Get Mystery Box with random crypto!

የሚጣፍጥ ስቃይ ተከታታይ ልብወለድ በያኔት ማስረሻ ክፍል ፵፯ @yanetmasra | Christian Mezmur - ክርስቲያን መዝሙር

የሚጣፍጥ ስቃይ

ተከታታይ ልብወለድ
በያኔት ማስረሻ
ክፍል ፵፯
@yanetmasra

ቀናት በጨመሩ ቁጥር ኑሮአችንም በዛው ልክ እየከበደ እንደ ዳገት አልገፋ አለ አንዳንድ ጊዜማ የሚላስ የሚቀመስም ይጠፋል እኔ የምሰራው ስራ ምንም በቂ ሊሆን አልቻለም የእናቴ አሠሪ የሆኑት ሠዎች በግ ይዘው ከመጡ ወዲህ ደብዛቸው ጠፍቷል አስቀድማ እንደነገረችን ከሆነ ሚስቲቱም የባሏን እጅ ነው የምትጠብቀው እንጂ ሌላ መተዳደሪያ የላቸውም አቅሟ ውስን እንደሆነ እና ማረግ ከምትችለው በላይ ማድረግ እንደማትችልም ነግራኛለች ደሞ ማድረግም ግዴታዋ አልነበረም ።
        አንድ ቀን ከትምህርት ቤት ስመጣ መሰረት እና ፍቅርተ ሠፋ ባለ ጎድጓዳ የወጥ መቀነሻ በሚመስል ሳህን ቆሎ ይዘው ተመለከትኳቸው ጠጋ ብዬ ወደነሱ ለመብላት እጄን ስዘረጋ " ተው ! " ብላ መሠረት ከለከለቺኝ " ለምን ? " ብዬ ጠየቅኳቸው ፤ ይህን ሁሉ ልትበይ ነው በሚል አመለካከት እየተመለከትኳት " ይሄ እኛ አንድንበላው የተዘጋጀ ሳይሆን እንዲሸጥ ተብሎ ነው የተሰጠን " አለቺኝ በድንጋጤ ተመለከትኳት ከመቼ ጀምሮ ነው ሻጭ  የሆኑት የሚል ጥያቄ ውስጤ ፈጥሮብኝ " ማነው ሽጡ ያላችሁ ? ለምንስ ትሸጣላችሁ ማለቴ ከመቼ ጀምሮ ? " ብዬ በቁም ነገር ጠየቅኳቸው " እማዬ ናት ከትምህርት ቤት ስንመለስ ፤ ' ከእንግዲህ በሗላ ከትምህርት ስትመጡ የውጭ ስራ መስራት አለባችሁ አሁን ህፃን ልጆች አይደላችሁም እኔ እናንተን ማስተዳደር ስለማልችል ፆማችሁን ላለማደር ስትሉ የግድ መስራት አለባችሁ ፤ ይህን ደም የምትጀምሩት ቆሎ በመሸጥ ነው ። ' ብላ አዘጋጅታ የጠበቀችንን ቆሎ እንድንሸጠው ሠጠችን ፤ ደሞ የት መሸጥ እንዳለብን ፣ ምን ማድረግ እንዳለብን ነግራናለች ስለዚህ ይህ ቆሎ የሚሸጥ ነው ። " ብላ አረፍተነገሯን ቋጨች



የሠማሁትን ነገር ማመን ከበደኝ አደባባይ ወጥተው ገና በታዳጊ እድሜያቸው ቆሎ ሲሸጡ ማየት ለኔ ከባድ ነው ሠካራሙ ፣ ዱርዬው ፣ በእድሜ ተልቆ በአስተሳሰብ የቀለለው ሁሉ መጫወቻ እንደሚሆኑ በአይነህሊናዬ ታየኝ ። ይህን ያልኩት እንዲሁ ከመሬት ተነስቼ አይደለም እኔ ጫማ የምጠርግበት አካባቢ ብዙ ጎዳና ተዳዳሪ የሆኑ ወላጅ የሌላቸው ህፃናት ፣ ቤተሰቦቻቸው ልጆቻቸውን ማስተዳደር ስለከበዳቸው እደጅ ወጥተው የሚሰሩ ልጆቻቸውን ስለማች በተለይ ሴቶቹን ምን ያህል ፈተናቸውን እንደሚያበዙት ስለማውቅ በሰው የምጠላው ነገር እህቶቼ ላይ ይደርሳል ብዬ ማሰቡ ሰቀጠጠኝ ማንኛውም ወንድም እህቱ የማይሆን ቦታ ስትገባ እያየ ዝም ማለት እንደማይችለው ሁሉ " እኔም  ፍቃዴን የጠየቁ ይመስል " " አትሄዱም " ብዬ ከለከልኳቸው ከነሱ አልፌ ከየት እንዳመጣሁት ባላውቅም እናቴን " እነሱ ወጥተው መስራት አይችሉም የቤቱንም ስራ እየሰሩ ስለሆነ የውጪውን መስራት ለነሱ አይታሰብም ፤ ደሞ በምን ጊዜ ሊያጠኑ ነው ትምህርት ቤት ውለው ፣ ቆሎ ሽጠው  የቤት ውስጥ ስራ ሰርተው " ብዬ ተናገርኩ በእርግጥ ይሄ ብቻ ሳይሆን ያሳሰበኝ በሴትነታቸው የሚደርስባቸውም ጥቃት ጭምር ነው ። ለእናቴ ግን ከምክንያቶቼ መካከል ይሄን ሳላካትት ነበር የነገርኳት " ያንተን ፍቃድ የጠየቀ የለም መኖር ከፈለጉ መስራት አለባቸው እንደድሮው ጉልበቷን አፍሳ የምታኖር እናት የለችም እዚው ተሽመድምዳ ቀርታለች ስለዚህ ሁሉም የድርሻውን መስራት እና እራሱን መምራት አለበት የምታመጣው ሽርፍራፊ ሳንቲም ቤቱን ቀጥ አድርጎ የሚያስተዳድር መስሎህ ከሆነ ተሳስተሀል እንኳን እሱ ቀርቶ ቀድሜ የሸመትኩት ሙጥጥ ተደርጎ ተበልቶ አልቋል ሌላ የገቢ ምንጭም ሆነ የሚረዳ ዘመድ የለንም ስለዚህ በማያገባህ አትግባ ልጆቹ ስራ ይስሩበት " አለቺኝ ....ይቀጥላል
#share

ለሌሎችም እንዲደርስ #share


     ይ ላ ሉን
@christian_mezmur
@christian_mezmur