Get Mystery Box with random crypto!

አታለቃቅስ!! ካጠገቤ ሚቆም አለሁህ የሚለኝ ሰው የለኝም ብለህ! ሰው ሆኖ የመጣው የናዝሬቱ ኢየሱ | Christian Mezmur - ክርስቲያን መዝሙር

አታለቃቅስ!!

ካጠገቤ ሚቆም አለሁህ የሚለኝ ሰው የለኝም ብለህ! ሰው ሆኖ የመጣው የናዝሬቱ ኢየሱስ ከቶ መች ያውቅና ላፍታ ተለይቶህ?

አታለቃቅስ!
ሰዎች ቅንነቴን ሞኝነት አረጉት ቆጠሩብኝ ብለህ! እግዚአብሔር የቅኖች
ፃድቅ ፈራጅ እንጂ የጮሌዎች አምላክ እንዳይደለ ረስተህ!

አታለቃቅስ!
ሰው አልፈለገኝም ስፍራም አልሰጠኝም ረስቶኛል ብለህ!
የፀጋውን ዙፋን ስር የግርማውን ክብር
ከቶ ማን ነፈገህ?

አታለቃቅስ!
ንቀት ጠግቤያለሁ አንገት ደፍቻለሁ የሳር የቅጠሉ መሳለቂያ ሆኛለሁ አረ ተውኝ ብለህ! ግንበኞች የናቁትን የማዕዘን ራስ ድንጋይ የክብርን ዓለት ኢየሱስን ይዘህ!

አታለቃቅስ!
አልተቀበሉኝም ጭራሽ ከቁም ነገር ሰዋች አልፃፉኝም ፊታቸውን ነሱኝ ተኩራሩብኝ ብለህ!
ፊቱን ሳይከሰክስ የተቀበለህን እንደባለማዕረግ ደግሞ የቆጠረህን
እሱን ማን አስረሳህ የኔ ነህ ያለህን?

አታለቃቅስ!
አቤት ነገሬ እኮ እጅግ ዘገየብኝ
ለኔ ሲሆን ሁሉ ተወሳሰበብኝ
ከበደብኝ ብለህ!
ሰባኪው እንዳለው አንዴ የተራመደ የተነሳ ለታ ዘመናትን ቀድሞ
ሚገኘውን ጌታ
የጊዜን ባለቤት እንዴት ዘነጋኽው የዕድሜህን አለኝታ!

አታለቃቅስ!
አንተ እኮ ከጌታ ጋር
አንተ እኮ ከአምላክህ ጋር
አንተ እኮ ከሰሪህ ጋር
አንተ እኮ ከአዳኝህ ጋር
ትበልጣለህ ከብዙ ሺህ
በል ተነሳ ቀጥል እሺ!!



@KALTUBE
@KALTUBE
@KALTUBE