Get Mystery Box with random crypto!

የክርስቶስ ደቀመዝሙር ✞

የቴሌግራም ቻናል አርማ christdisciples — የክርስቶስ ደቀመዝሙር ✞
የቴሌግራም ቻናል አርማ christdisciples — የክርስቶስ ደቀመዝሙር ✞
የሰርጥ አድራሻ: @christdisciples
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.08K
የሰርጥ መግለጫ

* ይህ channel ሰለ እውነተኛ የክርስቶስ ደቀመዝሙርነት ከቅዱሱ መፀሀፍ የሚታይበት ነዉ፡፡
" ማንም መስቀሉን ተሸክሞ በኋላዬ የማይመጣ፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።" ሉቃ 14 : 27

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-04-24 08:24:33
መልአኩ ድንጋዩን ያንከባለለዉ ኢደሱስ ከመቃብሩ እንዲወጣ ሳይሆን እነ መቅደላዊት ማሪያም ሽቱ ሊቀቡት እንዲገቡ ነበር ፡፡

#ሰንበትም ካለፈ በኋላ መግደላዊት ማርያም የያዕቆብም እናት ማርያም ሰሎሜም መጥተው ሊቀቡት ሽቱ ገዙ። ከሳምንቱም በፊተኛው ቀን እጅግ በማለዳ ፀሐይ ከወጣ በኋላ ወደ መቃብር መጡ።
እርስ በርሳቸውም። ድንጋዩን ከመቃብር ደጃፍ ማን ያንከባልልልናል? ይባባሉ ነበር፤
(የማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ 16 ፥ 1-3)

#እነሆም ፥ የጌታ መልአክ ከሰማይ ስለ ወረደ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ቀርቦም ድንጋዩን አንከባሎ በላዩ ተቀመጠ።"
(የማቴዎስ ወንጌል 28:2)
538 views05:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-23 09:00:13
ጌታዬና አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስ ኾይ፡፡➊
ለእኔ ኃጢአት ብለህ በጎልጎታ ቀራኒዮ ተሰቅለህ ሞተኃልኛል፤ እኔ የእግዚአብሔር ጽድቅ እሆን ዘንድ አንተ ኃጢአት ኾነህልኛል➋ እኔ ኃጢአተኛ፣ በደለኛ ነኝ፡፡➌ ዛሬም በደምህ ከኃጢአቴ አንጻኝ፡➍

ጌታ ኾይ፥ በመስቀሉ ስራ እንዳምን በመንፈስህ ስላበራህልኝ አመሠግናለሁ። አሜን

PS
➊" ቶማስም። ጌታዬ አምላኬም ብሎ መለሰለት።"
(የዮሐንስ ወንጌል 20:28)

➋" እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው።" (2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:21)

➌" ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤" (ወደ ሮሜ ሰዎች 3:23)

➍" ... የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።" (1ኛ የዮሐንስ መልእክት 1:7)

@Christdisciples
530 views06:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-23 07:41:56
#ቀን_ሃምሳ አምስት ፶፭/55 ቅዳሜ
የመጨረሻ ቀን.....


" የአዲስም ኪዳን መካከለኛ ወደሚሆን ወደ ኢየሱስ፥ #ከአቤልም_ደም_ይልቅ_የሚሻለውን_ወደሚናገር_ወደ_መርጨት_ደም_ደርሳችኋል ።"
(ወደ ዕብራውያን 12:24)

በመስቀል ላይ የፈሰሰልን ደም ተራ የአንድ ሰዉ ደም ብቻ አይደለም በመስቀል ላይ የፈሰሰዉ ደም አምላክ ሰዉ ሁኖ ስለኛ መተላለፍና በደል የከፈለዉ ዋጋ እንጂ ፡፡ ይህ ደም እንደ ዋዛ ፈሶም የቀረ ደም አይደለም ይልቁንስ ወደ እግዚአብሔር ዘወትር ስለ ምህረትና ይቅርታ ስለኛ የሚጮህ ነዉ ፡፡

" አለውም። ምን አደረግህ? የወንድምህ የደሙ ድምፅ ከምድር ወደ እኔ ይጮኻል። "
(ኦሪት ዘፍጥረት 4:10)

በእርግጥ ቃየን ወንድሙ አቤልን ሲገለዉ የአቤል ደም ስለ ራሱ ፍትህ ወደ እግዚአብሔር ይጮህ ነበር በመስቀል ላይ ስለኛ የፈሰሰዉ የንጉሳችን ኢየሱስ ደም ግን ስለ ራሱ ሳይሆን ስለኛ ምህረትና ይቅርታ ዘወትር ይጮኸል ፡፡ በእርግጥ እግዚአብሔር ከአቤል ይልቅ ለሚጮኸዉ ደም እንዴት ምህረቱን በኢየሱስ በኩል ለህዝቡ አይሰጥ???!

