፍ ይከተላሉ?

>መጽሐፍ ቅዱስ
ኢየሱስ እናቱን አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ እያለ እናቱን ይገላመጥ ነበር። { ዮሐንስ 2:4}

>ቁርአን
ኢየሱስ
«ለእናቴም ታዛዥ (አድርጎኛል)፡፡ ትዕቢተኛ እምቢተኛም አላደረገኝም፡፡
{ 19:32}

የትኛው መጽሐፍ ነው ለኢየሱስ ክብር የሰጠው? እርሶስ የትኛውን መጽሐፍ ይከተላሉ? ?

> መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ አርባ ቀን በሰይጣን ሲፈተንና ሲንገላተት ነበር ይለናል።
“አርባ ቀን *ከዲያብሎስ ተፈተነ*። በነዚያም ቀኖች ምንም አልበላም፥ ከተጨረሱም በኋላ ተራበ።”
— ሉቃስ 4፥2

> ቁርአን እና ሐዲስ ግን ኢየሱስን ምንም አይነት ሰይጣን አልነካውም ይለናል።
{ Quran 3:36}
{ ኢማሙ ቦኻሪ መጽሐፍ,60 ሐዲስ 102}

የትኛውም እምነት ነው ለኢየሱስ ክብር የሰጠው? እሥልምና ወይስ ክርስትና??
ፍርዱን ለህሊና።

ኢየሱስ ሆይ እንወድሃለን አንተ የተከበርክ የአሏህ ባሪያና ነቢይ ነህ።
መጽሐፍ ቅዱስ በአንተ ላይ ውሸትን ቀጣጥፎብሃል።
ቁርአን ግን ተገቢውን ክብር ሰጥቶሃል።

የመርየም ልጅ አልመሲሕ ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡
{ 5:75}

:-ሰላምም ቀጥታን በተከተለ ሰው ላይ ይሁን።
{20:47}

ሙከሚል ሙሥሊም ልጅ።
https://t.me/Christolgy_critic
370 views08:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-24 17:44:09 እነሆ ደግፌ የያዝሁት #ባሪያዬ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ምርጤ፤ በእርሱ ላይ መንፈሴን አድርጌአለሁ፥ እርሱም ለአሕዛብ ፍርድን ያወጣል።(ትንቢተ ኢሳያስ42፥1)

ይህን በትንቢተ ኢሳያስ ላይ ባሪያዬ የሚለውን ትንቢት የአማሪኛው መፅሐፍ ቅዱስ በአዲስ ኪዳን ባሪያዬ የምትለውን ቃል #ብላቴና በሚለው ለውጠውታል፦

በነቢዩ በኢሳይያስ የተባለው ይፈጸም ዘንድ እንዲህ ሲል። እነሆ የመረጥሁት ብላቴናዬ፥ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ወዳጄ፤ መንፈሴን በእርሱ ላይ አኖራለሁ፥ ፍርድንም ለአሕዛብ ያወራል።(የማቴዎስ ውንጌል12፥17-18)

የአማሪኛው መፅሐፍ ቅዱስ ብላቴና ይበለው እንጂ የእንግሊዝኛው ቅጅ ባሪያዬ ይለዋል፦

This was to fulfill what was spoken through the prophet Isaiah:
“Here is #my_servant whom I have chosen,
the one I love, in whom I delight;
I will put my Spirit on him,
and he will proclaim justice to the nations.(Matthew 12፡17-18)

Ma servant የምትለውን ቃል ለምን ብላቴና የሚል ትርጉም ሰጡት ?
በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ በብዙ ቦታ ብላቴና ለሚለው አቻ ትርጉም boy የሚው ቃል ነው ገብቶ የምናገኘው ፦

He went back to his brothers and said, #The_boy isn’t there! Where can I turn now?”Genesis 37፡30
ወደ ወንድሞቹም ተመልሶ። #ብላቴናው የለም፤ እንግዲህ እኔ ወዴት እሄዳለሁ? አለ።(ኦሪት ዘፍጥረት 37፡30)

#The_boy Samuel ministered before the Lord under Eli. In those days the word of the Lord was rare; there were not many visions.
1 Samuel 3
#ብላቴናውም ሳሙኤል በዔሊ ፊት እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር፤ በዚያም ዘመን የእግዚአብሔር ቃል ብርቅ ነበረ፤ ራእይም አይገለጥም ነበር።(1ኛ ሳሙዔል3፡1)
.
በመጨረሻም
ደበቃቹም አልደበቃቹም ኢየሱስ የአላህ ባሪያ ነው።
357 views14:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-23 11:20:08 የሚጸዳዳ አምላክ?

ለወግኖቼ ወደ ትክክልኛው መንገድ መመራትን እየተመኘሁ በአላህ ስም እጀምራለሁ !!

