Get Mystery Box with random crypto!

የሚጣፍጥ ስቃይ ተከታታይ ልብወለድ በያኔት ማስረሻ ክፍል ፳ @yanetmasra ከ | Christian Mezmur - ክርስቲያን መዝሙር

የሚጣፍጥ ስቃይ

ተከታታይ ልብወለድ
በያኔት ማስረሻ
ክፍል ፳
@yanetmasra

ከአእምሮ አውጣ ብለው ተቆጡኝ እኔም መልሼ ብሄድ የት እንደምሄድ እንኳን አላውቅም ነገር ግን በእናቴ ስራ እጅግ አፍርያለሁ እያዋረደቻችሁ እየተመለከትኩ ምንም እንዳልተፈጠረ ማስመሰል ለኔ ከባድ ነው የሚሆንብኝ " ብዬ መለስኩላቸው  መስሎህ ነው እንጂ አንተ ባትመጣም ለኔ ጥሩ አመለካከት የላትም ስለዚ ኖርህም አልኖርህም ልትወደኝ አትችልም ባንተ ምክንያት አደለም የሌለ ነገር እየፈጠርክ አትታወክ ድጋሚ እንዲ ካልከኝ ግን ከናንተ ጋር መኖር አልፈልግም አልተመቻችሁኝም እንዳልከኝ ነው የምቆጥረው ያኔ መብትህ ነው መውጣት ትችላለህ " አሉኝ ምንም እንዳልል አፌን አዘጉኝ እንኳን ላይመቹኝ ይቅርና የበዛ መልካምነታቸው ሠው መሆናቸውን እያጠራጠረኝ ነው ። የዛኑ ቀን ወደ ቤተሰቦቼ ቤት ሄድኩ እናቴ አልነበረችም ያሉት እህቶቼ ነበሩ ከእነሱ ጋር እያወራሁና እየተጫወትኩ እናቴን መጠበቅ ጀመርኩ እሷም ትንሽ ብቻ አስጠብቃኝ መጣች ገና እኔን ከማየቷ ፊቷ ድምን ሲል ታየኝ " ደሞ ምን ቀረኝ ብለህ ነው የመጣኸው ? እቤቴስ ማን ግባ አለህ ? እናንተስ ብትሆኑ አታስገቡት ብያችሁ አልነበር ለምን አስገባችሁት ነው ወይስ ትዕዛዜን ማክበር ተዋችሁ " ብላ አፈጠጠችባቸው ከመፍራታቸው የተነሳ እምባቸው ቅርር አለ እነሱን ተያቸው አላስገባህም ማለት ስላልቻሉ ነው እኔም ደሞ ላወራሽ ስለፈለኩ ነው የመጣሁት ከእቤት ውጪ የት ላገኝሽ እችላለሁ ልጠብቅሽ የምችለው እዚ ስለሆነ ነው ይቅርታ ግን ማውራት አለብን " አልኳት "ጭራሽ ልታዘኝ እየሞከርክ ነው አጅሬው ፤ ደሞ ስለምን ልታወራኝ መጣህ " አለቺኝ ቤቱን ቃኘት አረኩት እህቶቼ አሉ እነሡ ፊት ርዕሱን ማንሳት ባልፈልግም ግቡ የምላቸው ትርፍ ክፍል ስለሌለ እዛው እንዳሉ " ለምንድነው የበሱፈቃድን እናት በሠው ፊት የምታዋርጃቸው አንቺ ከቤት ስታባረሪኝ እና መሄጃ ሳጣ ሊያስጠጉኝ ቤታቸውን ከፈቱልኝ እንጂ ምን አደረጉኝ እና ነው ከቤት ያስወጡኝ ይመስል



እንደ ሀጥያተኛ ሠው ፊት የምታስኮንኛቸው ለምንስ ከእድር እንዲባረሩ ሰውን አሳመፅሽባቸው አሁን ይሄን ስራ እግዚአብሔር ይወደዋል ?.." ሌላውን ቃል እንድቀጥል ፋታ ሳትሰጠኝ " እንዴ ጭራሽ ብለህ ብለህ ልትቆጣኝ መጣህ ና ደብድበኝ እሱ ነው የቀረህ ምንስ ብል ምን አገባህና ልትናገረኝ መጣህ ወይስ ያቺ ክብረ ቢስ ሴትዬ ሂድና ስደባት ብላህ ነው የመጣኸው " አለቺኝ " እማ እንዴት እንዲ ትያለሽ እኔ በምን አቅሜና ህሊናዬ ነው አንቺን የምሰድብሽ እሳቸውም ቢሆኑ ሂድና ተናገራት አላሉኝም እራሴ ስለፈለኩ ነው ላወራሽ የመጣሁት ካለ ስራቸውና ካለ በደላቸው  እንዳገለላችሗቸው ሰምቻለሁ ለዛ ደሞ ዋናዋ አንቺ ስለሆንሽ እንድትተይ ልጠይቅሽ ነው ፤ እጅግ በጣም ፈጣሪ የሚጠላውን ነገር እያደረግሽ ነው አልገባሽም እንጂ ከእሳቸው ጋር ሳይሆን ከፈጣሪ ጋር ነው እየተጣላሽ ያለሽው ስለዚ እባክሽ ልለምንሽ ተያቸው መናገርም ፣ መደብደብም ፣ ልታደርጊ የምትፈልጊውን ነገር ሁሉ እኔን አድርጊኝ እሳቸውን ግን ተያቸው " አልኳት የበሱፈቃድ እናት ያረጁ ሆነው ሳይሆን ለአክብሮት ነው አንቱ የምላቸው በእድሜ ግን ከእናቴ በጥቂቱ ብቻ ቢበልጡ ነው ። " ሟሟና እንደ በረዶ ደሞ እማ ይላል እንዴ ገና ከሰፈሩ እንድትወጣ ነው የማደርጋት ገና ምን አየህና ነው የምታሞጠሙጠው ጨርቋን አስጥዬ ካላሳበድኳት ሠው አትበለኝ እንደውም በጊዜ መኖሪያሽን ፈልጊ በላት አንተም ብትሆን ከእንግዲ ደጄ እንዳትደርስ ሾካካ በል ውጣልኝ " ጥንብርኩሴን ከውጥታ እያመናጨቀች ከቤቱ አስወጣቺኝ እናቴ በጣም ብሶባት ነበር ከቀን ወደቀን ነገረኛ እየሆነች ነው....ይቀጥላል


ለሌሎችም እንዲደርስ #share


     ይ ላ ሉን
@christian_mezmur
@christian_mezmur