Get Mystery Box with random crypto!

አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ

የቴሌግራም ቻናል አርማ christian930 — አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ
የቴሌግራም ቻናል አርማ christian930 — አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ
የሰርጥ አድራሻ: @christian930
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.50K
የሰርጥ መግለጫ

የዮሐንስ ራዕይ 22፥11-14
«ዐመፀኛው ወደ ፊት ያምፅ፥ ርኩሱም ወደ ፊት ይርከስ፥ ጻድቁም ወደ ፊት ጽድቅ ያድርግ፥ ቅዱሱም ወደ ፊት ይቀደስ አለ። እንሆ፥ በቶሎ እመጣለኹ፥ለያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋራ አለ። አልፋና ዖሜጋ፥ፊተኛውና ዃለኛው፥ መዠመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ።
➘➘➘
☞ @christian930
ግሩፕ፦ @AlphaOmega930
📩☞ @Kyrieelesion

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 07:43:08
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ ሃያ ስድስት፦

እጅግ የከበሩ ታላለቆቹ ቅዱሳን አባቶቻችንን አቡነ ኢየሱስ ሞዐ እና አቡነ ሀብተ ማርያም የተፀነሱበት ዕለት ነው፡፡ ዳግመኛም በዚኽች ዕለት አባ ሞይስስና እኅቱ ቅድስት ሣራ ዕረፍታቸው ነው፡፡ የተመሰገነች የእናታችን የአብርሃም ሚስት ቅድስት ሣራም የመታሰቢያዋ በዓል ነው፡፡ የወገጉ አቡነ ሳሙኤልም ፍልሰተ ዐፅማቸው የተከናወነው በዚሁ ዕለት ነው፡፡ አባ አጋቦስና ሰማዕቷ ቅድስት ቴክላም ዕረፍታቸው በዚሁ ዕለት ነው፡፡ እነዚህም ቅዱሳን ጌታችንን በማመናቸው በከሃዲው ንጉሥ በሉልያኖስ ዘመን መከራን የተቀበሉ ናቸው፡፡ ከመኳንንቶቹ አንዱ ጽኑ ሥቃይን አሠቃያቸው፡፡ ማሠቃየቱም በሰለቸው ጊዜ ለተራቡ አንበሶች ሰጣቸውና ሰማዕትነታቸውን ፈጽመው የክብርን አክሊል ተቀዳጁ፡፡
2.3K viewsዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ, edited  04:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 07:17:27
ወርኅ ነሐሴ ፳፬

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ ሃያ አራት ጌታችን በቅዱስ አምላካዊ ቃሉ ‹‹ሐዲስ ሐዋርያ›› ብሎ የሰየማቸው የኢትዮጵያ ብርሃኗ የሆኑ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዕረፍታቸው ነው፡፡ ምግባር ሃይማኖት፣ ገድል ትሩፋታቸው ከማር የጣፈጠ ሰማዕቱ አቡነ ቶማስ ዘመርዓስ ዕረፍታቸው ነው፡፡ ለ12 ዓመታት በጉድጓድ ውስጥ በተጋድሎ የኖረች እንዲሁም በጣና ባሕር ውስጥ ገብታ ሰውነቷ ተበሳስቶ የባሕር ዓሣ መመላለሻ እስከሚሆን ድረስ እንደ ተተከለ ዓምድ ሆና ከባሕሩ ሳትወጣ 12 ዓመት ቆማ ስትጸልይ የኖረችው እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ዕረፍቷ ነው፡፡