#መልካም_ቀን!
384 viewsedited  04:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-22 08:23:40
#ቀን_ሃምሳአራት ፶፬/54 #አርብ

" ገና ደካሞች ሳለን ክርስቶስ ዘመኑ ሲደርስ ስለ ኃጢአተኞች ሞቶአልና።"
(ወደ ሮሜ ሰዎች 5:6)

ክርስቶስ ሞቶልኛል፡፡ የኔ ሕይወት የሚመዘነዉ ባለኝ ሀብት መጠን ፣ በእዉቀቴ ልክ ፣... ሳይሆን በወደደኝ ደግሞ ኃጢያተኛ ሁኜ በሞተልኝ በጌታዬ ፍቅር ነዉ ፡፡
በእርግጥ ክርስቶስ እጅግ በጣም ይወደኛል ፡፡ ለዚህም ሞቶልኛል !

ለዚህ ነዉ ፍቅሩን ላስታዉስ መስቀሌን የምሸከመዉ ፣ ለዚህ ነዉ አድራሻዬ መስቀሉ ስር ነዉ የምለዉ ፣
#መስቀሉን ሳስብ እበረታለሁ
#መስቀሉን ሳስብ እፅናናለሁ
#መስቀሉን ሳስብ እታደሳለሁ
#መስቀሉን ሳስብ ሀሴት አደርጋለሁ

ለዚህ ነዉ ደቀመዝሙርነቴን የምወደዉ ፣ ለዚህ ነዉ አድራሻዬን የቀየርኩት ፤ ኢየሱስ ኃጢያተኛ ሁኜ ወዶኛል ደግሞም ሞቶልኛል ፡፡ እንዴት ያለ ፍቅር ነዉ ?!

#መልካም ቀን
358 views05:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-21 05:55:48
#ቀን_ሃምሳሶስት ፶፭/53 #ሀሙስ

" ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ #ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ #ፍቅር ለማንም የለውም።"
(የዮሐንስ ወንጌል 15:13)

ፍቅር ! ፍቅር ! ፍቅር !
በዚህ ክፍል እራሱ ኢየሱስ ስለ ፍቅር ለደቀመዛሙርቱ ሲያስተምር እንመለከታለን ፡፡ ፍቅር ማለት ኢየሱስ እኛን እንደወደደን ሌሎችን መውደድ ነው ፡፡ እሱ ደግሞ የወደደን ነፍሱን ስለእኛ አሳልፎ እስኪሰጠን ድረስ ነው ፡፡ ኢየሱስ እንዲህ ሲለን ሌሎችን እንደዚህ መውደድ ቀላል ስለሆነ አይደለም ግን በቁጥር 4 ላይ በእኔ ባትኖሩ ማፍራት አትችሉም ብሏል ኀላም ወደአብ ሲሄድ ብቻችሁን እንዳትሆኑ መንፈስ ቅዱስን እልክላችኀለሁ ብሎናል ፡፡ ስለዚህ ሰዎችን ከልብ መውደድ (ክፉ ያረጉብንን ጭምር) በስጋ አይን በጣም ከባድና የማይታሰብ ነው ፡፡ ግን በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ እንችላለን ፡፡ ኹልጊዜ በልባችን ከነድካማችን መንፈሱን መጠማት ይኹንልን ፡፡


(የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 15)
----------
12፤ እኔ እንደ ወደድኋችሁ እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ ትእዛዜ ይህች ናት።

13፤ ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም።

14፤ እኔ ያዘዝኋችሁን ሁሉ ብታደርጉ እናንተ ወዳጆቼ ናችሁ።

#መልካም ቀን
344 viewsedited  02:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-20 07:39:18
#ቀን_ሃምሳሁለት ፶፪/52 ረቡዕ

" ሙሴም በምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ እንዲሁ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ይሰቀል ይገባዋል።"
(የዮሐንስ ወንጌል 3:14-15)


እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን ጊዜ ህዝቡን ከስጋ ሞት ሊያድን ሙሴን የነሀሱን እባብ በመስቀል ላይ እንዲሰቅል አደረገ ፡፡ ያንን የተሰቀለ እባብ ያየ ሁላ ከስጋዉ ሞት ይድን ነበር ፡፡ በእርግጥ በመስቀል ላይ የተሰቀለዉ እባብ የሚወክለዉ እርግማንንን ሀጢያትን ክፋትን በደልን ነበር ፡፡

በሚሻለዉ በአዲሱ ኪዳን ግን እግዚአብሔር ህዝቡን ከስጋዊ ሞት ሳይሆን ከስጋ ሞት ከሚከፋዉ ዘላለማዊ ሞት ሊያድን አንድያ ልጁን በመስቀል ላይ እንዲሞት ወሰነ ፡፡ ኃጢያት የማያዉቀዉንም ቅዱስ ልጁን በመስቀል ላይ ስለሁላችን በደል ኃጢያት አርጎ ስለኛ ክፋት እኛን ለማዳን ሰቀለዉ ፡፡


ማጣቀሻ

(ኦሪት ዘኍልቍ ምዕራፍ 21)

6፤ እግዚአብሔርም በሕዝቡ ላይ እባቦችን ሰደደ፥ ሕዝቡንም ነደፉ፤ ከእስራኤልም ብዙ ሰዎች ሞቱ።

7፤ ሕዝቡም ወደ ሙሴ መጥተው። በእግዚአብሔርና በአንተ ላይ ስለ ተናገርን በድለናል፤ እባቦችን ከእኛ ያርቅልን ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸልይልን አሉት።

8፤ ሙሴም ስለ ሕዝቡ ጸለየ። እግዚአብሔርም ሙሴን። እባብን ሠርተህ በዓላማ ላይ ስቀል፤ የተነደፈውም ሁሉ ሲያያት በሕይወት ይኖራል አለው።

9፤ ሙሴም የናሱን እባብ ሠርቶ በዓላማ ላይ ሰቀለ፤ እባብም የነደፈችው ሰው ሁሉ የናሱን እባብ ባየ ጊዜ ዳነ።

2ኛ ወደ ቆሮንቶስ 5:21

እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው።

መልካም ቀን
317 views04:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-19 08:12:32
#ቀን_ሃምሳአንድ ፶፩/51 ማክሰኞ

" ... #የልጁም_የኢየሱስ_ክርስቶስ_ደም_ከኃጢአት_ሁሉ_ያነጻናል።"
(1ኛ የዮሐንስ መልእክት 1:7)

ከአዳም ጀምሮ የሰዉ ልጅን ባሪያ አርጎ ሲገዛ የነበረዉ ፣ ወደማይፈልግበት የሚነዳዉ ትልቁ የሰዉ ልጅ ጠላት ኃጢያት ነበር ፡፡ ኃጢያት ደግሞ የሚሰራ ብቻ ሳይሆን የሰዉ ማንነት ሆኖ ሰዉን ከአምላኩ አጣልቶ ከወንድሙ አባልቶ የሰዉ ልጆችን ሁሉ በምድር ያልተገባ ሕይወት እንዲኖሩ የሚያስገድድ ሀይል ነበር ፡፡
የሰዉ ልጆች በዘመናቸዉ ከጥንት ጀምሮ ከዚህ ጨቋኝ ገዢ ለመላቀቅ ቢያስቡም የሚቻልና የሚዘለቅ አልነበረም ፡፡ አምላክም ፍጡሩን ስለሚወድ ከዚህ እንዲወጡ የተለያየ መንገድ ሲያዘጋጅላቸዉ እንደነበር መፀሀፍ ቅዱስ ይነግረናል ፡፡ ይሁን እንጂ የሰዉ ልጆች አምላክ የሰጣቸዉን ህግ ለመጠበቅ ሲጣጣሩ ነገር ግን ሳይችሉ ደግሞም መስዋት በማቅረብ ለኃጢአታቸዉ ስርየት ደም ሲያፈሱ እንደነበር ቅዱስ ቃሉ ይነግረናል ፡፡

ይህም ሆኖ ዘላቂ መፍትሔ ማምጣት አልተቻለም ፡፡ ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በቀረበ ጊዜ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ስለ ሰዋች ሁሉ ኃጢያት መስቀል ላይ ሰዋዉ ፡፡ ልጁም ኢየሱስ ስለኛ ታዞ በመስቀል ላይ ደሙን አፈሰሰልን ይህንንም ደም ይዞ ስለኛ ዘወትር ሊማልድ በአብ ቀኝ ተቀመጠ ፡፡ አሁን በእርሱ ለሚያምኑ ሁሉ ባፈሰሰዉ ደም ኃጢያታቸዉን ሊያነጻ ስለኛ በአብ ዘንድ ጠበቃ ሆኖ ተቀምጧል ፡፡

