Get Mystery Box with random crypto!

ከራስ ጋር ትግል ተከታታይ ልብወለድ ምዕራፍ=ሁለት ክፍል=55 ሳባ | CHRIST TUBE - ETH🇪🇹

ከራስ ጋር ትግል
ተከታታይ ልብወለድ
ምዕራፍ=ሁለት
ክፍል=55
ሳባ ካሳሁን

ዛሬ ወደ ትምህርት ቤት ለመሄድ እየተጣደፍን ነው ሊዱ ልክ እንደ ህፃን ልጅ እማዬ ያዝ አድርጋት ፊቷን ታሻሽላታለች እሷ ግን ልቧ በጣም የምትወዳቸው ጋሽዬ ጋር ስለነበር እማን እያስቸገረቻት "ሜሪ! ኸረ ሜሪ! ቶሎ በያ!" ብላ ደጋግማ ትጠራኛለች እኔ ስሜቴና ባህሪዬ ፍፁም ተደበላልቀው ለምንም ነገር ግድ መስጠት እንዳቆምኩ ነው ቦርሳዬን ያዝኩና እንደ ወትሮው ቦታ የማልሰጣቸውን እናትና አባቴን "በቃ ሄደናል ሰላም ዋሉ" ብያቸው የመጀመሪያ ትምህርት የምንጀምርበት ቀን እንደመሆኑ ቃሉን አንብበን ፀልየን ክርስቶስ ከፊታችን እንዲቀድም በመንፈሱ ተሞልተን መውጣት ሲገባን አባዬ "ቆይ. .ሜሪ" እያለኝ ቅዱሱን መፅሀፍ ሊያመጣ ሲኔሳ እኔ ግን ሊዱን እያጣደፍኩ ይዣት ወጥቻለሁ ቡቻዬ አሁንም ልክ እንደ በፊታችን ነች ልቧ ፍፁም ንፁህ ነው ከጥርሶቿ ሳቅ አልተለየም ከባህሪዋም አንዳችም ለውጥ የለም እኔን እየተሰማኝ ያለው መንስኤ ወይ ከየት እንደመጣ ተጨባጭ ማስረጃ የሌለው ተስፋ መቁረጥ፣ መሰላቸትና ብቸኝነት ሁሉ እሷ ጋር የሚገለፀው በፈገግታዋ ነው እንደረፈደብን እያወቀች በጣም የምትሳሳላቸውና የፈለገ ቢመጣ እነሱን ሳታይ የማትቀርበት አባዬ የምትላቸው ጋሽዬ ጋር እየሮጠች ሄዳ በመቆሸሹ ምክንያት ከነጭነት ታሪኩ ወጥቶ ቀለሙን በቀየረው ጋቢያቸው ስር ተሸጎጠች። እሳቸውም ዐይናቸው ማየት አይችልምና በጉያቸው እቅፍ ስትገባ የሚንሰፈሰፍሏትን ልጃቸውን ፀጉሯን እየደባበሱ ". . . መጣሽ? ልጄ. .መድሀኒቴ መጣሽልኝ?" አሏት እሷም እጃቸውን ጥብቅ አድርጋ ይዛ "አዎ አባዬ መጣሁ. . ደሞ አባ የሚጣፍጥ ቁርስ ይዤልሀለሁ ላጉርስህ" ብላ ከቦርሳዋ ውስጥ የቋጠረችላቸውን ማዕድ አውጥታ ታጎርሳቸው ጀመር።