ብዙ ክርስቲያን ወገኖች ለምን የሚጸዳዳ ሰው ታመልካላችሁ ስንላቸው፣ ባይብል ኢየሱስ ይጸዳዳል በፍጹም አይልም በማለት ትላልቅ የሚባሉ የክርስቲያን ሙህር ነን የሚሉ ሳይቀሩ ይናገራሉ። ታዲያ ይሄን እሳቤ ዛሬ ይገነዘቡ ዘንድ ላሳያቸው ወደድኩ!

በመጀመሪያ እኛ ኢየሱስ ይጸዳዳል ብለን ስንሞግት የርሱን ተፈጥሮ እየተቃወምን አይደለም፤ የሰው ልጅ የተፈጥሮ ህግ ስለሆነ አንቃወምም። እኛ ግን ይሄን የምናነሳው ክርስቲያን ወገኖች አምላክ ብላችሁ ስለያዛችሁት ሲሆን፣ እንዴት አለማትን የፈጠረ አምላክ ይጸዳዳል ይሄ የርሱ ባሃሪ ነው? የሚለውን ትገነዘቡ ዘንድ ነው። ወደ መረጃዎቹ ስገባ ኢየሱስ እንደሚመገብ መጀመርያ እንይ!

“የሰው ልጅ እየበላና እየጠጣ መጥቶአልና፦ እነሆ፥ በላተኛና የወይን ጠጅ ጠጭ፥ የቀራጮችና የኃጢአተኞች ወዳጅ አላችሁት።”
— ሉቃስ 7፥34
እዚህ ላይ ኢየሱስ እየበላ እና እየጠጣ እንደመጣ በግልጽ ተቀምጧል!

ሉቃስ 24
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴² እነርሱም ከተጠበሰ ዓሣ አንድ ቁራጭ፥ ከማር ወለላም ሰጡት፤
⁴³ ተቀብሎም በፊታቸው በላ።

እዚህ ላይ ደግሞ ምን እንደተመገበ ግልፅ ነው።
ታድያ ይሄ የሚበላው እና የሚጠጣውን ምግብ ብሎም መጠጥ በምን መልኩ ይጸዳዳል? ለሚለው እራሱ የተናገራቸውን እንመልከት
“ወደ አፍ የሚገባ ሁሉ ወደ ሆድ አልፎ ወደ እዳሪ እንዲጣል አትመለከቱምን?”
— ማቴዎስ 15፥17
እዚህ ላይ ወደ አፍ የሚገባ ነገር #ሁሉም ወደ እዳሪ ይወጣል በማለት አስቀምጧል። ስለዚህ ኢየሱስም የሚበላ እና የሚጠጣውን በሌላ መልክ የሚያስወጣ ፍጡር ነበር ማለት ነው። ተጨማሪም፦

“ወደ ሆድ ገብቶ ወደ እዳሪ ይወጣል እንጂ ወደ ልብ አይገባምና፤ መብልን ሁሉ እያጠራ አላቸው።”
— ማርቆስ 7፥19
እዚህ ላይ ደግሞ በጣም ግልጽ አድርጎታል ወደ አፍ የሚገባ ወደ እዳሪ እንጅ ወደ ልብ አይገባም፣ ሰለዚህ ኢየሱስ ይጸዳዳል!

አላህም በተከበረው ቃሉ ምግብን ይመገቡ ነበር ብሎ አስቀምጦታል የሚበላና የሚጠጣ አካል ምን አይነት ነገሮችን እንደሚያከናውን ለመረዳት አዳጋች አይደለም።
ምዕራፍ اݪݦائدة 5:75

ݦَّا اݪْݦَسِيځُ ابْݧُ ݦَڔْيَݦَ إِݪَّا ڔَسُۅݪٌ قَدْ خَݪَټْ ݦِن قَبْݪِهِ اݪڔُّسُݪُ ۅَأُݦُّهُ صِدِّيقَةٌ ۖ كَاݧَا يَأْكُݪَاݧِ اݪطَّعَاݦَ ۗ اݧظُڔْ كَيْڣَ ݧُبَيِّݧُ ݪَهُݦُ اݪْآيَاټِ ثُݦَّ اݧظُڔْ أَݧَّىٰ يُؤْڣَكُۅݧَ

የመርየም ልጅ አልመሲሕ ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ እናቱም በጣም እውነተኛ ናት፡፡ (ሁለቱም) ምግብን የሚበሉ ነበሩ፤ አንቀጾችን ለነርሱ (ለከሓዲዎች) እንዴት እንደምናብራራ ተመልከት ከዚያም (ከእውነት) እንዴት እንደሚመለሱ ተመልከት፡፡

