Get Mystery Box with random crypto!

የሚጣፍጥ ስቃይ ተከታታይ ልብወለድ በያኔት ማስረሻ ክፍል ፲፱ @yanetmasra | Christian Mezmur - ክርስቲያን መዝሙር

የሚጣፍጥ ስቃይ

ተከታታይ ልብወለድ
በያኔት ማስረሻ
ክፍል ፲፱
@yanetmasra

ለተወሰነ ቀን እቤት ውስጥ ተኝተው ከረሙ እስኪያገግሙ ድረስ እደጅ መውጣት የማይታሰብ ነገር ነበር ቢሆንም ግን ሊፀልይላቸው የሚመጣ እና በዛ ሁኔታ ውስጥ ሆነው ፀልዩልኝ እያለ የሚመጣ ሰው የዋዛ አልነበረም በጣም ቢገርመኝም አንድ የተረዳሁት ነገር ቢኖር መቼም ቢሆን ወንጌል እንደማይቆም ነው ምንም ቢፈጠር ቢገደሉ ፣ ቢታሰሩ ፣ ቢደበደቡ እውነት ግን እያደረች ራሷን ትገልጣለች አንድ ቢታመም አንዱን ይተካል ፤ አንዱ ቢሞት እግዚአብሔር አንዱን ይሾማል የሰዉ ቁጥር በዛም አነሰ እግዚያብሄር ግን መወደሱ እና መመለኩ የማይቀር ነገር ነው

   ነገሮች እያየናቸው እየከፉ መጡ ከትላንት ዛሬ ፣ ከዛሬ ነገ መከራው አንድ ደረጃ እየባሰ መጣ እኔና በሱፈቃድ ሳንቀር ትምህርት ቤት ያሉ ተማሪዎች ይዝቱብን ጀመር አንድ ቀን በጃቸው ከገባን እንደማይለቁን እርግጠኛ ነበርኩ በወቅቱ ያዘንኩት ለበሱፈቃድ እናት ነው አሁን እኛንም ከደበደቡ እንዴት አድርገው ሶስት ህመምተኛ ብቻቸውን ያስታምማሉ ብዬ ተጨነቅኩላቸው እግዚአብሔር ፀሎቴን የሰማኝ መሰለኝ የበሱፈቃድ አባት አገግመው ከቤት እስኪወጡ ድረስ ምንም ሳንሆን ቀረን አንድ ነገር ቀለለ ኡፎይ ከማለታችን ሌላው ችግር መምጣቱ የማያባራ ሆነ አንዱን መሰናክል አለፍን ብለን ሳንጨርስ ሌላው ደሞ ሊተበትበን ይመጣል ቤተሰቡ አንድ በአንድ መጠቃት ጀመረ ፤ ቀጣዩ ተጠቂ ሆነው የተገኙት ደሞ የበሱፈቃድ እናት ናቸው የሠፈሩ ሴቶች ተማክረው ከእድሩ አስወጧቸው ከሀዲ ከኛ ጋር ህብረት የለውም ብለው ተነሱባቸው በእምነታቸው ብቻ ከማህበራዊ ህይወት እንዲገለሉ ተደረጉ ማንም ቢሆን ከሳቸው ጋር ህብረት ማድረግ የሚፈልግ ጠፋ ታድያ



እንዲ እንዲሆን ያደረገችው አንደኛዋ እናቴ መሆኗን ስሰማ ከልብ አዘንኩ የጥፋተኝነት ስሜት ተሰምቶኝ አይናቸውን ማየት ከበደኝ ይባስ ብለው ደሞ " ይኸው ሰው ሁሉ እምነቱን እንዲበርዝ እየበከሉ ነው የኔንም ምንም የማያውቀውን ልጄን ጴንጤ አደረጉብኝ ዝም ካላችሁ ነገ ከነገ ወድያ ወደናንተ ቤት ሰተት ብሎ እያንኳኳ ይመጣል ካሁኑ ልጆቻችሁንና ቤተሰባችሁን ካሁኑ ካላራቃችሁ እንዲሁም ከማንኛውም ማህበራዊ ግንኙነት ካልገደብናቸው መጨረሻችን አያምርም እያደር ባዶ  ያስቀሩናል " ብላ አሳመፀች ሰውም ያጉረመርምባቸው ጀመር " ልክ ነው ካሁኑ እርምጃ ካልወሰድን እዬዬው ነገ ቤታችን ሰተት ብሎ ይገባል " ብለው ከእድሩ አስወጧቸው ሰድበው ፣ አንጓጠው በክብራቸው ተዘባብተውባቸው መለሷቸው እንዲህ ከተባሉ በሗላ አብርያቸው መኖር ከበደኝ ሳወጣና ሳወርድ ቆይቼ " በኔ ምክንያተሸ ችግር ውስጥ እንድትገቡ አልፈልግም እናቴ ስላደረገችው ነገር በጣም ይቅርታ እኔ በሷ ቦታ ሆኜ ይቅርታ እጠይቃለሁ ከዚ በሗላ ግን አትደግመውም አሁን እናንተ ጋር ስለምኖር በንዴት ነው ልጄን ጴንጤ አደረጉብኝ ብላ በክፋት የተነሳችባችሁ ከዚ ቤት ግን ከወጣሁ ምንም ልትላችሁ ስለዚህ ከዚ በሗላ ከናንተ ጋር መኖር አልችልም ስለሁሉም አመሠግናለሁ አልኳቸው እሳቸውም " ስለምን መውጣት ነው የምታወራው ወጥተህስ የት ለመሄድ ነው በዛ ላይ ያንተ ጥፋት ባልሆነ ነገር ራስህን መውቀስና ይቅርታ መጠየቅ አስፈላጊ አደለም እናትህ አለማወቋ ነው እንድትሰድበኝ ያደረጋት በዛ ላይ እሷ ሳትሆን በውስጧ ያለው እርኩስ  መንፈስ ነው እንዲ እንድትናገር የሚያደርጋት እኔ ቂም አልይዝባትም አንተም ብትሆን እወጣለሁ የሚለውን የጅል ሀሳብ ከአይምሮህ አውጣ" አሉኝ ....ይቀጥላል


ለሌሎችም እንዲደርስ #share


     ይ ላ ሉን
@christian_mezmur
@christian_mezmur