የኢየሱስ ደም ከኃጢያት ሁሉ ያድናል ፡፡ ወንድሜ ፥ በኃጢያት ዉስጥ አለህ ፣ ማንነትህ ኃጢያት ነዉ ? እንግዲያዉስ ኃጢአትህን ሁሉ ሊያነፃ ወደሚችል ወደ ኢየሱስ ተመለስ ፡፡

ማመሳከሪያ ጥቅስ ፦
" የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።"
(ወደ ሮሜ ሰዎች 8:34)
314 views05:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-18 07:48:26
#ቀን_ ሃምሳ ፶/50 ሰኞ

" እንዲሁ ክርስቶስ ደግሞ፥ የብዙዎችን ኃጢአት ሊሸከም አንድ ጊዜ ከተሰዋ በኋላ፥ ያድናቸው ዘንድ ለሚጠባበቁት ሁለተኛ ጊዜ ያለ ኃጢአት ይታይላቸዋል። "
(ወደ ዕብራውያን 9:28)

በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት አምነን ለዳንን እኛ ፦ በአብ ዘንድ ሁልጊዜ የሚታይልን ዘራችን ፣ iቋንቋችን ፣ የትምህርት ደረጃችን ፣ የሀብት መጠናችን ፣ የጤና ሁኔታችን ሳይሆን ስለኛ እንደተሰቀለ ያመነዉ ክርስቶስ ነዉ ፡፡ እሱ ደግሞ በእግዚአብሔር አብ ፊት ቅዱስ መስዕዋትና ለእኛ ጠበቃ ነዉ ፡፡

መስቀሉን ስናስብ ፍቅሩን እናስታዉስ ፤
መስቀሉን ስናይ የተከፈለልንን አንርሳ ፤
ይህ ሁሉ ስቃይ ፣ ይህ ሁሉ መከራ በአምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ የደረሰዉ እኛን ከዘላለም ፍርድ ለማዉጣት ስለኛም በአብ ፊት በፍፅምና ለመታየት ነዉ ፡፡

#መልካም_ቀን!
286 views04:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-17 11:07:12
#ቀን_አርባዘጠኝ ፵፱/49 #እሑድ
ሆሣዕና

" ያን መንፈስም፥ በጸጋው ጸድቀን በዘላለም ሕይወት ተስፋ ወራሾች እንድንሆን፥ በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በእኛ ላይ አትርፎ አፈሰሰው።"
(ወደ ቲቶ 3:6-7)

መልካም የሆሣዕና በዓል ይኹንላችሁ፡፡ አዳኙን ጌታ ዛሬም በልባችን "ሆሣዕና፤ በጌታ ስም የሚመጣ የእስራኤል ንጉሥ የተባረከ ነው ... ። " (የዮሐንስ ወንጌል 12:13) ብለን መቀበል ይሁንልን፡፡

" ሆሣዕና - አቤቱ አኹን አድን " ብለን ፀሎታችንንና ልመናችንን ደግሞ ለሀገራችን እና ለአለም ሁሉ ህዝቦች እናድርግ ፡፡

#መልካም_ቀን!
291 views08:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-16 07:16:11
#ቀን_አርባስምንት ፵፰/48 #ቅዳሜ

" ከእናንተም አንዳንዶቹ እንደ እነዚህ ነበራችሁ፤ ነገር ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በአምላካችንም መንፈስ #ታጥባችኋል፥ #ተቀድሳችኋል፥ #ጸድቃችኋል።"
(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6:11)

በጌታ ሳንሆን በፊት አታላዮች ፣ በዳዮች ፣ ዓመፀኞች ፣ሴሰኞች፣ ጣዖትን የምናመልክ ፣ ሌቦች ወይም ገንዘብን የምንመኝ ፣ተሳዳቢዎች .... ነበርን ፡፡ ነገር ግን በጌታ ኢየሱስ ስም ስናምን ኹሉ ተሻረልን ተቀደስን ፣ ጸደቅን ፣ ነጻን ለዛውም ያለ ስራ ፡፡


#መልካም_ቀን!
287 views04:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