Get Mystery Box with random crypto!

#Alert ከአበበ ቢቂላ ወደ አዲስአበባ ስታድየም ተዘዋውሮ የነበረው ፕሮግራም ተሰርዟል! ውዝግ | Christian Mezmur - ክርስቲያን መዝሙር

#Alert
ከአበበ ቢቂላ ወደ አዲስአበባ ስታድየም ተዘዋውሮ የነበረው ፕሮግራም ተሰርዟል!

ውዝግብ ሲያስነሳ የነበረው ቅድሚያ በሻንበል አበበ ቢቂላ ስታዲየም ሊካሄድ ቀን የተቆረጠለትና በአንዳንድ አስቂኝ ምክንያቶች እድሳት ላይ ወደ ሚገኘው አዲስ አበባ ስታዲየም የተዘዋወረው ፕሮግራም መሰረዙ ተሰምቷል።

የፊታችን ቅዳሜ ከሐዋርያው ታምራት ታረቀኝ እና ከሐዋርያው ጉሌርሞ ማልዶናዶ ጋር ልዩ የሆነ የትንቢት፣ የፈውስ እና ነፃ የመውጣት አገልግሎት በዋናው የቤተክርስትያኒትዋ ግቢ ይኖረናል። በእለቱም ከተጋባዥ ዘማሪያን ጋር ጌታን እናመልካለን! በአዲስአበባ ስታድየም ልንመጣ የነበረን ምዕመን መያዝ በሚችል መልኩ ቤተክርስትያናችንን ያዘጋጀን መሆኑን እንገልፃለን ስትል ቤተክርስቲያኒቷ ገልፃለች።

የዛሬው የአገልጋዮች ስልጠናና ፀጋን የመካፈል ጊዜ በተያዘለት መርሃግብር እንደሚቀጥልም ተጠቁሟል።

ኮንፈረንሱ የተሰረዘበትን ምክንያት በእለቱ(ቅዳሜ) እናሳውቃለን።
በፍፁም እንዳትቀሩ ስትልም ለምዕመናን ጥሪዋን አስተላልፋለች።

ቦታ
ኮተቤ 02 ወደ ወንድራድ ትምህርት ቤት በሚወስደው መንገድ 200 ሜትር ሄዶ ከዚያ በስተ ቀኝ በኩል

ወንጌል ብቻውን ያሸንፋል!

@christian_mezmur