የእኔ የተዘበራረቀ ስሜት ግን አይደለም በትዕግስት እስክትጨርስ ሊያስጠብቀኝ በፈገግታ እንኳን እንዳያቸው የማይከፈልበትንም ሰላምታ እንዳቀርብላቸው አላስቻለኝም ራቅ ባለ አንድ ፓል ጋር ደገፍ ብዬ የመሰላቸትና የድብርትን ትንፋሼን በረጅሙ እየተነፈስኩ ሳለ እነ ናሆሜ ከሩቁ ሲመጡ አየኋቸው እነሱም እንደኔ ልክ ከራስ ጋር ትግል ያለውን አስቀያሚ የመረበሽ ስሜት ያህል እንደዚያ ፈገግታቸውና ሳቃቸው ከላያቸው ርቋል በዚያው ድባብ እንዳሉ ሰላም አሉኝና ናሆሜ ብቻዬን መቆሜ ግራ አጋብቶት "ሜሪዬ ሊዱስ?" አለኝ እኔም በምልክት ወደ ጋሼ እያሳየሁት "ያቹትልህ" አልኩት ቢኒ በሁኔታዬ ሳቅ አለና "እንዴ ታድያ አንቺ እዚህ ምን ታደርጊያለሽ ኸረ ኑና ጋሼን ሰላም እንበላቸው" ብሎ እኔና ናሆሜን ግራና ቀኝ ይዞን ወደነ ቡቹዬ ሄድን ጋሼ እጅግ በጣም ትልቅ ፍቅርና የሰው ረሀብ ያላቸው ሰው ናቸው ሊዱ ስታጎርሳቸው ከያዘችው ምግብ ይልቅ እጇን ሳም ያደርጓታል ልክ ድምፃችንን ሲሰሙ በቀልድና በሚያስደስት ጨዋታቸው ተሞልተው "እናንት ጮሌዎች መድሀኒቴን ልትወስዱብኝ ነው አይደል?" አሉንና ሁለቱንም እጆቿን አጥብቀው ያዟት አንዳንዴ ናሆሜ የጋሼ ከሊዱ መለየትን መፍራት ሲያስበው "ሜሪ ግን ጋሼ ሊዱ ከዚህ ስትሄድ እንዴት ነው የሚሆኑት?" ብሎ ይጠይቀኛል በዚያ ሰዐት የኔ ምላሽ እምባ ባቀረረ አይኔ ዝምታ ነበር። ቢኒ ቀስ አድርጎ "ጋሽዬ ትምህርት ቤት ረፍዶብናል ለዛ ነው" አላቸው እሳቸውም ሊዱዬ እንድትማርና አንድም ነገር እንዲጎልባት ስለማይፈልጉ "ሂጅ! ሂጅ መድሀኒቴ ይቺን ታህል ጠረንሽን ካሸተትኩ ከእጅሽ ከቀመስኩ ምን ፈልጋለሁ?" ሂጅ ቡቻዬ" ብለው በዳበሳ እጇን ሳምዋት እሷም እየተፍለቀለቀች "በቃ አባዬ ቻው እሺ! ደሞ ትንሽ ብር ነው የጎደለኝ ሰሞኑን ከየትም ሞልቼ አሳክምሀለሁ ቻውውው" ብላቸው አብረን መሮጥ ጀመርን ትንሽ እንደሮጥንም ከወደ ትምህርት ቤታችን ደረስን ግቢው በሙሉ ተለውጧል በትምህርት ቤታችን አዳዲስ የ""እንኳን ደህና መጣችሁ"" ማስታወቂያዎች ተለጥፈዋል ሳር ቅጠሉ ሁሉ ከበፊቱ እድግ ብለው ለግቢው ውበትን አላብሰውታል የመጀመሪያ ቀን ስለሆነ ሁሉም ተማሪዎች ክፍል አልገቡም በግቢው ውስጥ ስንሄድ ያዩን ሁሉ ዕርስ በዕርሳቸው በመገረም አፋቸውን ከፍተው "ፐ! እነዚህ እኮ ናቸው ከall የዘጉት ፐ 'ኸረ ይመቻቸው አንደኞች! 'ደግሞ ሲያምሩ በጭራሽኮ አይለያዩም' ይባባላሉ አንዳንድ እኛን የማይወዱን በፊት ላይ የወንጌል አርበኞች ሆነን በሄድንበት የምንሰብካቸው ሲቃወሙን የምንባርካቸው ደግሞ በቅናትና በምቀኝነት እያዩን "ቲሽ ባካችሁ አስደግመው እኮ ነው እነዚህን እኮ አብረን ተምረን እናውቃቸዋለን ምንም አያውቁም" እያሉ በውሸት ያሙናል እኛ ግን ከማንነታችን ይልቅ በስሜታችን ስለተዋጥን ምንም ሳይመስለን ክፍላችን የት እንደሆነ መፈለግ ቀጠልን በጣም የሚገርመው ነገር የደረሰን ከእነ ሊያ ጋር አንድ ክፍል ነው ሁላችንም በጣም ደስ አለን ከኬብሮኔ ጋር ብዙም ሳይቆዩ መጡ ደስታችንን መቆጣጠር ስላቃተን ሰላምም ሳንላቸው አንድ ክፍል እንደደረሰን ነገርናቸው እንደጠበቅነው በደስታ ተሞሉና እቅፍ አደረጉን ወዲያውም አንድ በዕድሜ ገፋ ያሉ ለእኛ አዲስ የሆኑ መምህራችን ገቡ እኛም ተከትለናቸው ገብተን ተቀመጥን መምህሩም ራሳቸውን በደንብ ካስተዋወቁን በኋላ "እሺ ተማሪዎች አሁን ደግም አንድ በአንድ እየተነሳችሁ ስማችሁን አሳውቁኝ" አሉን ጥቂት ተማሪዎች ከተናገሩ በኋላ ተራችን ደርሶ ቢኒ ብድግ አለና "እሺ ቲቸር ቢኒያም ሳሙኤል እባላለሁ" ብሎ ቁጭ አለ ቀጣይ እኔ ስለነበርኩ "ሜሮን ሰለሞን" ብዬ ልቀመጥ ስል ቲቸር ወደ ሊዱ እያዩ "ካልተሳሳትኩ አንቺ ሊዲያ ሰለሞን? (ወደ ናሆሜ ዞር አሉና) አንተ ደግሞ ናሆም?" አሉት ሁላችንም ተገርመን እንደማፈር እያደረገን "አዎ ቲቸር" አልናቸው ቲቸርም በሙሉ ዕምነት "Ok ከእናንተ ብዙ እጠብቃለን" ብለውን ሄዱ እኛም ምንም ሳይሰማን ዝም አልናቸው ወዲያው ግን ሊያን ሳያት ወደኛ የነበራት አስተያየት ለየት ያለ ነበር ሰዐት ከሰዐት በቆጠሩ ቁጥር የምንማረውን ትምህርት ትተን ሀሳባችንና ትኩረታችን ሁሉ ጥምና እርካታን ወደሚሰጡን እነዚያ ዕፆች ነበር ታድያ ይሄ ነገር እኔን እየባሰብኝ መጣ ቁጭ ብዬ መማሩ ረፍት ነሳኝ ራሴን ከሚባለው በላይ ወጥሮ ያዘኝ ዝም ብዬ መምህሩን ለመከታተል ስሞክር ይባስ አይኖቼ ማየት እያቃታቸው በእምባ ተሞሉ እስኪብርቶዬን ቀና አድርጌ ልፅፍ ስል እጄ ፍፁም መታዘዝ አቃተው ሰውነቴንም በሀይል ያንቀጠቅጠኝ ጀመር. . .
. . . . . . ይቀጥላል
ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
ቻናሉን ይቀላቀሉ
➥ @CHRIST_TUBE
➥ @CHRIST_TUBE
ሼር በማድረግ ለሌሎች ያድርሱ!