Get Mystery Box with random crypto!

የቀጠለ... #ቃልም_ሥጋ_ሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድር ለምን መጣ? 16. ኃጢአተኞችን | 🗣ወንጌል ለአለም ሁሉ

የቀጠለ...

#ቃልም_ሥጋ_ሆነ


ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድር ለምን መጣ?


16. ኃጢአተኞችን ወደ ንስሃ ለመጥራት

“ኢየሱስም ሰምቶ፦ ሕመምተኞች እንጂ ብርቱዎች ባለ መድኃኒት አያስፈልጋቸውም ኃጢአተኞችን እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም አላቸው።”
ማርቆስ 2፥17

17. ለመሞት

"እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የስንዴ ቅንጣት በምድር ወድቃ ካልሞተች ብቻዋን ትቀራለች፤ ብትሞት ግን ብዙ ፍሬ ታፈራለች። ነፍሱን የሚወድ ያጠፋታል፥ ነፍሱንም በዚህ ዓለም የሚጠላ ለዘላለም ሕይወት ይጠብቃታል። የሚያገለግለኝ ቢኖር ይከተለኝ፥ እኔም ባለሁበት አገልጋዬ ደግሞ በዚያ ይሆናል፤ የሚያገለግለኝም ቢኖር አብ ያከብረዋል። አሁን ነፍሴ ታውካለች ምንስ እላለሁ? አባት ሆይ፥ ከዚህ ሰዓት አድነኝ። ነገር ግን ስለዚህ ወደዚህ ሰዓት መጣሁ።"
ዮሐንስ 12፥24-27

18. የጠፉትን ለመፈለግ እና ለማዳን

“የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቶአለና አለው።”
ሉቃስ 19፥10

19. ለማገልገል

“እንዲሁ የሰው ልጅም ሊያገለግልና ነፍሱን ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም።”
ማርቆስ 10፥45

20. ሠላምን ለማምጣት

"እርሱ ሰላማችን ነውና፤ ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ፤ ይህም ከሁለታቸው አንድን አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ፥ ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው። መጥቶም ርቃችሁ ለነበራችሁ ለእናንተ ሰላምን፥ ቀርበው ለነበሩትም ሰላምን የምስራች ብሎ ሰበከ፤ በእርሱ ሥራ ሁላችን በአንድ መንፈስ ወደ አብ መግባት አለንና።"
ኤፌሶን 2፥14-18

ይቀጥላል...

━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲⇲
─── ❖ ── ✦ ── ❖ ───

SHARE SHARE SHARE
   JOIN US

@christ_mossion
@christ_mossion
@christ_mossion