ሰለዚህ የሚበላ እና የሚጠጣ ፍጡር እንጅ አምላክ የለም! ይሄንን ተረድታችሁ ወደ ቀጥተኛው መንገድ ኑ! ስል እጠራችኃለሁ አላህ ይምራችሁ!

https://t.me/Christolgy_critic
ወሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላህ
330 views08:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-19 17:44:23 መርገምት

ክርስቲያን ወገኖች እንደሚያምኑት የሴት ልጅ የወር አበባ እና በመውለድ ግዜ መሰቃየት የመጣው በሄዋን ኃጢአት ምክንያት ነው ይላሉ።

“ሴት ፈሳሽ ነገር ቢኖርባት በሥጋዋም ያለው ፈሳሽ ነገር ደም ቢሆን፥ በመርገምዋ ሰባት ቀን ትቀመጣለች፤ የሚነካትም ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ነው።”
— ዘሌዋውያን 15፥19

“ለሴቲቱም አለ፦ በፀነስሽ ጊዜ ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፤ በጭንቅ ትወልጃለሽ፤ ፈቃድሽም ወደ ባልሽ ይሆናል፥ እርሱም ገዥሽ ይሆናል።”
— ዘፍጥረት 3፥16
በዚህ መሰረት ይሄ የወር አበባ ደም እና የወሊድ ጭንቀት የመጣው በሄዋን ኃጢአት ምክንያት ከሆነ፤ ኢየሱስ ለኃጢአታችሁ ከሞታላችሁ ለምን ይሄ ስቃይ አልተወገደም? ምክንያቱም እርግማናችንን እርሱ ተረግሞ በመስቀል ቋጭቶታል ሰለምትሉ!

“በእንጨት የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎአልና ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ ከሕግ እርግማን ዋጀን፤”
— ገላትያ 3፥13

ኢየሱስ ከሞተ እና ከተሰቀለ ይሄ እርግማን መቅረት ነበረበት አይደል? ከዚህ ጥቅስ ምንን እንረዳለን መሰላችሁ፦ ስቅላት የሚባለው ነገር ከንቱና ሀሰተኛ አስተምህሮ መሆኑን!

ምዕራፍ آل عݦڔان 3:64
قُݪْ يَا أَهْݪَ اݪْكِټَابِ ټَعَاݪَۅْا إِݪَىٰ كَݪِݦَةٍ سَۅَاءٍ بَيْݧَݧَا ۅَبَيْݧَكُݦْ أَݪَّا ݧَعْبُدَ إِݪَّا اݪݪَّهَ ۅَݪَا ݧُۺْڔِكَ بِهِ ۺَيْئًا ۅَݪَا يَټَّخِذَ بَعْۻُݧَا بَعْۻًا أَڔْبَابًا ݦِّن دُۅݧِ اݪݪَّهِ ۚ ڣَإِن ټَۅَݪَّۅْا ڣَقُۅݪُۅا اۺْهَدُۅا بِأَݧَّا ݦُسْݪِݦُۅݧَ

የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በእኛና በእናንተ መካከል ትክክል ወደ ኾነች ቃል ኑ፡፡ (እርሷም) አላህን እንጅ ሌላን ላንገዛ፣ በርሱም ምንንም ላናጋራ፣ ከፊላችንም ከፊሉን ከአላህ ሌላ አማልክት አድርጎ ላይይዝ ነው፤ በላቸው፡፡ እምቢ ቢሉም፡- እኛ ሙስሊሞች መኾናችንን መስክሩ በሏቸው፡፡

አላህ ቀጥተኛውን መንገድ ይምራችሁ
እኛንም ያጽናን!

ወሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላህ

https://t.me/Christolgy_critic
383 views14:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-19 17:01:50 ስቅለት

ለወግኖቼ ወደ ትክክልኛው መንገድ መመራትን እየተመኘሁ በአላህ ስም እጀምራለሁ !!

እንደሚታወቀው ክርስቲያን ወገኖች "እኛ የምንድነው ደም ፈሶ ነው እንጅ ደም ሳይፈስ ስርየት የለም" እያሉ ምንም የማያውቅ ንጹሁን ሰው ኢየሱስን አስገድሎ ነው እግዚአብሔር ያዳነን በማለት ያምናሉ፤ በዚህም ይሞግታሉ።

ይሄን ጭካኔ፥ ወይም ኃጢአትን በኃጢአት ማከማቸት ልንለው እንችላለን።
ምክንያቱም እራሱ እግዚአብሔር አንዱ በሰራው ሌላው አይሞትም በማለት ተናግሮ ሳለ ተመልሶ ደግሞ ለሌላው ኃጢአት ሌላኛው ሰውን ማስገደል አቅል የማይቀላበለው ነው።

ይሄን የሚደግፍልኝን ጥቅስ የቱ ጋ ነው ካላችሁኝ...