❖ የቅዱስ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት አብይት በዓላት እነዚህ ናቸው፦
መጋቢት 24 ቀን 1196 ዓ.ም ፅንሰታቸው
ታኅሣሥ 24 ቀን 1197 ዓ.ም ልደታቸው
ኅዳር 24 ቀን ከ24ቱ ካህናተ ሰማይ ጋር በሕይወተ ሥጋ እያሉ የሥላሴን መንበር ያጠኑበት ሲሆን
ጥር 4 ቀን 1289 ዓ.ም ደግሞ በጸሎት ብዛት አንድ እግራቸው የተሰበረበት ነው (ነገር ግን የዕረፍታቸውን ቀን ይዞ በዚሁ በጥር ወር በ24 ይከበራል)
ነሐሴ 24 ቀን 1296 ዓ.ም ዕረፍታቸው
በግንቦት 12 ቀን 1353 ዓ.ም ፍልሰተ ዐፅማቸው ነው፡፡

«ስማቸውን ከሚጠሩት ነፍሳት ሁሉ ጻድቅም ቢሆን ኃጥእም ቢሆን ወደ ክቡር አባታችን ተክለ ሃይማኖት ሳያደርሱት ወደ ዘላለም ርስቱ ወይም ወደ ሲኦል አያገቡትም»

[አርኬ]
ሰላም ዕብል እንበለ አርምሞ በጽዋዔ፡፡ ኪያከ አበ ወኪያከ ረዳዔ፡፡ ተክለ ሃይማኖት መዋዒ እንዘ ትጸንሕ ተስፋ ትንሣኤ፡፡ አጽናዕከ ለቀዊም አእጋረ ክልኤ፡፡ ወእምስቴ ማይ አህረምከ ጕርዔ፡፡

የከበረች ቃልኪዳናቸው ኹላችንንም ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ይጠብቀን! አሜን!
t.me/AlphaOmega930
338 viewsዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ, 04:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 13:31:35 ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን
እምነት ፣ ተስፋ ፣ ፍቅር
ትምህርት ክፍል-2 (መ)
~ 21- ነሐሴ - 2014 ዓ.ም ~
2.6K viewsዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ, edited  10:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 07:48:19
3.8K viewsዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ, 04:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 11:09:55 Emailing መልእክተ_ሱባኤ_2014_ዓ_ም_ባለ_ትንቢቱ_ቴወድሮስ_ማን_ነው_ምን_እያደረገ_ነው_መቼ_ነው_በይፋ_በአካል.pdf
754 viewsዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ, 08:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 11:07:02 መልእክተ ሱባኤ | 2014 ዓ.ም
"ባለትንቢቱ ቴዎድሮስ ማን ነው?
"ምን እያደረገ ነው?
"መቼ ነው በይፋ በአካል የሚገለጸው?


በተክለኪዳን | ነሐሴ 15ና 16 / 2014 ዓ.ም
3.0K viewsዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ, edited  08:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 10:23:30



3.7K viewsዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ, edited  07:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 09:40:52
3.5K viewsዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ, 06:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 20:17:00
ቅዱሳኑን አብነት ማድረግ ይገባናል
ሐዋርያው ‹‹ የእግዚአብሔርን ቃል የነገሩአችሁን ዋኖቻችሁ አስቡ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመላከታችሁ በእምነት ምሰሉአቸው›› ዓለን እዕ 13፡7 በቆሮንቶስ መልእክቱም
‹‹ እኔ ክርስቶስ እንደምመስል እናንተም እኔን ምሰሉ›› 1ኛቆሮ 11፡1
መንፈሳዊ ልጁ ጢሞቴዎስንም ኑሮዮን አብነት ፣ አርአያ አድርግ ብሎታል በትንቢት መጽሐፍም
‹‹ ወደ አባታቸወሁ ወደ አብርሃም ወደ ወለደቻችሁ ወደ ሳራ ተመልከቱ›› ተብሎ ተጽፏል፡፡ት.ኢሳ 51፡2 ይህ ማለት አርያአ አድርግዋቸው ምሰልአቸው ማለት ነው፡፡

የአባታችን አለቃ አያሌው ታምሩ በረከት ይደርብን። አሜን
3.1K viewsገብረ ሥላሴ የኢትዮጵያ ልጅ, 17:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 12:41:28
4.1K viewsየኔሰው @Ethiopia, 09:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