ሕዝቅኤል 18
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁹ እናንተ ግን፦ ልጅ የአባቱን ኃጢአት ስለ ምን አይሸከምም? ትላላችሁ። ልጅ ፍርድንና ቅን ነገርን ባደረገ ትእዛዜንም ሁሉ በጠበቀና ባደረገ ጊዜ ፈጽሞ በሕይወት ይኖራል።
²⁰ ኃጢአትን የምትሠራ ነፍስ እርስዋ ትሞታለች፤ ልጅ የአባቱን ኃጢአት አይሸከምም፥ አባትም የልጁን ኃጢአት አይሸከምም፤ የጻድቁ ጽድቅ በራሱ ላይ ይሆናል፥ የኃጢአተኛውም ኃጢአት በራሱ ላይ ይሆናል።
²¹ ኃጢአተኛውም ካደረጋት ኃጢአት ሁሉ ቢመለስ ትእዛዜንም ሁሉ ቢጠብቅ ፍርድንና ቅን ነገርንም ቢያደርግ ፈጽሞ በሕይወት ይኖራል እንጂ አይሞትም።
²² የበደለው በደል ሁሉ አይታሰብበትም፤ በሠራው ጽድቅ በሕይወት ይኖራል።

እንግዲህ እንደምንመለከተው ይህ ጥቅስ የኢየሱስን አለመሞት በግልጽ ያሳያል፥ ምክንያቱም ኣንዱ ባጠፋው ሌላኛው አይጠየቅም፣ ሊቀጣም አይችልም ይላል። በተጨማሪም ልጅ ያባቱን ኃጢአት አይሸከምም ስላለን ኢየሱስ ደግሞ የአዳም ልጅ በመሆኑ የአዳምን ኃጢአት ሊሸከምም ሆነ ስለ አዳም ኄጢአት ሊቀጣ አይችልም ማለት ነው።
“የመላልኤል ልጅ፥ የቃይናን ልጅ፥ የሄኖስ ልጅ፥ የሴት ልጅ፥ የአዳም ልጅ፥ የእግዚአብሔር ልጅ።”
— ሉቃስ 3፥38

ኢየሱስ ዝርያው የአዳም ልጅ፣ የሴት ልጅ ነው። በመሆኑም አንዱ በሰራው ሌላኛው ካልተቀጣ ደግሞ ኢየሱስ ሞተልን ማለቱ ትርጉም አይሰጥም ማለት ነው።

ይህ ነገር ደግሞ በብሉይ ኪዳን ውስጥ መሆኑ ነገሩን ጠበቅ የደርገዋል። ለምን ብትሉ፥ ጥቅሱ በአዲስ ኪዳን ቢሆን "ንስሃ ከገባን እግዚአብሔር ይቅር ይለናል፤ ምክንያቱም ያለፈውን ኢየሱስ ሞቶልናል" ብለው ሰለሚሞግቱ ይሄ ግን የሚያሳየው ብሉይ ኪዳን ኢየሱስ ከመምጣቱ በፊት ነው።. ስለዚህ ይሄን ጥቅስ አይታችሁ ኢየሱስ ሞቷል ካላችሁ ትርጉም አይሰጥም ወይም ይጋጫል ወይም አልሞተም አልተሰቀለም የሚል ሶስት ሃሳቦች ነው የሚሰጠን።

ምዕራፍ النساء 4:157

وَقَوْلِهِمْ إِنَّا قَتَلْنَا الْمَسِيحَ عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ رَسُولَ اللَّهِ وَمَا قَتَلُوهُ وَمَا صَلَبُوهُ وَلَٰكِن شُبِّهَ لَهُمْ ۚ وَإِنَّ الَّذِينَ اخْتَلَفُوا فِيهِ لَفِي شَكٍّ مِّنْهُ ۚ مَا لَهُم بِهِ مِنْ عِلْمٍ إِلَّا اتِّبَاعَ الظَّنِّ ۚ وَمَا قَتَلُوهُ يَقِينًا

«እኛ የአላህን መልክተኛ የመርየምን ልጅ አልመሲሕ ዒሳን ገደልን» በማለታቸውም (ረገምናቸው)፡፡ አልገደሉትም አልሰቀሉትምም፡፡ ግን ለእነሱ (የተገደለው ሰው በዒሳ) ተመሰለ፡፡ እነዚያም በእርሱ ነገር የተለያዩት ከእርሱ (መገደል) በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፡፡ ጥርጣሬን ከመከተል በስተቀር በእርሱ ነገር ምንም ዕውቀት የላቸውም፡፡ በእርግጥም አልገደሉትም፡፡

ወሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላህ
https://t.me/Christolgy_critic
369 views14:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